>

የትናንቱ የዕዳነች ዕባቤ ሴራና የአቡነ ማትያስ ተጋድሎ!  (ንፍታሌም ቤተ-ተዋህዶ)

የትናንቱ የዕዳነች ዕባቤ ሴራና የአቡነ ማትያስ ተጋድሎ! 

ንፍታሌም ቤተ-ተዋህዶ

ትግል ከዚህ ይጀምራል ምዕመናንን ለማንቃት ማዛመት ግዴታችሁ ነው የተዋህዶ ልጆች!!!
ከትናንት ወዲያ ማታ የአዲስ አበባ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ቀንአ ያደታ (ከወራት በፊት የመከላከያ ሚንስትር የነበረው)፣ በአብይ አህመድ ትዕዛዝ ቤተክህነት ቁጭ ብሎ ያለ እውቀቱ ያለ ቦታው ቤተክርስቲያን ላይ እንደመዥገር የተጣበቀባት ዛፍ ቂቤ ቀቢው ቀሲስ በላይ እና አንድ ለጊዜው ስሙን ያላወቅነው ግለሰብ ዕዳነች ዕባቤ ከቢሮዋ ቀጭን ትዕዛዝ እንዲያስተላልፉ ወደ ቤተክህነት ላከቻቸው።
እዛ ሲደርሱም መጀመሪያ ያገኙት የሴትዮዋም የመንግስትም ቀኝ እጅ በመሆን ሴራ እየጎነጎኑ ቤተክርስቲያናችን ልዕልናዋን እንዳታስከብር አረንቋ የሆኑት፣ የአባቶቻችን ምስጢር ከቤተክህነት ወደ ቤተመንግሥት የሚልኩት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የሆኑት አባ ዮሴፍን ነው።
ቢሮ ውስጥ ሴራ ከሸረቡ በኋላ ተያይዘው ወደ ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ቢሮ ይሄዳሉ። አባታችንም ለአቡነ ዮሴፍ ማናቸው ብለው ይጠይቋቸዋል። የቤተክህነት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጁ ቀሲስ በላይ ፈጠን ብሎ «የመንግስት ሰዎች ናቸው። የመንግስትን ውክልና ይዘው ነው የመጡት» ብሎ ይመልሳል። ቅዱስነታቸውም ከራሳቸው ለማረጋገጥ መንግሥት ወክሏችሁ ነው የመጣችሁት ይሏቸዋል። ቀንአ ያደታም «አዎ» ብሎ መለሰ በትዕቢት። #አባታችን በስጨት ብለው «ለመሆኑ እናት ቤተክርስቲያን መንግስትን ምን ብትበድለው ነው ይህን ያህል ግፍ የሚፈፅምባት?» ብለው ብዙ ጉዳዮችን አንስተው ጠየቁ። ቀንአ ያደታ መለሰ፣ «አሁን ያነሷቸው ጉዳዮች እኛ ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት እንወያያለን።
የዛሬ የእኛ አመጣጥ የነገው የስብሰባ ቦታችን ሸራተን አዲስ መሆኑን ለመናገር ነው ይላቸዋል።» አቡነ ማትያስም ተገርመው «ልጄ ነገ ቋሚ ሲኖዶሱ የሚሰበሰበው መደበኛ ስብሰባውን ነው። እናንተን ለማናገር የፈለግነውም በዚህ ስብሰባ ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ደሞ በመንበሩ እንዲካሄድ ቀኖና ቤተከርስቲያን ይደነግጋል። ስለዚህ ወደዛ መምጣት ስለማንችል እናንተ ለትንሽ ሰዓት ነው ተቸገሩልን።» ይላሉ። ቀንአ ያደታም በፍፁም የመንግሥት ባለስልጣናት ወደዚህ እንደማይመጡ ተወስኖ ያለቀ ጉዳይ እንደሆነ ይናገራል። «እንደዛ ከሆነ እኔ በራሴ የምወስነው ስላልሆነ ጠዋት ስብሰባችን ሲደርስ ለአባቶች ነግሬ እናሳውቃችኋለን» ብለዋቸው ሰዎቹ ከቤተ ክህነት በV8 መኪናቸው ውስጥ ከነአጃቢዎቻቸው እየከነፉ ወጡ። አይነጋ የለ ነጋ። ጠዋት የቋሚ ሲኖዶስ አባላት የሆኑት አባቶቻችን ወደ ቤተክህነት ገና መድረስ እንደጀመሩ አካባቢው በፌድራል ፖሊስ ተወረረ። ብዛት ያላቸው ነጭ የመንግስት V8 መኪኖችም ተደረደሩ። አቡነ ማትያስ ምንድነው ጉዱ ሲሉ። ወደ ሸራተን ልንወስዳችሁ ነው የመጣነው ይላል አዛዡ። መኪኖቹም የተዘጋጁት ለእናንተ ነው ይላቸዋል። በዚህ ጊዜ አባቶቻችን ወደ ስብሰባው ገብተው አንድ አቋም ያዙ። «ለመሆኑ አዳነች ማነች?? ቅዱስ ሲኖዶሱ በቀኖና ቤተክርስቲያን እንዳይሄድ የተፈለገውስ ለምንድነው? አንድ ካድሬ የቤተክርስቲያንን ልዕልናና ክብር ብሎም መፈራቷን ለማውረድ ሲታትር እኛ እንዴት ተኝተን ከረምን?? ለመሆኑ ቀሲስ በላይስ እዚህ ጉዳይ ውስጥ ምን አግብቷቸው ነው በመንግስትና በኛ መሐል አሳላጭ ሆነው የተገኙት???» በሚልና በሌሎችም ጥያቄዎች ሁሉም ሊቃነ ዻዻሳት በገኑ። የቅዱስ ፓትርያርኩ ግን የተለየ ነበር። በቤተክርስቲያን መደፈር መናቅና መዋረድ የሚዙትና የሚጨብጡት አሳጣቸው። ንዴቱም ግለቱም ቁጭቱም ወደ ሌሎች አባቶች በፍጥነት ተዛመተ። ብቻ አቡነ ማትያስ Pace Maker ነበሩ።  ከሁሉም ግን ተለይቶ ጳጳሳቱ አንሄድም ወደሚል ድምዳሜ እየደረሱ መሆኑን ሲያይ አንድ ሰው ተቃጠለ። ይህ ሰው አቡነ ዮሴፍ ናቸው። ደበቅ ብለው ለከንቲባዋ «ሰዎቹ እንቢ አሉ» ብለው  text አደረጉላት። ሸራተን ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ከነ ግብረ አበሮቿ ቁጭ ብላ «እኛ መጥተን እነሱ ቀሩ» ለማስባል ሴራ ስትሸርብ የቆየችው እዳነች እባቤ «እሺ!» የሚል text መልሳላቸው ፎቶ ተነስታ ከሸራተን ወጣች። ዜናም አሰራች። በሚገርም ሁኔታ የቋሚው ቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት እዛው አዲስ አበባ የሚገኙት አቡነ ያሬድ በስብሰባው አልተገኙም። አባቶች አንሂድ እንደሚሉ ቀድመው ስለሚያውቁ የውሳኔው አካል በመሆን መንግሥትን ላለማስቀየም ነው። እሳቸውም ሌላው የአቡነ ዮሴፍና የአብይ ቆሪጥ ናቸው። አባቶተቻችንን ወደ ሆቴሉ ለመውሰድ የመጣው የእዳነች እባቤ #ግሳንግስም ቁርጡን ተነግሮት ከአካባቢው ነቅሎ ወጣ።
ከትናንቱ ክስተት ቤተክርስቲያን የተማረችው ነገር ቢኖር ትልቁ ጠላታችን ያለው እኛው ጉያ ውስጥ መሆኑን ነው። እስከዛሬም መረጃ ለመንግስት በመስጠት፣ ውሳኔ በማስቀየር፣ ቀጠሮ እንዲራዘም በማንዛዛት፣ ሴራና ግራ መጋባትን ቤተክህነት ውስጥ በመፍጠር፣ በአባቶች መሐል መናብብ እንዳይኖር ነገሮች ተድበስብሰው እንዲያልፉ የሚያደርጉት እነዚህ ሰዎች ናቸው።
1-አቡነ ዮሴፍ
2-አቡነ ያሬድ
3-ቀሲስ በላይ
ቅዱስ ሲኖዶስ መጀመሪያ ውስጡን ያጥራ። እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞችን እየገረፈ ከቤተክህነት ያስወጣ። መጀመሪያ ውስጣዊውን ችግር በድል እንወጣ! ውጫዊው እዳው ገብስ ነው። መንግስት ጆሮው ተይዞ እጁም ተጠምዝዞ በአንድ ቀን ልክ ማስገባት እንችላለን። እኛ የተዋህዶ ልጆች እናንተ ውስጣችሁን አጥርታችሁ አንድም ሆናችሁ ውሳኔ ስጡን እንጂ ለትግበራው አትጨነቁ። ቤተከርስቲያን ወደቀደመ ልዕልናዋና መፈራቷ እንመልሳታለን! የትናንት ወከባ ስብሰባው ሸራተን ይሁን አይሁን ከሚል ከፍ ያለና ጳጳስ ማለት ምንም ማለት ነው፣ እንደሚታዘዙ በኛም ትዕዛዝ እንደሚሄዱ እናሳይ፣ ኦርቶዶክስ ለብልፅግና የማትመች ወግ አጥባቂ ነች ከሚል የብልፅግና ወንጌል የተቀዳ ነው።
የድንግል ማርያም እርዳታ አይለየን አሜን! 
Filed in: Amharic