>

ዐብይ አህመድ፡ በማንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት ውስጥ የገባ የወያኔና የኦነግ ድቃይ አውሬ! (መስፍን አረጋ)

ዐብይ አህመድ፡ በማንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት ውስጥ የገባ የወያኔና የኦነግ ድቃይ አውሬ!

 

መስፍን አረጋ


በዐብይ አሕመድ ላይ አሁንም ድረስ ተስፋ ያልቆረጥክ አማራ ካለህ ተስፋህን ቁረጥና ራስህን የራስህ ተሰፋ ለማድረግ ቆርጠህ ተነሳ፣ ተነሳሳ፡፡  የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ወይም ኦነግ ሳይሆኑ፣ ወያኔ ከኦነግ የደቀለው ዐብይ አሕመድ የሚባል በሽተኛ ግለሰብ መሆኑን ያልተረዳህ አማራ ካለህ ደግሞ እርምህን አውጣና፣ በቀንደኛው ጠላትህ ላይ አስቀድመህ ዝመት፡፡    


ሰካራም ባል ሚስቱን አድንቆ እንደማይጠግብ የታወቀ ነው፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሚያወራው ስለሷ ወደርየለሽነት ነው፡፡  ይህን የሚያደርገው ደግሞ በሰካራምነቱ ሳቢያ በሚስቱ ላይ የሚደርሰው ዘርፈብዙ ጉስቁልና ሕሊናውን ስለሚሸነቁጠው ነው፡፡  እንዲህ ዓይነቱን ባሕሪ ልቦናሲነኛወች (psychologists) ማካካስ (compensation) ይሉታል፡፡  ባጠቃላይ አነጋገር ማካካስ ማለት ያንድን ዘርፍ ደካማነት በሌላ ዘርፍ ጠንካራነት ለመዋጥ (ለመሸፋፈን ወይም ለማድበስበስ) ሲባል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚደረግ ያላሰለሰ ጥረት ማለት ነው፡፡ 

የዐብይ አህመድ ድርጊቶች ሁሉም የሚጠቁሙት ግለሰቡ በሥርሰደድ (chronic) የማካካስ በሽታ በጽኑ የታመመ  የልቦናሲን (psychology) በሽተኛ ሳይሆን እንደማይቀር ነው፡፡  ዐብይ አህመድ የልቦናሲን በሽተኛ መሆኑን ለመጠርጠር ደግሞ ልቦናሲነኛ (psychologist) መሆን አያስፈልግም፡፡  አኳኋኑ ግልጽ ስለሆነ፣ ምንነቱን ለመረዳት ልቦናሕግ  (ሕገ ልቦና፣ common sense) ብቻ በቂ ነው፡፡             

ስለ ሰላምና ስለ ፍቅር አውርቶ የማይታክተው ዐብይ አህመድ፣ የሰላምና የፍቅር ቀንደኛ ጠላት ስለሆነ ይሆናል፡፡    ነጋ፣ ጠባ ጦቢያ አትፈርስም የሚለው፣ ቀን ከሌት የሚያስበው ጦቢያን ስለሚያፈራርስባቸው መንገዶች ስለሆነ ይሆናል፡፡  ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ መግደል መሸነፍ ነው የሚለው ደግሞ ማሸነፍ መግደል ነው በሚል መርሕ የሚመራ ደም ጠማሽ ስለሆነ ይሆናል፡፡  ደም ጠማሽ መሆኑን ደግሞ በግልጽ የሚያሳዩ አያሌ ምሳሌወችን መጥቀስ ይቻላል፡፡  እኔን ብትነኩ ባንድ ጀምበር መቶ ሺወቻችሁ ትታረዳላችሁ በማለት ሳይሰቀጥጠው በኩራት የሚናገር ግለሰብ፣ የቆሪጥ ጭራቃዊ መንፈስ የተጠናወተው፣ የሰው ደም ጥሙ መቸም የማይረካ፣ ደም ጠማሽ ካልተባለ በስተቀር ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡   

