>

"ሁሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል....!!!"  የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት‼

ሁሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል….!!!
 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት‼

ሁሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ።
የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ልክ እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ ለአገራቸው በአንድነት ዱዓ (ጸሎት) ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች እና ሰውነት ይቀድማል በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር በደሴ ከተማ በአገራዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እያካሄዱ ነው።
በምክክሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ኡለሞች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እንዳሉት አንድነት እና ሰላምን በጋራ ማስጠበቅ ይገባል። ወሎ የእምነት አባቶች እና የኡለሞች መፍለቂያ መኾኗን ያወሱት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ በተለይ በዚህ ወቅት መደጋገፍ እና መተባበር ያስፈልጋል ብለዋል።
❝ሁሉም የየራሱን አመለካከት ይዞ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አገራዊ አንድነት ሊሠራ ይገባል❞ ነው ያሉት።
የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዬች ለዘመናት አብረው በአንድነት እና በመተባበር የኖሩ መኾኑን ያወሱት የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች የኹሉም ሃይማኖት ተከታዬች ለአገራቸው ዱዓ (ጸሎት) እንዲያደረጉ ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት የዳዓዋ እና የፈተዋ ዘርፍ ኃላፊ ሽህ አህመድ አወል በምክክሩ ወቅት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች ከአራት ሚሊዬን ብር በላይ የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
Filed in: Amharic