>

አዲስ አበባን እና ህዝቧን የዘለፉ ሹመኞች አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ለባልደራስ ምላሽ ሰጠ ...!!! (ሰለሞን አላምኔ)

አዲስ አበባን እና ህዝቧን የዘለፉ ሹመኞች አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ለባልደራስ ምላሽ ሰጠ …!!!
ሰለሞን አላምኔ

 የአዲስ አበባ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘላለም ሙላት፣  የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በሰጡት ዘለፋ አዘል አስተያየት፣ ” በፊንፊኔ ዙሪያ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ አካባቢዎች አዲስ አበባ ከርሷን ሞልታ ፈርሷን የምትጥልባቸው አካባቢዎች ናቸው ” ማለታቸው በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን በፕሬዚዳንቱ የሚመራው የባልደራስ ጽ/ቤት መግለጹ የሚታወቅ ነው።
በተመሳሳይ ከዚህ በፊት አሁን ገዢውን ፓርቲ ወክለው የተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ሀንጋሳ አህመድ የአዲስ አበባ ተወላጆችን ሰብዕና የሚያንቋሽሽ ዘለፋ መሰንዘራቸው ይታወሳል።
እነኚህን  ሹመኞቹን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እና ከኃላፊነት ለማስነሳት ፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት አስመልክቶ ፤ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ  ላቀረበው ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ምላሽ ሰጥቷል ።
ከምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ምላሽ አስመልክቶ ባልደራስ አፅንኦት በመስጠት እየተከታተለው ሲሆን ፤በቀጣይ በጉዳዩ ዙሪያ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይፋዊ ምላሽ ይሰጣል።
ለዚህም መላው የአዲስ አበባ ነዋሪ  ባልደራስ ለሚያከናውናቸው ሕጋዊ ተግባራት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ከወዲሁ ጥሪ እናቀርባለን ።
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!
Filed in: Amharic