በልጅነቱ ጫካ ገብቶ ሐይማኖትና ምግባር ከሌላቸው፣ በነውር ከተጨማለቁ፣ በጎጠኝነት ከታወሩ፣ በጥላቻ ካበዱ፣ በስቃይ ከሚደሰቱ፣ በደም ከሚታጠቡ ከወያኔ ጉምቱወች ጉያ ሥር ያደገ ግለሰብ በኣካልም ሆነ በመንፈስ ጤነኛ የመሆኑ ዕድል እጅግ የመነመነ ነው፡፡  በዚያው መጠን ደግሞ ከባድ ወንጀለኛ የመሆኑ ዕድል በጣም ከፍተኛ ነው፡፡  ስለዚህም ዐብይ አሕመድ እንዳይታወቁበት የሚፈራቸው አያሌ ጉዶች ሊኖሩት ይችላሉ ማለት ነው፣ አሉትም ተብሎ ይጠረጠራል፡፡  ጉደኛ ከሆነ ደግሞ ጉዱን የሚያውቁበት ሰወች በመረጃቸው እያስፈራሩት (black mail) አድርግ ያሉትን ሁሉ እንዲያደርግ ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡  

ዐብይ አህመድ ጃዋር ሙሐመድንና ለማ መገርሳን አለቅጥ የሚፈራቸው ወዶ ሳይሆን በጉዱ ምክኒያት በግድ ተገዶ ሊሆን ይችላል፡፡  ጦቢያ ከኦሮሚያ ትውጣ (Ethiopia out of Oromia) የሚለው ጃዋር ሙሐመድ ያገኘውን ክፍተት የሚበረግድ ወንበዴ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ሱሴ የሚለው ለማ መገርሳ ደግሞ ባገኘው ቀዳዳ የሚገባ ሸለመጥማጥ ነው፡፡  ወያኔወች ደግሞ ዐብይ አሕመድን እናጋልጥኻለን እያሉ ዘወትር የሚዝቱበት የያዙትን ቢይዙበት ነው፡፡  እስካሁንም ያላጋለጡት ደግሞ ዐብይ አሕመድ ባጸፋው እንዳያጋልጣቸው ስለሚፈሩ ነው፡፡  እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ፡፡ 

አያሌ አገር ወዳድ ጦቢያውያን የዐብይ አህመድ ወላጅ እናት አልኦሮሞ (non-oromo) መሆን የዐብይን የኦሮሞ ጎጠኝነት ስሜት ያለዝበዋል የሚል እምነት ነበራቸው፡  ታሪክ የሚመሰክረው ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፡፡ ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ የዚያ ብሔር ጽንፈኛ ከሆነ፣ በብሔር አባልነቱ ሊጠረጠር እንደማይገባው በግልጽ ለማስመስከር ሲል ያማያደርገው ድርጊት የለም፡፡  ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  አብዛኞቹ ያሜሪቃ ነጭ ልዕለኛወች (white supremacists) አንግሎ-ሳክሶኖች ከነጭ የማይቆጥሯቸው የደቡብና የምሥራቅ አውሮጳ መደዴወች ናቸው፡፡  

በወያኔ በኩል ደግሞ ኤርትሬውን በረከት ስምዖንን መጥቀስ ይቻላል፡፡  የወያኔን ፀራማራ አጀንዳ በማራመድ ረገድ ከራሱ ከመለስ ዜናዊ በላይ ትልቁን ሚና የተጫወተው በረከት ስምዖን ነው፡፡  እነ አዲሱ ለገሰን፣ ተፈራ ዋልዋን፣ አለምነው መኮንንን፣ ከበደ ጫኔን፣ ተመስገን ጥሩነህንደመቀ መኮንንን፣ … የመሳሰሉትን አማራ ነኝ ባይ ፀራማሮች፣ በብአዴን ቁልፍ፣ ቁልፍ ቦታወች ላይ አስቀምጦ፣  በአማራ ሕዝብ ላይ መርገምት ያወረደው፣ ይህ ጎንደር ተወልዶ ያደገ፣ የበላበትን ወጭት ሰባሪ እኩይ ግለሰብ ነው፡፡  በረከት ስምዖን ደግሞ ከወያኔወች በላይ ፀራማራ የሆነበት አንዱ ምክኒያት፣ ተጋሩ ባለመሆኑ ተጋሩወች እንዳይጠረጥሩት ነው፡፡ 

