>
5:13 pm - Saturday April 19, 5851

የዶክተር አብይ ወርቃማ ንግግር በተግባር ሲፈተሽ ውሸት ነው...!!!"  አስቴር (ቀለብ) ስዩም የባልደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር

የዶክተር አብይ ወርቃማ ንግግር በተግባር ሲፈተሽ ውሸት ነው…!!!”

 አስቴር (ቀለብ) ስዩም የባልደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር


“የኛዋ ሴት ሚንስትር ወይም ከፍተኛ ባለስልጣን የተባለች ነች ስለ እነዚህ የታገቱ ሴቶች የጠየቀችው…!!!”
“ፋኖን ትጥቅ ፍታ ማለት ማህተብህን በርስ ማለት ነው ብዬ አምናለሁ…!!!”

https://www.youtube.com/watch?v=465QLdsXCfk

*     *     *     *
እውነት ታሸንፋለች አሳሪዎችሽም የእጃቸውን ያገኛሉ… !!!
በሻህ የጭንቁ
ወ/ሮ ቀለብ ስዩም በቅጽል ስሟ አስቴር ስዩም ከዚህ ቀደም ለእኩልነት ፣ለዴሞክራሲ  እና  ለፍትህ በመወግኗ ፤በሽብር ክስ 3 ዓመት ከ6 ወር አሰቃቂ የእስር ጊዜ አሳላፋለች ። በወቅቱ ወደ ግፍ እስር ቤት ስትወሰድ የ6 ወር እመጫት አራስ ነበረች  ። ብዙ ስቃይ ደረሰባት ።
አስቴር በሽብር ክስ ተሰቃይታ ከእስር ከወጣች በኋላ ፤ በዚያን ወቅት ዶ/ር ዐብይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ” አሸባሪ እኛ ነን፡፡ ኢህአዴግ ይቅርታ ጠይቋል፤ ህዝቡም ይቅር ብሎናል፤ ህዝቡ እኛን ማሰር ነበረት ነገር ግን በይቅርታ አልፎናል፡፡  ” በማለት ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
ዶ/ር ዐብይ ይህን ንግግር ካደረጉ ከሁለት አመት በኋላ ፤  የዶ/ር ዐብይ አስተዳደር አሁንም ዳግመኛ ፣ አስቴር አስቀድሞ ከሳሾቿ እንደ-ሚከሷት ክስ ተከሳ ፣ ወደ እስር ቤት እንድትመለሰ ተደርጓል  ።
አስቴር ዳግመኛ ለእስር በተዳረገችበት ወቅት (በዶ/ር ዐብይ አስተዳደር ዘመን ) የ10 ወር ልጅ አራሳ እያለች ነው።
” እኔ የታገልኩት የምታገለውም  ንብረት በጠራራ ፀሀይ የማይወድምበት ኢትዮጵያን ለማቆም ነው ።  ሀቁ ይህ ሆኖ ሳል መስታወት ሰብረሻል በሚልና ከቆምኩለት ዓላማ ውጭ በሆነ የሀሰት ወንጀል ጠርጥሮ ያለ ፍትሕ እስካሁን እስር ቤት ማቆየት ፍፁም ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው።  የእኛን እውነት የሚዳኝ የፍትህ ስርዓት የት ነው ያለው ?! “በማለት ዳግመኛ በግፍ በታሰረችበት ወቅት በችሎት ፊት ተናግራለች ።
አስቴር ከህወሓት አገዛዝ ጀምራ እስከ አዲሶቹ አሳሪዎች ድረስ “የመከራን ጅራፍ” መቀበል የተገደደችው ፤ ከራሷ እና ከቤተሰቧ ሕይወት በላይ የሐገሯ ና ሕዝቧ ጭቆና ስለሚያንገበግባት እንጅ እንደ ማንም  መኖር ተስኗት አልነበረም፡፡ በትምህርቷ ታታሪ ስትሆን የማስተርስ ዲግሪዋን በተከታታይ 4 ነጥብ በማምጣት በማዕረግ የተመረቀች ግን በመጨረሻ ቃሊቲ እስር ቤት በመሰቃየት ያለች ምርጥ ኢትዮጵያዊ ናት !
ጀግኒት በግፍ ታስራ፤ ስለ አዲስ አበባ ኽየው አለው በማለት  በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆና ቀርባለች ። በግፍ እስር ቤት ሆኖ በምርጫ ተወዳዳሪ በመሆኑ ታሪክ እነ ቀለብ ( አስቴር ስዩም አበራ ) የመጀመሪያዎቹ ናቸው።
   ከግፍ እስር ከተፈታች በኋላ ስለ-ኢትዮጵያ ስለ-ሃገር በተሰኘው መሰናዶ  ” ሴት ፣ እናት ፣ እስር ፣ ፖለቲካ ፤የዶ/ር ዐብይ ንግግር እና ተግባር ” በሚል እርዕስ ጉዳይ ቆይታ አደረገና ።
 ሙሉ የቃለ መጠይቅ  ዝግጅት  https://youtu.be/58BNGNhs8HI በዚህ ማስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል። የተወሰነውን ክፍል በዚህ ቪዲዮ ላይ ይገኛል ፤ መልካም ቆይታ
Filed in: Amharic