>

የባልደራስ አመራሮች ፓስተር ቢንያም ሽታዬን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው ጠየቁ ...!!! ሰለሞን አላምኔ

“…. አየህ ወዳጄ እውነትን ስትይዝ ክብር ቤትህ ድረስ ትመጣለች….!!!”
መስከረም አበራ

የባልደራስ አመራሮች ፓስተር ቢንያም ሽታዬን
በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው ጠየቁ …!!!
ሰለሞን አላምኔ

ብጹዕ አቡነ መቃርዮስ ፓስተር ቢንያም ሽታዬ እውነቱን በመናገር መስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው ብሎ በመመስከሩና እስከ እስር ዋጋ በመክፈሉ እቤቱ ድረስ በመሄድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።አየህ ወዳጄ እውነትን ስትይዝ ክብር ቤትህ ድረስ ትመጣለች።
የፓስተር ቢንያም ሽታዬ ባለቤት ለብጹዕ አቡነ መቃርዮስ ምስጋናቸውን ገለጹ….!!!
ይህንን ፍቅር የምገልፅበት ቃላት የለኝም።አባታችን በጎ ፈቃድዎ ሆኖ ወደ ቤታችን ስለመጡ እግዚአብሔር ይስጥልን።  ጉብኝትዎ እና በረከትዎ የሆነብን እና የደረሰብን ምንም እንዳልሆነ እንድንቆጥር አድርጎናል ። አባት አያሳጣን። ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው። መከባበር መዋደድ አንዱ ስለአንዱ ዋጋ መክፈል አባታችን ይህንን አስተምረውናል።አባታችንንም አብረዋቸው የመጡትንም ወንድሞች  በእኔና  በቤተሰቤ ስም ቸሩ መድሐኒያለም ይስጥልኝ ያክብርልኝ።
 
 የባልደራስ አመራሮች ፓስተር ቢንያም ሽታዬን
በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው ጠየቁ …!!!
ሰለሞን አላምኔ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ማለትም ፕሬዚደንቱ እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በቅርቡ ከእስር የተፈቱትን ፓስተር ቢንያም ሽታዬን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው ዛሬ ሰኞ ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠይቀዋል።
 ፓስተሩ መስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ መሆኑን መግለፃቸውን ተከትሎ በግፍ እስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።
Filed in: Amharic