>

ባልደራስ  ለምርጫ ቦርድ በድጋሚ ጥያቄ አቀረበ....!!! 

ባልደራስ  ለምርጫ ቦርድ በድጋሚ ጥያቄ አቀረበ….!!! 

ሰለሞን አላምኔ

“…. ሕዝብን በአደባባይ የዘለፉት አቶ ዘላለም ሙላቱን ለማስነሳት የሚያስችል እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ ቅፅ እንዲሰጠው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በድጋሜ ጠይቋል!!!
   ሕዝብን በአደባባይ የዘለፉት አቶ ዘላለም ሙላቱ ከአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነታቸው እንዲነሱ የሚያስችል እንቅስቃሴን ለማስጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ድጋፍ እንዲያደርግለት ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በድጋሜ ጠይቋል።
    ፓርቲው ከዚህ ቀደም ላቀረበው ይኸው ጥያቄ፣ በምርጫ ክልሉ ኗሪ የሆነው መራጭ ሕዝብ ጥያቄውን ሲያቀርብ ቦርዱ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተገልጾለታል። ይህ ምላሽ ከደረሰው በኋላ ቦርዱ ጥያቄውን በአግባቡ እንዳልተረዳው የገለፀው ባልደራስ፣ በድጋሜ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ልኳል።  በአዲሱ ደብዳቤ ውስጥ የሚከተሉት ጉዳዮች ግልፅ እንዲሆኑ አብራርቷል፦
፩. ጥያቄው የተነሳው በምርጫ ክልሉ ኗሪ ከሆነው ህዝብ መሆኑን፣
፪. የተፈለገው፣ ፊርማ የሚሰባሰብበት ቅጽ ላይ ቦርዱ ያስፈልጋል የሚላቸው መረጃዎች (ለምሳሌ፣ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ) ዝርዝር ብቻ መሆኑን፤ ይህንንም ህጋዊ ተቀባይነት የሚኖረው ቅጽ አዘጋጅቶ ቦርዱ ለባልደራስ ብቻ ሳይሆን፣ በቀጣይነት ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚያቀርቡ ሊሰጥ የሚችል መሆኑን፣ ይህም ህዝቡ መብቱን ለማስከበር እንደሚረዳው
፫. አሁን ባለው ሁኔታ፣ ቦርዱ አስቀድሞ ባላዘጋጀው ቅጽ ላይ ፊርማ ተሰባስቦ ካለቀ በኋላ “ያላሟላው ነገር አለ” ተብሎ ውድቅ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ያለ በመሆኑ፣ ቦርዱ በዚህ ረገድ ህጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟላ ቅጽ በማዘጋጀት ሊተባበረን ይገባል ብሏል።
አቶ ዘላለም ሙላቱ የተባሉ የገዥው ፓርቲ ወኪል፤ የአዲስ አበባ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል በምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ የአዲስ አበባን ሕዝብ ‘ፈርሳምና ከርሳም’ በማለት በፀያፍ ንግግር መግለፃቸው ይታወሳል።
Filed in: Amharic