ጌታቸው አሰፋ በላኤአማራ የሆነበት አንዱ ምክኒያት አባቱ አማራ ቢሆኑም ‹‹ከሙሉ ትግሬወች›› በላይ አማራጠል መሆኑን ለማስመስከር ነበር፡፡  ጌታቸው ረዳ ደግሞ ከአማራ ጋር ሒሳብ እናወራርዳለን አለበለዚያ ሲኦል እንወርዳለን እያለ የሚቅለበለበው ወዶ ሳይሆን፣ ባማራነቱ እንደሚጠረጠር ስለሚያውቅ ጥርጣሬውን ለማስወገድ ነው፡፡  

ዐብይ አሕመድ ደግሞ በአማራ ጥላቸው ወደር የሌለው ኦነጋዊ አውሬ መሆኑን በስካሁን ድርጊቶቹ በግልጽ አስመስክሯል፡፡  ኦነጋውያን በመቶ ዓመታት እንፈጽመዋልን ብለው ሊያስቡት ቀርቶ ሊያልሙት የማይችሉትን፣ በረቀቀ የሽንገላ ክሂሎቱ በሦስት ዓመታት ብቻ በመፈጸም ኢትዮጵያን የኬኛ፣ በኬኛ ለኬኛ አድርጓታል፡፡  ባጭሩ ለመናገር  ዐብይ አሕመድ ማለት የሦስት ሺ ዓመት አገር በሦስት ዓመት ያፈራረሰ የሉባወች ሉባ ነው፡፡     

ለኦነጋውያን የዋለው ውለታ ወደርየለሽ ቢሆንም፣ በኦነጋውያን የዘር እሳቤ መሠረት ሙሉ ኦሮሞ አይደለም ስለሚባል ግን፣ ኦነጋውያን መቸም ቢሆን አያምኑትም፡፡  እሱም ራሱ ቢሆን፣ በማንነቱ ምክኒያት በኦነጋውያን እንደሚጠረጠርና ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቅ፣  እያንዳንዷ ድርጊቱ በዘር መነጽር እንደምትመረመር፣ ትንሽ ቢሳሳት ግዙፍ ውለታው መና ቀርቶ ከሃዲ ተብሎ ተዘቅዝቆ እንደሚሰቀል ወይም ደግሞ ከነነፍሱ ቆዳው እንደሚገፈፍ ነጋሪ አያስፈልገውም፡፡  

ስለዚህም ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ከፈለገ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡  ይህ ማለት ደግሞ ዐብይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የበለጠ እና የበለጠ እያረመነ (አረመኔ እየሆነ) ይሄዳል ማለት ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አህመድ ማለት በማንነቱና በምንነቱ ምክኒያት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ የኦነግ አውሬ ነው፡፡  ካዟሪቱ ነጻ የሚያወጣው ደግሞ ዳግም ምጽአት ብቻ ነው፡፡   

በዐብይ አሕመድ ላይ አሁንም ድረስ ተስፋ ያልቆረጥክ አማራ ካለህ ተስፋህን ቁረጥና ራስህን የራስህ ተሰፋ ለማድረግ ቆርጠህ ተነሳ፣ ተነሳሳ፡፡  የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት ወያኔ ወይም ኦነግ ሳይሆኑ፣ ወያኔ ከኦነግ የደቀለው ዐብይ አሕመድ የሚባል በሽተኛ ግለሰብ መሆኑን ያልተረዳህ አማራ ካለህ ደግሞ እርምህን አውጣና፣ በቀንደኛው ጠላትህ ላይ አስቀድመህ ዝመት፡፡    

Email: መስፍን አረጋ mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic