>

"የዋንጫው ጨዋታ እየቀረበ ነው፤ ጭምብሉም እየወለቀ ፤ ለምዱም እየተገፈፈ ነው...!!!"  (ዘመድኩን በቀለ)

የዋንጫው ጨዋታ እየቀረበ ነው፤ ጭምብሉም እየወለቀ ፤ ለምዱም እየተገፈፈ ነው…!!!” 
ዘመድኩን በቀለ

ሜካፑም እየለቀቀ ነው። ወርቅ ቅቡ ተፈርፍሮ በአፈር፣ በጭቃ የተለበጠው እውነተኛው ማንነቱም እየተገለጠ ነው። ስለ ሰውዬው ማንነት ለማስረዳት ከባድ የነበረው ዘመን አሁን አልፏል። እንሰደብበት፣ እንወቀስበት የርግማን መዓት ይወርድብን የነበረውም ዘመን አልፏል። አሁን ሁሉም በየቤቱ ዱላውን፣ ጡጫውን ቀምሶት ልክ ገብቷል። ቀድመን ያበድን ስናገግም አዲስ እብዶች ሃገር ምድሩን ሞልተዋል። ሳያስበው የህዝብ ድጋፍ እንደ ሎተሪ የወጣለት የበሻሻ አራዳው የድጋፍ ብሩን በቸበርቻቻ፣ በድግሥና በራት በትኖ ጨርሶ አሁን ባዶ እጁን ቀርቷል። አሁን በዲስኩሩ ናላቸው የሚዞር፣ ሲያዩት የሚያስመልሳቸው፣ ቋቅ የሚላቸው በዝተዋል። እንዲያም ሆኖ ነገ ሊደሰኩር ቢመጣ አንጀታቸው የሚንበጫበጭ ሴቶችና ወሴዎች አይጠፉም። የወሴ ነገርማ ከባድ ነው።
“…መጨው ጊዜ ግን ከባድ ነው። ይሄ ጭብጨባ የለመደ፣ ውዳሴ ምግቡ፣ ሙገሳ ልብሱ የሆነ ሰው ልምዱ ሲቀርበት ወደ አደገኛ ጨዋታ መግባቱ የማይቀር ነው። ወዳጄ ቀጣዩ ጨዋታ የዋንጫ ጨዋታ ነው የሚሆነው። ፍልሚያውም ከእስከ አሁኑ የከፋ ነው የሚሆነው። እስከ አሁን በክልል አንዳንድ ከተሞች እና ገጠሮች የነበረው ጨዋታ አሁን በዋና ከተማዋ እና በመሰል ከተሞች ሳይሆን አይቀርም።
“…ሰውየው ቡዱን ለማጠናከር እየተንደፋደፈ ነው። ሱሴ ሱሰኛውን ከአሜሪካ… ጀዌውን ከቂሊንጦ…ሸንሻኙን ከጫካ ማስፈረሙን ተያይዞታል። የቀድሞውን የቡዱንን ፈጣሪና በጡረታ፣ በመገፋትም ከቡድኑ የራቁትን እነ አሰልጣኝ ሂዊንም ሳያስፈርም አልቀረም። በፊት በአደባባይ ይሰድቡት ይወቅሱት የነበሩትም አሁን የማታ ማታ ከጎንህ ነን ማለት ጀምረዋል። ኦነግና ህወሓት በአንድ ላይ ፓርቲ አዘጋጅተው ጭፈራ ጀምረዋል። ደጋፊውም ከአሁኑ “…ይበላሃል፣ ይበላሃል ጅቦ ” የሚለውን የተለመደ መዝሙር እንዲዘምር አጣና ፍልጥ እደላውም ተጀምሯል። ሰይፍ፣ ስለት፣ ቢለዋም፣ ሜንጫና ጎራዴም በብዛት ይከማች ዘንድ በይፋ በየመስጊዱ ቅስቀሳም ተጀምሯል። (ቪድዮ አለኝ) እናም ሰውዬው አደገኛ ቡድን መስርቶ 100 ሺዎችን ፊንታ ሠርቶ አጋድሞ ዋንጫውን ለመብላት አሰፍስፏል። ቋምጧልም።
