ሳይበር ሲቲዝን
በርካቶች በኢትዮጵያ የትዝታ ሙዚቃ ስልት ንጉስ ሲሉ የሚስማሙበት አንጋፋው ድምጻዊ መሃሙድ አህመድ ከተደረገለት የልብ ቀዶ ህክምና በኋላ ሙሉ በሙሉ በማገገሙ ዛሬ ወደ መኖርያ ቤቱ መግባቱን ታውቋል። ድምጻዊ መሃሙድ አህመድ ባለፈው ቅዳሜ ከገጠመው የኮሮና ወረርሽኝ በኋላ በደርሰበት የልብ ውስጥ ደም መርጋት በሽታ ወደ ሆስፒታል ገብቶ አጣዳፊ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለታል።
ደምጻዊ መሃሙድ አህመድ አዲስ አበባ ወስጥ በሚገኘው የልብ ህክምና መስጫ ማዕከል በዶክተር በቀለ አማካይነት የቀዶ ህክምና ከደረገለት በኋላ በልዩ ህክምና ክትትል መስጫ ውስጥ ክብካቤ አግኝቷል ። የድምጻዊው ቤተሰቦች ዛሬ ለዘሃበሻ ይፋ እንዳረጉት ጋሽ መሃሙድ ዛሬ ከህመሙ አገግሞ ወደ መኖርያ ቤቱ ገብቷል። የ 82 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ የትዝታ ሙዚቃ ቅኝት ንጉስ ከ 60 ዓመታት በላይ በአማርኛና በጉራጚኛ ሙዚቃዎች ተወዳጅ ሆኖ የዘለቀ ሲሆን በሙያውም ከህገር ወስጥና ከዓለም አቀፍ ተቋማት በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል።
አርቲስት መሃሙድ አህመድ በገጠመው ህመም በአፋጣኝ እንዲያገግም አድናቂዎቹና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለተደረገለት ፀሎትና የመልካም ምኞት ምስጋና ማስተላለፉን ዘገባው አመልክቷል።