>

እስክንድር ነጋ ጤነኛ ነው....!!! (ፍርድ አወቅ ንጉሴ)

እስክንድር ነጋ ጤነኛ ነው….!!!

 

ፍርድ አወቅ ንጉሴ

*… የዚህ ባንዲራ ሀይል ልዩ ነዉ!
ባንዲራዉን ሊያጠፉ የሚነሱ ሁሉ በባንዲራዉ እግር ስር ተንበርካኪ ናቸዉ…!!!
 
*….. ሰሞኑን እስክንድር ነጋ ከእስር ከተፈታ በኋላ ባደረጋቸው ነገሮች ሳቢያ በተለይ ይቺን ሁለት ቀን አብዛኛው ሰው አፌዘበት፣ ጤንነቱን በመጠራጠር ጠየቀ፣ even በሚያሳፍር መልኩ የቤተሠቡም ስም ተነሳ። ለሚያልፍ ግዜ፣ ላይክ ለመሠብሠብ ሲባል ይህን ያህል መተዛዘባችን ይገርማል
1- አንተ መንግስት ‘ይህን ባንዲራ መልበስ አይቻልም’ የሚልበት የሚልበት ቀንና ተያያዥ ችግሮች የተከሰቱ ቀን ደጋግመህ እዬዬ ትላለህ። ከሁለት ቀን በኋላ ግን ጉዳይህም አይደለም። ትዝም አይልህም። ግና በአዘቦቱ ቀን፣ ምንም ነገር በሌለበት ዕለት “ይሄን ባንዲራ የመያዝ መብት አለኝ” ብሎ የሚናገር ሰው ስታይ ‘ዊርድ’ ይመስልሃል።
ጤንነቱ ያጠራጥርሀል። ግን ያለፉትን አምስት ስድስት ዓመታት የሀገራችንን ፖለቲካል ዳይናሚክስ በጣም ብትረዳ እስክንድር ከትክክለኛነቱም በላይ ላንተም መብት ነበር የጮኸው❗እሡ ስለመሬት እና ስለተለያዩ ፍትሃዊ ነገሮች ሲያወራ የምትሰማውም አብዶ አይደለም። አንተ በየቤትህና በተለያዩ ስፍራዎች ከምታምናቸው ሰዎች ጋር የምታወራውን የአደባባይ ምስጢር ነው እሱ በአደባባይ የሚጠይቀው።
የእስክንድር ችግሩ እሱ ልክ እንዳንተ ወይም እንደኔ የአጀንዳ ሠው አይደለም። የመርህ ሰው ነው። አንድ ማሳያ ልስጥህ። በጥምቀት በዓል ላይ ህይወታቸው ስላለፈ ወጣቶች የዕለቱ ለት ብዙ አልክ፣ ብዙ ሙሾ አወረድክ፣ ላይክ ሰበሰብክ። ከዛ ቀን በኋላ በዛ ዙሪያ ምን አልክ? ምን ፃፍክ? ቤተሠቦቻቸውንስ አፅናናህ? የሆነ ቀን እስክንድር ይሄን ቢያደርግ ግን አይግረምህ። እሱ የአጀንዳ ሰው ሳይሆን የመርህ ሠው ነውና!
.
2 – ሌላው በጣም የዘገነነኝ “ልጁ አይናፍቀውም? ሚስቱ አትናፍቀውም?” አይነት መረን የለቀቀ ክብረ ነክ አስተያየቶች ናቸው። ‘አለማወቅ ደግ ነው ብዙ ያስወራል።’ ይላል ያገሬ ሰው። ስማኝ ወንድሜ በጣም አስቀያሚው ነገር ላይክ ለመሠብሠብ አንድን ሠው ከልጅ ወይም ከቤተሠብ ጋር አያይዞ መዝለፍ ፍፁም ብልግና ነው። (ልጅ ያለው ሰው ስለማወራው ነገር በደንብ ይገባዋል)
እንኳን እንደ እስክንድር አይነቱ የዓላማ ሰው እኛ እዚህ መንደር የባጥ የቆጡን የምንቀባጥር ሰዎች እንኳን ለመሠረትነው ቤተሠብ ፍቅርና ክብር አለን። የሚገርመው ግብዝነታችን ነው እንጂ እስክንድርም ፍቅርን የምታውቀው  ቆንጆ ሚስቱ፣ በጣም የሚያሳሳው አስተዋይ ልጁ ይናፍቁታል። በነርሱ ናፍቆት ውስጡ ሳይደማ ቀርቶ አይደለም። ግን የሱ ችግር ከቆንጆዋ ሚስቱ እና ከልብ ንፁሁ ልጁ በላይ ኢትዮጵያን ወደደ። ፍትህን ወደደ። እኩልነትን ወደደ። እሱ ስላንተ ይሟገታል፣ አንተ እዚህ ቁጭ ብለህ ፀጉር ሰንጥቅ።
ደሞ ደርሶ ለቤተሠቡ አዛኝ ሆነን መገኘታችን። ሆ! የኔ እህት አንቺ በልጅነትሽ በማዳበሪያ ደረቅ እንጨት በምትለቅሚበት፣ አንተ ብቻህን ሽንት ቤት መሄድ በምትፈራበት ዘመን’ኮ እስክንድር ከባለቤቱ ጋር በመሆን ከወያኔ ጋር አንገት ላንገት ተናንቀው ጋዜጦችን ያሳትሙ፣ ህዝብን ያነቁ ነበር። (በቁም እስር ላይ ሆነውም ጭምር) 1997 ዓ.ም ያን የመሠለ የህዝብ መነቃቃት ለመፈጠሩ የእስክንድርና ባለቤቱም አሻራ ሠፊ ነው።
.
3- እዚህ ፌስቡክ ላይ ያሉ አንተን ‘አሃዳዊ’ የሚሉህ ሌሎቹ ጎራዎች በዚህ መልኩ act ሲያደርጉ አይተህ ታውቃለህ? የትኛውም ነገር አንድነታቸውን ሲሸረሽር፣ አቋማቸውም ሲለያይ ገጥሞህ ያውቃል? የማወራው ከገባህ በቂ ነው።
   የዚህ ባንዲራ ሀይል ልዩ ነዉ::ባንዲራዉን ሊያጠፉ የሚነሱ ሁሉ በባንዲራዉ እግር ስር ተንበርካኪ ናቸዉ::
———
ይህ ባንዲራ ለሽህ ዘመናት የኢትዮጵያ ጠላቶችን አፈር አስግጧል::
የቅርብ ዝመናት የኢትዮጵያ ጠላቶችን እንኳን ብናይ ግብጾች:ጣሊያኖች:ቱርኮች በጣም በቅርቡ ደግሞ ወያኔዎች በዚህ የባንዲራ ሀይል አፈር ግጠዋል::
አረንጓዴዉ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ላይ ሀይል አለ::
የምን ሀይል ብለህ ጠይቅ?
የ እግዚአብሄር የቃል ኪዳን ሀይል አለብት::
ለዚህ ነዉ መከራ የሚበዛበት::ግን የመጨረሻዉ አሸናፊም ይሄ ባንዲራ ነዉ::
ተረኛዉ ኦህድዴድ ይሄን አዉቀህ ከዚህ ባንዲራ ጋር የጀመከዉ የጠላትነት መንፈስ የት እንደሚያደርስህ ታያለህ::
የዚህ ባንዲራ ሀይል ልዩ ነዉ::ባንዲራዉን ሊያጠፉ የሚነሱ ሁሉ በባንዲራዉ እግር ስር ተንበርካኪ ናቸዉ::
Filed in: Amharic