“…በድኑ ብአዴንን እርሱት። እንደ ባቄላ ከንፍሮው መሃል የሚገኙ ካልተፈጠሩ በቀር እርሱት። በጣት ከሚቆጠሩ፣ ሆዳም፣ ነውረኞች፣ ሙናፊቆች፣ የሰጎን ጭንቅላት፣ የጉማሬ ሆድ ካላቸው ከበድኑ ብአዴን ሰዎች በቀር እስከ አሁን የሶዬው የድጋፍ መሰረት የነበረው ዐማራው በአብዛኛው በግድም በውድም አዚሙ በኃይለኛው ተወግዶለታል። ዐማራው ከሱዳን፣ ከህወሓት፣ ከኦነግና ከግራኝ አሕመድ ደጋፊዋ ከያኔዋ ቱርክ የሚወርድበትን የድሮን፣ የጀትና የታንክ የኳስ ናዳ ለማምከን ከወዲሁ መዘጋጀት አለበት።
“…በወንድሜ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት በኩል በጣና ሀይቅ በገዳመ ዳጋ እስጢፋኖስ ውስጥ ከመሸጉ ጥቂት ምናምንቴዎች ዘንድ እየታደሰ በየጊዜው በሚላክ ክፉ መናፍስት ተይዞ፣ ተጠርንፎ ታስሮ የነበረው ኦርቶዶክሳዊም አሁን አዘሙ በብዛት ወልቆለታል። ትግሬንና ዐማራን ብቻ ለማፋጀት፣ ለማጣላት፣ ለማለያየት በዳኒ በኩል የተላከው መንፈስም ዳኒን ራሱን መትቶት፣ ሽባ አድርጎ፣ ፀጋውን ገፎ የተጠመቀ አህዛብ አድርጎ አስቀምጦታል። ዘንዶው ዳኒን አስበላው።
“… የበሻሻ አራዳው አሁን በዐማራ ባንክ ያስቀመጠውን ጥሪት ስለጨረሰ ከዐማራና ከአገው በሚወለደው በተወዳጁ ጀነራል በአበባው ታደሰ በኩል ዐማራውንና የአንድነት ኃይሉን ለማማለል ዊኒጥ ዊኒጥ እያለ ይገኛል። ዐማራውን ለማማለል የሚደረገውም መንደፋደፍም ብዙም ዋጋ የለውም። አሁን አውሬው እነ ዶክተር ቀሲስ ዘበነ ለማን፣ መምህር ምህረተአብ አሰፋንና መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁን ቢያስፈርም እንኳ ኦርቶዶክስን ወደ ድባቴው መመለስ አይችሉም። የጳጳስ ግዝት፣ የሽማግሌ እርግማንም የተዋሕዶ ልጆችን አይመልሳቸውም። እስቲ ወንድ የሆንክ ሞክር። EBS ለማዳን ወደ ኢቢኤስ እንደመግተልተሉ ቀላል መስሎሃል።
“…መምህር ዘበነ ለማም ቢዝነሱን፣ መምህር ሄኖክም የመጽሐፍ ንግዱን፣ መምህር ርዳስም ኮከብ ቆጠራውን፣ መጋቤ ሃዲስ እሹቱም ብሔራዊ ቲያትር ስታንዳፕ ኮሞዲኖ ነው ኮሜዲውን ይሥሩ እንጂ ለብልጽግና ተሰልፌ አጀንዳ አስቀይራለሁ የሚሉ ከሆነ ይሄ ኢቢኤስን በሻይ ቡና ግብዣ እንደማዳን ቀላል አይሆንላችሁም። ምህረተአብን ያየ ይቀጣ። ተናግሬአለሁ።
“…አሁን ዐማራ ሊጠቃ የሚችለው፣ የሚጠቃውም ዐማራ ማንነታቸውን በከዱ፣ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናቸውን በከዱ፣ የወይዘሮ አሰለፈች ወልደ ሀና የልጅ ልጅ፣ የደቡብ ጎንደር የጋይንቱ ሰንበት ተማሪ የነበረው ከሃዲ፣ አሩሲ ተወልዶ ኦሮሞ አግብቶ ዐማራ ማንነቱን፣ ኦርቶዶክሳዊ እምነቱን እንዲክድ፣ እንዲረግም ተደርጎ አረንጓዴ የዲፕሎማት ፓስፖርት በተሰጠው በፓስተር ዮናታን አክሊሉ፣ በናትናኤል ዳዊት፣ በእነ አቡና እና ለዚሁ ዐማራንና ኦርቶዶክስን እንዲያዋርዱ በአውሬው ፊት የደም ቃልኪዳን ገብተው ከደቡብ አፍሪካ ድረስ በመጣችው በፌቨን ጋሻው አማካኝነት ነው።
“… ሆዳም ዐማራውን፣ ፀረ ኦርቶዶክሱን፣ ለገንዘብ ብሎ ኦርቶዶክሳዊውን ወጣት በመልካም ወጣት ስም መልሶ ዐማራ ማንነቱንና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖቱን እንዲያረክስ፣ እንዲያወግዝ፣ እንዲሰድብ፣ እንዲረግም፣ እንዲዋጋ በሚደረገው ወጣት በኩል የመጨረሻ ሙከራ ሊደረግ ይችላል። ዐማራና ኦርቶዶክስን በእነ ዲያቆን ዳንኤል በኩል መማረኩ ስለከሸፈ፣ ዐማራና ኦርቶዶኩሱን በዐማራ ፓስተሮች በኩል ለመስበር ይሞከራል። እሱም በቅዱሳኑ ጸሎት ይከሽፋል።
“…እነሱ አሰላለፋቸውን ጨርሰው ለዋንጫ ጨዋታ ዝግጁ ሆነው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። አሜሪካ አዲስ አበባ ገብታለች። ሱዳን በቶሎ የውስጥ ጣጣዋን ጨርሳ ለዐቢይ ቡድን ድጋፏን እንድትሰጥ እየተደከመ ነው። ይሰበራል ብለው የጠበቁት ዐማራ እንኳን ሊሰበር ጭራሽ ፌሮ ሆኖ አስደንቋቸዋል። ከሰሜን ወሎ፣ እስከ ሸዋ፣ ከሰሜን ጎንደር እስከ ደቡብ ጎንደር፣ ጤናውን ለማሳጣት ጤናጣቢያውን ቢያወድሙበትም በዳማከሴ፣ በጠበልና በጸሎት ጤነኛ ሆኗል። ፋብሪካው፣ ከብቱ፣ እህሉን ቢያወድሙበትም እሱ እቴ ከቁብም አልቆጠረው፣ አሮጊት፣ መነኩሴ፣ ህጻን፣ ባለትዳር ደፍረው ሞራሉን ለመስበር ቢጥሩም እሱ እቴ የሞራል ልዕልናው ራሳቸውን ካሉበት ፈጥፍጦ በአናታቸው ተክሎአቸዋል። ከመተከል፣ ከኦሮሚያ፣ ገድለው፣ ገድለው፣ አርደው አርደው፣ በግሬደር ጭምር እየቀረጹ ቢያሳዩት እሱ እቴ ብሶበታል። ጭራሽ ንቋቸዋል።
“…ሰንደቅ ዓላማህን አትያዝ ቢሉት፣ ዐዋጅ ቢያወጡበት፣ ቢያስሩት፣ ቢገዝቱት፣ ቢወግሩት፣ ቢቀጠቅጡት እሱ እቴ እንደውም ፈላበት፣ እየተገደለ ወደ ገዳዮቹ አፍጥጦ ይሄድ ጀመር። አሁን ነው ከባዱ ጊዜ። ተዘጋጅ፣ ለዋንጫ ጨዋታው ተዘጋጅ። ዳኛው የእነሱ ነው። ታዛቢዎቹ የእነሱ ናቸው። ትጥቅና ስንቅ አበልም፣ ደሞዝም ከፋዮቹ የእነሱ ናቸው። አንተ ከሰማዩ ዳኛ ከኢትዮጵያ አምላክ ከቅዱስ እግዚአብሔር በቀር የሚደርስብህን በደል የሚቆጥር፣ የሚደግፍህና የሚያበረታህ ስለሌለ በቶሎ ከእሱ ጋር ተጣበቅ።
“… ጫወታው ከመጀመሩ በፊት በቶሎ ወንዝ ወርደህ አሰልጣኝ ካህንህን በንስሀ ሳሙና፣ እጠበኝ በለው። ትንፋሽ ለመቆጣጠር እንዲያመችሁ ፆም የሚባለውን ኪኒን ከአሁኑ ቶሎ ቶሎ ውሰድ፣ የኪዳን ጸሎት፣ ዕጣኑም ቢጤስብህ መልካም ነው። ረጅም ርቀት እንድትጓዝ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበሉ ግድ ነው። ከጨዋታው በፊት ጠበል መጠበልን ከወዲሁ መለማመድ ሸጋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ውዳሴ ማርያም፣ ገድለ ጊዮርጊስ፣ ድርሳነ ሚካኤል፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበቡን አትዘንጋ፣ ዳዊትማ መድገም ከቻልክ ያለጥርጥር ዋንጫው የአንተ ነው።
“…ዋንጫው ዝም ብሎ አይመጣም። መጋጋጥ፣ መሰበር፣ መድማት፣ መቁሰል፣ ማላብ፣ የውኃ ጥም፣ መፈንከት፣ መሞት ሁሉ አለው። ከባድ ፍልሚያ ነው። ጥሎ ማለፉ ላይ እንኳ አይተኸው የለ። ጨዋታው አዎ እጅ ከባድ ነው። እናም ከወዲሁ ተዘጋጅ። በሆድህ፣ በዲስኩር፣ በሴት፣ አትዝረክረክ። ለተቃራኒ ቡድን ጥቃት አትጋለጥ፣ ሁል ጊዜ ልምምድ አድርግ። አዕምሮህ እንዲሠራ፣ መቅኖህ እንዳያልቅ አመንዝራነትን ተው፣ ጋለሞታ ቀሚስ ስር ተወሽቀህ አትዋል፣ እንደውሻ የሴት እግር አትከተል። በሚስትህ እርጋ፣ ልብህ፣ ኩላሉትህ እንዳይፈርስ አንቡላ፣ አረቄ፣ ቢራ፣ ጠጅና ጠላህን መጋፉን ተው፣ ጥርስህ ካካ የገመጠ እንዳይመስል ጫቱን ትፋው፣ አንጀትህን በጫት ጭማቂ አታድርቀው። ሲጋራ፣ ሀሺሽና ሺሻ እያጤስክ የሰይጣን ኩሽና አትሁን። ነግሬሃለሁ።
“…ዐማራ የሆንክ እስላምም ብትሆን ዋንጫውን መበላትህ አይቀርምና ለዐማራነትህ ወጥር። ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል የፈለከውን ሁን ኦርቶዶክስ ከሆንክ ይበሉሃል። ጠቡ ከዐማራነትና ኦርቶዶክስ መሆን ጋር ነው። ለዚህ ነው አክራሪው ወሐቢይና አክራሪው ጴንጤ በመስቀል አደባባይ ያለአቻ ጋብቻ የተጋቡት። ያልተቀደሰ ጋብቻ። አባቴ ይሙት፣ ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት በፈለጋችሁት እናስይዝ አያቸንፉንም። 4 ነጥብ።
•…ስለ ጎንደሬው ጋይንቴ የመልካም አጭቤ በደንብ እሄድበታለሁ። ከሚስቱ ሌላ ስላስወለዳቸው ልጆችም እናወራለን። 12321 ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችንም እንዴት ማዕተባቸውን እንደሚያስበጥስም እንነጋገራለን።
• አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ለብሰሃል ተብሎ ወህኒ ስለተወረወረው ጋዜጠኛም እናወራለን። አሌልቱ ስለታሰሩት የኦሮሞና የዐማራ የተዋሕዶ ወጣቶችም እናወራለን።
• በወይብላ ጥይት በጀርባው ገብቶ በደረቱ ስለወጣው ልጅም እናወራለን። የእመቤታችን ተአምር ይደንቃል እኮ። አውርቼዋለሁ። አወራችኋለሁ።
ይቀጥላል
Filed in: Amharic