>
5:13 pm - Sunday April 19, 3344

የኤርሚያስ አመልጋ በነገር...!!! ሸገር ሾው

የኤርሚያስ አመልጋ በነገር…!!!

ሸገር ሾው

የሰው ልጅ የተፈጠረው ለደስታ አይደለም ይላል ፣
ስለ ኤርሚያስ አመልጋ ብዙ ብዙ ብዙ ዙ ተብሏል…. ከታች ጀምሮ የልጥጥ ልጅ ሀብታሞች የሚማርበት ትምህት ቤት የተማረ ነው ፣ ደፋርና ሪስክ ቴከር ነው ፣ ወርልድ ክላስ ማይንድ ነው ፣ የአለማችን ትልቁ ስቶክ ማርኬት ጅው ጅው የሚልበት ቢሊየ ዳለር የሚንቀሳቀስብተ ወልስትሪት ባንከር ነው ፣ ሃገሬ ላይ ልስራ ብሎ እንጂ አሜሪካን ውስጥ የከበርቴዎች መኖርያ በሆነው መንሃተን ውስጥ ከማንም በላይ ደልቀቅ ብሎ የሚኖር ሰው ነበር ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከምኒልክ ቀጥሎ ብዙ ነገር የጀመረው እሱ ነው ብላ ብላ ብላ….. ምናምን ታቃለህ አሜሪካ  ጎልፍ መጫወቻ ያላው መኖርያ ቤት ውስጥ ነበር ሚኖረው ፣
እርግጥ ነው እንዲህ ከባድ ሲቪ ያለውን ሰው አለማክበር አለማድነቅ አይቻልም:: ጀግና ነዋ ፤ ታገይ ነዋ… ታድያ ጀግንነቱ ዩኒፎርም ቦላሌ ለብሶ ክላሽ አንግቶ ጦር አዝምት እንዳይመስልህ የጦር ሜዳ ጀግንነት ግዚያዊ ነው ሰውዬው ጀግንነቱ ችግርን እያሳደደ መማረክ ነው በዚህ ግዜ እንኳን ችግርን መዋጋት ይቅርና ችግርን ሸሽቶ ማምለጥ ራሱ ጀግንነት ነው ይሄ ግን እንኳን ሊሸሽ ይቅርና እየሄደ ነገር እየፈለገ ድራሹን ያጠፋዋል ፣
  ስንቱ ብር ያለው የዚህ ሃገር ሃብታም የተለመደውን እንትን አስመጥቶ መጋዘን አስቀምጦ ዋጋ እስኪጨምር ጠብቆ አስወድዶ ሲሸጥ “እሱ እኮ እሳት ነጋዴ ነው!” በሚባልበት ሃገር እንዲ ያልተለመዱ ሥራዎችና ቢዝነሶችን ላይ ደፍሮ መግባት ድፍረት ፣ አቅም እና እውቀት ይጠይቃላ ሌላውን ነገዴም ኢንስፓየር ያደርጋላ….
ግን ችግሩ ምን መሰለህ ወዳጄ እኔ በጥንጥዬ ስራም ቢሆን ስላየሁት መሬት ላይ ስላለው ሃቅ ነው የምነግርህ… የዚህ ሃገር ቢዝነስ ከቢዝነስ ህግ በተቃራኒው የሚሄድ በደላላ የሚመራ ቢዝነስ ሲስተም ነው ያለው:: የገበያው ሁኔታ ተገማች ያልሆነ የእቃዎችና የአገልግሎት ዋጋ ለምን እንደጨመረ እና እንደቀነሰ ምክንያቱን በተለመደው የኢኮኖሚክ ስሌት ልትረዳው የማትችልበት ሁኔታዎች የሚያጋጥምህ ግዜ ብዙ ነው…
ሌላው የተቋማቶቻችን ላይ የሚመሩበት ህገደንብና መመሪያዎች… ” ተገልጋዩ ይሄን ማረግ ይፈቀድለታል ወይም ይሄን ማድረግ ክልክል ነው::” ብለው በግልፅ በብላክ ኤን ዋይት አለመቀመጣቸው የሚያመጣው ክፍተት ነው::
ከተቋሙ መመሪያ ይልቅ ቦታው ላይ በየተቋማቱ ያሉት ሹመኞች/ ባለስልጣናት በሚያሳዩት ይሁንታና ክልከላ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ህጉን /መመሪያውን ተከትሎ መብትን መጠየቅና ጉዳይህን ማስፈፀም ከባድ ስለሚሆን ነው::
በዚም ምክንያት እዚህ ሃገር ቢዝነስ ለመስራት ስታስብ ውሳኔዎች በሹመኞቹ ይሁንታና ክልከላ እንጂ በተቋሙ ህገደንብ/ መመሪያ መሰረት ብቻ ሊፈቀድልህና ልትከለከል እንደምትችል በመገመት አለብህ:: ስለዚህ እዚህ ሃገር ቢዝነስ ለመስራት ስታስብ ግትርነትህን ትተህ…. ከደንብ አስከባሪ ጀምሮ እስከ ላይ ካሉ ባለስልጣናቱ ጋር ጎንበስ ቀና ብለህ… መሞዳሞድ ማሽርገድ ጉቦ መስጠት መንግስትን የመደገፍ ግዴታ መወጣት ይኖርብሃል:: ጅብ እንደሃገሩ ይጮሃል ወይም “when you’re in Rome, do as the Romans do” ይባል የለ…
