>

የጄኔራሉ እምቢታ እና የክፉቀን ደራሾችን የማባረሩ ብአዴናዊው ተግባር (ወንድወሰን ተክሉ )

የጄኔራሉ እምቢታ እና የክፉቀን ደራሾችን የማባረሩ ብአዴናዊው ተግባር
ወንድወሰን ተክሉ 

ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ የተመደቡበትን ስልጣን/የስራ ዘርፍ እንደማይቀበሉ አስታወቁ!!


“ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ወያኔ በአማራ ላይ ወረራ በከፍተችበት ወቅት ከተሾሙበት የአማራ ክልል ልዪ ኋይል አዛዥነት ተነስተው በተሾሙበት  ወይም በተመደቡበት አዲስ የስራን ተቀብለው እንደማይሰሩ ማስታወቃቸውን ማወቅ ተችላል።
 ጄኔራሉ ከልዩ ሃይሉ  ዋና አዛዠነት እንዲነሱ የተደረገበት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በአማራ ላይ የተከፈተ ጦርነት የሌለ ነው የሚለውን መንግስታዊ አቌምን ባልተቀበለ መልኩ ጄኔራሉ ግን የአማራ ህዝብ ተደራጅቶ ራሱን መጠበቅ አለበት ወጣቶች ሰልጥነው ፋኖ መሆን አለባቸው አለበለዚያ የአማራ ልዩሀይልን መቀላቀል አለባቸው  በማለተቻዉ ነው ተብሎ ይነገራል።
በአማራ ህዝብ ረጅም ታሪክ ውስጥ ለአማራ ህዝብ መከራና ሰቆቃ ከገባቸው በጣት ከሚቆጠሩ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ጀኔራል ተፈራ ማሞ አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን  የአማራን  ልዩ ኃይል ሰራዊት ካደራጁት ጀግኖች መካከል ጀነራል አሳምነው ጽጌና ጄኔራል ተፌራ ማሞ  በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ  ናቸዉ   ።
የአማራን ህዝብ ህይወቱን ሁሉ ገብሮ ማገልገል ፍላጎት ያለው ለአማራ ህዝብ ተወልዶ ለአማራ ህዝብ ለመሞት ቃል የገባው ፤  ሸማቂው ኮማንዶ ተፈራ ማሞ  ስራን በነጻነት እንዳይሰራ ፣ የሚፈልገውን እና የሚያግዘውን አካል ወደ ፊት እንዳያመጣ ፣ የሚያቀርበውን እቅድ እና የሰው ሀይል ውድቅ ሲያደርጉበት እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል ።”
ይህ ሆኖ ሳለ በአቢይ መራሹ ብአዴን አመራር ጄኔራሉን ለምን ከልዩ ኋይሉ ዋና አዛዥነት አንስተው  የሰላምና ደህንነት አማካሪ ለማድረግ ለምን እንደፈለጉ የገለጹት ይፋዊ ምክንያት አልታወቀም። ሆኖም የብአዴንን ውስጠ ሕገ ደንብ እና አሰራርን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች እና የኦህዴድ መራሹን የብልጽግናን መንግስት በአማራ ላይ ያለውን ፖሊሲ የሚያውቁ የቅርብ ምንጮች ጄኔራሉን የማዛወር ውሳኔ ከአራት ኪሎ የተወሰነ ነው በማለት ይገልጹና መምስኤውንም ስርዓቱ በአማራ ላይ የወጠነውን አላማን ለመፈጸም ካለመ እቅድ የመነጨ ነው ሲሉ ይናገራሉ።
ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ከዚህ በፊትም ከሙያቸው ውጪ በሆነ ስፍራ ተመድበው አልቀበልም በማለት ተቀምጠው የነበሩ ሲሆን የወያኔን በአማራ ላይ የከፈተውን ወረራን ተከትሎ ከሕዝብ በኩል የጎረፈውን ተጽእኖ አድራጊን – ማለትም ተፈራን መልሱትን ጥያቄን ተከትሎ የአማራ ክልላዊ መንግስት በጭንቅ እለት ልዩ ኋይሉን እንዲመሩ የተሾሙ ናቸው።
ሆኖም የጃንደረባው ብአዴን ጸረ አማራነት ፖሊስ እያደር በማገርሸት ስርዓቱ ለስልጣኔ የሚያሰጋኝ ሃይል የለም ብሎ በሚያስብበት ሰዓት እንደነ ብ/ጄ  ተፈራ ማሞና ፋኖዎችን የክፉ ቀን ደራሽ ጀግኖች ላይ በመዝመት እያደነ የመብላትን ዘመቻ የሚከፍት ጸረ አማራዊ ሃይል በመሆኑ ዛሬም ጄኔራሉን ከሃላፊነታቸው አንስቶ ለማዘዋወር መወጠኑን ነው መረዳት የምንችለው።
የጄኔራል ተፈራ ማሞን አዲሱን የስራ ሃላፊነትን አልቀበልም ብሎ እምቢ ማለትን ተከትሎ ጃንደረባው ብአዴን ያስተላለፈው ውሳኔ ገና አልታወቀም።
Filed in: Amharic