>

"ታቦት አናሳልፍም!"  አዲስ አበባ ጫፍ  ኦሮሚያ -  4 ምእመናን በጥይት ተመተዋል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ታቦት አናሳልፍም!” 

አዲስ አበባ ጫፍ  ኦሮሚያ –  4 ምእመናን በጥይት ተመተዋል…!!!
ዘመድኩን በቀለ

*…. እስከአሁን 4 ምእመናን በጥይት ተመተው ዞዊ አቢሲንያ ክሊኒክ ገብተዋል። እነ ሙጂብ አሚኖ፣ እነ ጃዋር መሀመድ ሥራቸውን በይፋ ጀምረዋል። ፌደራሎች አሁን በብዛት መተዋል። የተመቱት ይሙቱ ይዳኑ እስከአሁን የታወቀ የለም። ወታደሩም፣ ፖሊሱም፣ መንገድ ዘግተው ታቦት አናሳልፍ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ምእመናኑና ወደ ታቦቱ እየተኮሱ መሆኑን ነው በስፍራው የሚገኙት ምእመናን የሚናገሩት። 
 አዲስ አበባ ጫፍ ቀራንዮ ወይብላ ማርያም ~ በኦሮሚያ ክልል መግቢያ ላይ መከላከያና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ባሉበት የእነ ጃዋር፣ ዐቢይ ሽመልስ ቄሮ ታቦት አያልፍም ብለው ዘግተው ቆመዋል። ተኩስም እንደነበረ እየተነገረ ነው።
“…የበዓሉ በሰላም ማለፍ ያበገነው ብልፅግና የሚሠራውን እያሳጣው ነው። ይሄን ድፍረት አቁሙ። በሶማሊያ ክልል፣ በዱባይ በቤሩት፣ በኵዌት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ በእሳላሞቹ ሃገር እየከበረች፣ በጀርመን ፣ በእንግሊዝ ከፍ ባለ ማዕረግ እየተወደሰች፣ በኦሮሚያ ያውም በአዲስ አበባ ጫፍ እንዲህ አይነት ጥጋብ አያምርም።
“…መላ ኢትዮጵያ ሰላም ሆኖ የሚንበጫበጨው ለማ መገርሳ ለዲሞግራፊ ብሎ ከሀረር፣ ከአርሲና ባሌ ከወለጋ አምጥቶ በሱሉልታ፣ በጣፎ፣ በቡራዩና በአሸዋ ሜዳ ያሰፈራቸው አክራሪ የወለጋ ፕሮና የባሌአሩሲ ወሄ ናቸው። እረፉ። ታቦታችን በሰላም ይግባበት። መንግሥት እንደሁ የአጀንዳ ማስቀየሻ ያለህ እያለ ነው። እረፉ። ሙጂብ አሚኖ፣ ሃምዛ ቦረና እረፉ።
“… ፋሽስቱ ኢጣልያም እንዲህ አልቀበጠ‼
የታቦት አታስገቡም ፍጥጫው ቀጥሏል።
ታቦቷ ባለችበት እንድታድርም መወሰኑ ተነግሯል። 
 
“… አምናም እንዲሁ ነበር። ታቦተ ሕጓ ባለችበት ቀራኒዮ የሺ ደበሌ አካባቢ እንድታድር ተወስኗል እየተባለ ነው። አሁን ባለ ቀይ ቦኔቶቹ ሪፐብሊካን ጋርዶች በብዛት መጥተዋል። አስለቃሽ ጭስና ጥይትም መተኮስ ጀምረዋል። ግን ያው አብዛኞቹ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ናቸው። የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ ኦሮሞ ነው።  የጦሩ ኢታማዦር ሹሙም ማርሻል ብራኑ ጁላ ናቸው። አየር ኃይሉም እንደዚያው። የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም የአዲስ አበባም አዛዡ ኦሮሞ ነው። የፌደራል ፖሊስ አዛዡም ኦሮሞ ነው። ህወሓት ተከሽና ከች እኮ ነው ያለችው።
እስከአሁን የደረሰ ጉዳት ፦
“… እስከአሁን 4 ምእመናን በጥይት ተመተው ዞዊ አቢሲንያ ክሊኒክ ገብተዋል ተብሏል። እነ ሙጂብ አሚኖ፣ እነ ጃዋር መሀመድ ሥራቸውን በይፋ ጀምረዋል። ፌደራሎች አሁን በብዛት ተዋል። የተመቱት ይሙቱ ይዳኑ እስከአሁን የታወቀ የለም። ወታደሩም፣ ፖሊሱም፣ መንገድ ዘግተው ታቦት አናሳልፍ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ምእመናኑና ወደ ታቦቱ እየተኮሱ መሆኑን ነው በስፍራው የሚገኙት ምእመናን የሚናገሩት።
“…ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ስፍራው ቢሄዱ መልካም ነው። ወጣቶች ተረጋጉ። ተረጋጉ ማለት ግን እምነታችሁን አስደፍሩ ማለትም አይደለም። ታቦታችሁን አስደፍሩ ማለትም አይደለም። አንዲት ነፍስ ናት። እንደ ሬት መምረር ያስፈልጋል። ነገር ግን የአባቶችን ምክር እየሰማችሁ፣ እየተናበባችሁ ይሁን።

የታቦት አታስገቡም ፍጥጫው ቀጥሏል።
ታቦቷ ባለችበት እንድታድርም መወሰኑ ተነግሯል

“… በስልካችሁ ቅረጹ። ቶሎ ቶሎም ወደ ወዳጅ ዘመድ መረጃ ላኩ። ይኸው ነው።
•••
ወይ ብላ ማርያም ዘንድሮም እንደአምናው ጥይት ተተኩሶባታል…!!!
የተደራጁ ሰዎች (ቄሮዎች) ያቃጠላቸውን እንጃ ይኽን ሰንደቅ ይዛችሁ አታልፉም ብለው ረብሻ ፈጥረዋል። ጥይቶችም ተተኩሰዋል። 4 ሰዎች ተመትተዋል ። በዚህም የተነሣ ወደ ቀራንዮ መድኃኔዓለም ለመመለስ አልያም እዛው ዳስ ተጥሎ ለምድር እየተመከረ መኾኑን ከቦታው ጥቆማ ደርሶናል።
ሺመልስ አብዲሳ ቄሮን ውጣ ግባ የምንለው እኛ ነን ማለታቸው ይታወቃል። “ግባ!” ቢሉት አይሻልም?
ግን ለምን ኦሮሚያ ብቻ?
• ወይ ብላ ማርያም ⇓
Filed in: Amharic