>

ያሳዘነኝ ነገር...!!! (ሰለሞን አላምኔ)

ያሳዘነኝ ነገር…!!!

ሰለሞን አላምኔ

……ከ2 አመት በፊት እስክንድር ነጋ ፊት ወጥቶ የሽግግር መንግስት ያስፈልጋል! አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ሁኔታ «ተረኝነት እንጅ ለውጥ የለም!» ሲል የተሰላቀው ሰው ብዛቱ ሽ ነው።…. አብዛኛው ሰው ይህን ሃቅ አሁን ላይ ትክክል ነበር ብለው ቢረዱም አንድ አንዶች ከእስክንድር ጋ ብቻ ሳይሆን ከራስ-ህሊናቸው ጋር የእለት ተእለት ጠብ ላይ ናቸው። መቼ ነው ታዲያ እስክንድር ልክ ነበር! ያለው ሁሉ ሆኗል! አብረነው ልንቆም ይገባል ልንለው የምንችለው ︎!? ራሳችንን እንፈትሽ!
….. ከ2 አመት በፊት እስክንድር ነጋ ዶክመንት ሰብስቦ «በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊፈፀም ነው!» በተለይም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል! እያለ ሲናገር እንደ እብድ ተቆጠረ! ምን ይላል ይሄ ሰው ተባል! ተዘመተበት! ያለው ነገር አልቀረም። ሁሉም ሆነ። የተሳለቁበት ሰዎች የት እንዳሉ ባይታወቅም አብዛኛው ህብረተሰብ እስክንድርን ተረድቶታል።
አሁንስ? አሁንም እስክንድር የአለም አቀፉን ማህበረሰብ በር እያንኳኳ ሳይታሰር በፊት የተናገረውን ዶሴ እያገላበጠ ተፈፅሟል እርምጃ ውሰዱ እያለ አሁንም የዘረ ማጥፋቱ እንዲቆምና የዘረ ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላትን በጦር ወንጀል እንዲከሰሱ እየጠየቀ ይገኛል! እኛስ ምን ላይ ነን?
 [ ስንቶቻችን እስክንድር ከተፈታ በኃላ የሚያደርገውን ነገር እንከታተላልን? ስንስቅ የነበረን ሰዎች አሁን ምን እያልን ነው? ዛሬም እስክንድርን ጠልፎ ለመጣል ሴራ ውስጥ ነን? ]
…..ከ2 አመት በፊት እስክንድር ነጋ ሳይታሰር «ሁሉን አቀፍ የሽግግር በባለሙያዎች የሚመራ መንግስት እና የሽግግር ጊዜ ፍትሕ ይቋቋም እና ሀገሪቱን ካልችበት ውጥንቅጥ በጋራ እናውጣት፣ ባልደራስ አቋሙ ይህ ነው » ሲል በኢትዮጵያ ውስጥ በቂ መሪ እና አሻጋሪ መንግስት አለ! የሽግግር መንግስት ምናምን የሚባል ነገር አይሰራም! ከእኛ በላይ ኢትዮጵያን የሚወዱ መሪዎች ናቸው ስልጣን ላይ ያሉት! እንዴውም እናግዛቸው የሚል ክርክር ነበር የሚንፀባረቀው!
 #አሁን ላይ ሆነን ስናስበው ማን ነበር ልክ? ኢትዮጵያስ ምን ላይ ነች? ማንን እንመን ከሁለቱ? ምርጫው የራሳችን ነው!
…. አንድ ጠንካራ ኢትዮጵያን ከነ ሙሉ ታሪኳ ሊወክል የሚችል ጠንካራ ኢትዮጵያንስት የፖለቲካ ፓርቲ ላለፉት 40 አመታት [ ኢትዮጵያኒስት ፓርቲ ቢኖሩም ውጤት ሊያመጡ ስላልቻሉ ] አሸናፊ ሆኖ ሊውጣ ስላልቻለ ቢያንስ እንደ ሀገር ካሉት ተፈትሾ ለህዝብ ቆሞ ያስመሰከረውን ባልደራስ በመሪነት ደረጃ እስክንድርን ተከትለን ስንቶቻችን ከራስ ኢጎ ወጥተን ይህንን የታሪክ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ ነን?
ቢያንስ ቢያንስ ስህተት እንኳን ቢኖር መጥቶ በጋራ ተነጋግሮ ለአንድ አላማ መቆም ያቅተናል? ዛሬም በ60ዎች የሴራ ፖለቲካ ከበርቴዎች የኔን ዘመን ወጣት በስመ ታጋይነት ብቻ ካባ ደርበው የራስ-ሂሊናቸውን እንዳይከትሉ ራሳቸውን በዲናር በሸጡ ምሁር እና መሪ ነን ባዬች አሳስተው አዛው አዙሪት ውስጥ ነን!! ልንነቃ ይገባል። ወደ ራስ እንመልከት!!
❝ ያሳዘነኝ ዛሬም እስክንድርን የሚተቹ ሰዎች አንድም ማሰረጃ ሳያቀርቡ ለምን ያልሰራነውን ስራ ሰርቶ አሳፈረን እና መንግስታች ሊከስ ተነሳ በሚል መሆኑ ነው። ❞
እስክንድር እና ባልደራስ 
በእኔ እይታ ያለችን ጠባብ መንገድ ናት ያችን ጠባብ መንገድ ልንጠቀምባት ይገባል። ይገባል ብቻ ሳይሆን የታሪክ አጋጣም የውዴታ ግዴታ ናት። በአንድ እንቁም! በቅርቡ አዲስ ነገር ይዘን እንደምንመጣ ሙሉ ተስፋ አለኝ። ሁላችንም ልንተጋገዝ ይገባል። ራሳችንን እንሁን ስህተቶችን በቀላሉ እያየን ከማለፍ ስህተት የሰራውን ሰው ነቅሰን በአንፃራዊነት ትክክለኛውን ሰው እንከተል። በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ «በእኛ ድክመት እንጅ በተረኞች ጥንካሬ አይደለም! » እስከዛ እኛ ምን ያህል ራሳችንን አርመናል! መንገዳችንን እንምረጥ
Filed in: Amharic