መሆን ያለበት የቢዝነስ ሰው ከሁኔታዎች ጋር እራሱን እያመቻመቸ ግዜውን መስሎ መንቀሳቀስ ስልት መቀየስ ቢኖርበትም ፤ አንዳንድ ግዜ ግን ሰው ነህ እና ከምታምንበት ነገር ውጭ ሲሆን ህሊናህ ላይቀበለውና ግትር ሆነህ ቢዝነስህን ስንት የደክምክለት እንጀራህን ሪስክ ላይ ልትጥለው ትችላለህ:: የኤርሚያስ ጉዳይ ውስጥ ይሄ ነገር ትልቅ ቦታ እንዳለው ይሰማኛል። ምክንያቱም እሱ የመጣበት የኖረበት የቢዝነስ አካሄድ በ ደላሎች የሚመራ ሳይሆን በኢኮኖሚ ባለሞያዎች ፎርካስት እየተደረገ በሚሄድ ሲስተም ውስጥ በማለፉ ጉዳዮችህን የምታስፈፅመው በባለስልጣናት ይሁንታና ክልከላ ሳይሆን የተቋማቱን ህግና ደንብ በሚፈቅድልህ መሰረት እሱን በመከተል የሚፈፀም ስለሆነ ነው…  እዚህ ሃገር ያለው ግን በተቃራኒው በባህላዊ የንግድ ስርአትና ከባለስልጣናት ጋር በመሞዳሞድ በመሃይም ደላላች ጉዳዮቹን ማስፈፀም በመሆኑ ሰውየው ይህንን ለመረዳት ከብዶታል ወይም ለመረዳት ባለመፈለግ የመጣ የግትርነት ችግር ሊሆን ይችላል::
ለዚህም ነው ከባለስልጣናት ፣ ከሚዲያ ፣ ከተወዳዳሪዎች ጋር እሱ በሚያምንበት ነገር ግን እዚ ሃገር ሊያስኬድ በማይችል እሰጣገባ ውስጥ እየገባ ከማይችላቸው ባላጋራዎች ጋር መላተሙ ብዙ ዋጋ ያስከፈለው::
እርግጥ ነው ላመኑበት ነገር መቆም ፣ መታገል ፣ ጫፍ መድረስና ሪስክ ወስዶ የሚመጣም ነገር ካለ ለመቀበል መዘጋጀት ትልቅነት ነው:: ጉዳዩ ይህንን ሁሉ የማደርገው ወይም ሪስክ የምወስደው በምን ኮስት ነው ነው? ጥያቄው…
እንደው ለትዝብትም ይሆን ዘንድ
ከሀይላንድ ወሀ ጀምሮ እስከ አክሰስ ሪልእስቴት ብታስቡ የጀመራቸው ስራዎች ሁሉም ያሉበት ደረጃ የትዬለሌ ነው ፣
በሀገራችን በባንክ ታሪክ ዘመን ባንክን እሚያህል ዘመናዊ ባንክ የለም ለራሱ አልፎ ተኝተው ሲቃዡ የነበሩ ባንኮችን ተረክ ነው ያረጋቸው ፣
አክሰስ ሪልእስቴት ብታስቡት አሁን ላይ ከህዝቡ የተሰበሰበው ገንዘብ በካሽ ተቀምጦ ቢሆን ኖሮ እንኳን ቤት ለመግዛት ለአመት ክራይም  አይበቃ ኤርሚያስ አክሰስ ሪል እስቴትን ከህዝብ ብር ሲሰበስብ አንድ ቪትስ ሶስት መቶ ሺ ነበር አሁን ስምንት መቶ ሺ እና ሚሊየን ነው ፣
ያኔ ትዝ ይለኛል ኤርሚያስ ደጋግሞ ሲናገር የነበረው ገንዘቡ መሬት ላይ ነው ምንም የጠፋ ነገር የለም ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለውም ገንዘብ በተለይ ያኢትዮጲያ ካልቃምክበት እና ካሹን ካላስቀመጥከው ዝም ብሎ ያድጋል ማለቱ ነው በቃ ገንዘቡን ንብረት ላይ ካለ እያየኸው ይጨምራል  ሲል ነበር አሁን ላይ ሲታሰብ ልዩነቱ የትናየት ነው ።
ሰሞኑን ሴፉ ላይ ደሞ ምን አለ
በቀን አንዴ እበላለው በትንፋሹ እስፖርት እየሰራ ከሚቅሙት በላይ ትክክለኛ ንቃት ነቅቶ ስምንት ሰአት ተኝቶ እምሞትበትን ግዜ ማራቅ ነው የምፈልገው አላለም ፣
ብቻ በጠቅላላ አቶ ኤርሚያስን ኢትዮጵያ ነበረች ፈልጋ ማምጣት የነበረባት ግን የሱ ችግር ወዳጅነት ኢትዮጵያ ከጃይነት  እሱ ኢትዮጵያን ፈልጎ መጣ ባይሆን ተንከባክባ አሞላቃ መጠቀም ነበረባት ግን እሱ ባይሆን ማክበር አነበረባትም ? እንኳን ኤርሚያስን ይቅርና ማንም ባለስልጣን ሁለት ግራ እግር ለዛውም ፈረንጅ ሀገር ቤት ሊገዛ ሚጋጋጥን ታሞላቅ የለ ??
ወንድም ጅራ ይዘፍናል:-
” ይቀመጣል እንዳደራ ሰው ክፋም ሰራ ደግም ሰራ ሁሉም የጁን ያገኘዋል ይቆይ እንጂ መች ይቀራል “
ኢትዮጵያ ራሱ አፍ አውጥታ ምትናገርበት ግዜ ይመጣል ።
ቸር  እንሰንብት
Filed in: Amharic