>

የቡዳ መድኃኒቱ ነፍጠኛው ፑቲን !!  (ዘመድኩን በቀለ)

የቡዳ መድኃኒቱ ነፍጠኛው ፑቲን !! 

ዘመድኩን በቀለ

• በሴረኞች የፈረሱ የፈራረሱ ሃገራትን እንደ ፑቲን ያለ “አንድ አድርጋቸው!” የሆነ ነፍጠኛ መሪ ይስጣቸው አሜን!! 
…. እኔም የኢትዮጵያዬን ፑቲን እየጠበቅኩት ነው። የሆነ ቀን፣ ከሆነ ስፍራ ድንገት ይመጣል። እየጠበቅኩት ነው
“…በዩክሬን የሚኖረው አብዛኛው ዜጋ ሩሲያኛ ተናጋሪና በደምም ሩሲያዊ የሆነ ነው። ምዕራባውያኑ ታላቋን የሶቬየት ኅብረትን አፈራርሰው ብዙ ክፍለ ሀገሮቿንም እንደ ሃገር ጠፍጥፈው ፈጥረው እውቅናም ሰጥተው ከአባት ሃገር ሩሲያ ገንጥለው የፈጠሩ ክፉዎች ናቸው። ዩክሬን የሩሲያ አካል ራሷ ሩሲያም ነበረች። ኤርትራን ባሰብኩ ጊዜ ሩሲያ ዩክሬንን አስታውሳለሁ። ክፉዎቹ ከእናት ሃገሯ ከኢትዮጵያ ገንጥለው ኤርትራን አዲስ ደሃ ሃገር አድርገው በመፍጠር፣ ልጆቿን ለሁለት ከፍለው ስደተኛ፣ ተንከራታች፣ የዓሣ አንበሪ ቀለብ እንዲሆኑ ፈርደው ኢትዮጵያንም ከውኃው ዳር በግፍ አርቀው እንዳስቀሯት ማለት ነው። እነሱ እንደ ሃገር ሳይፈጠሩ እኛ ግን በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት በ5 መቶኛው ክፍለ ዘመን መርከብ ሠርተን፣ ባህር ኃይል መስርተን ቀይ ባህርን ተሻግረን የመን ድረስ ተጉዘን በሃገረ ናግራን መዝመታችን ይታወቃል። እኛ የሰላም አስከባሪነትን የጀመርነው ጩጬው የተባበሩት መንግሥታት ገና ሳይታሰብ ሳይፈጠርም ነበር።
“…በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሶቬየት ኅብረት አስር ትናንሽ ሆና ስትፈራርስ የዛሬው የሩሲያ ፕሬዘዳንት የሆነው ነፍጠኛው ፑቲን የአባት ሃገር የሩሲያ የስለላ ድርጅት የኬጂቢ የሰላዮች አዛዥ አለቃ ሆኖ በያኔዋ ምሥራቅ ጀርመን በዛሬዋ ሙሉ ጀርመን በርሊን ከተማ ነበር። ጀርመን ምዕራብና ምሥራቅ የሚለውን የሁለት ሃገርነት ግንብ አፍርሳ ታላቋ ጀርመን አንድ ጀርመን ስትሆን እኛ ግን ታላቋን የምታምረዋን ኢትዮጵያ አፍርሰን ኢትዮኤርትራ ተብለን ለሁለት እንድንገመስ አደረጉን። ጀርመኖች አንድ ሃገር የሆኑበትን ቀን ሲያከብሩ እኛ ሁለት ሃገር የሆንበትን ቀን እናከብራለን። እነሱ በአንድነት ጠንካራ፣ ገናና፣ ኃያል እንደሚሆኑ ሲያምኑ፣ እኛን አስር ትንንሽ አድርገው ለማኝ የእኔቢጤ ደካማ ያደርጉናል።
“…ፑቲን ሩሲያ ስትፈራርስ ጀርመን ሆኖ ምርር ስቅስቅም ብሎ አልቅሷል። በሃገሩ መፈራረስ ተቆጭቷል፣ ተንገብግቧል። የታላቋ ራሺያ መድከም፣ መጎሳቆል፣ መፈራረስ፣ መቦጫጨቅ፣ የምዕራባውያኑ ሴራ መፈንጫ፣ ማላገጫ፣ ከወደቁስ አይቀር እንደሩሲያ ስብርብር፣ ብትን ብትንትን ማለት ነው ብለው የፈራሽ ሃገሮቸረ ምሳሌ መሆኗም አንገብግቦታል። የሩሲያን ውርደት በዓይን በብረቱ ቆሞም አይቷል። ማነው እነ መለስ ዜናዊ ግብፃዊውን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊን ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ ደጅ ጠንቶ ድንጋይ ተሸክሞ ገንጥሉልኝ ብሎ ሲያስገነጥል እንደ ፑቲን ያለቀሰ? ኤርትራና ኢትዮጵያ በምዕራብያውያኑ ሴራ ሲገነጣጥሉን ምርር ብሎ ያነባ? የተቆጨ? ማነው አንድ ሃገር ሁለት ቦታ ሲገመስ የተከዘ፣ የበሰጨው? ማነው? ማነው? ማነው ወደፊት “ታሪክን አርሞ አንዲት ጠንካራ ሃገርን የሚፈጥረው? የሆነ ያሰበ ሰው ካለ ቀስቀስ ብቻ ይበል። ሃይማኖትና ልብ ካለህ ታሸንፋለህ። ይሳካልህማል። ግፋ ቢል 30 ዓመት ቢፈጅብህ ነው። እኛ ባንደርስበት ልጆቻችን ይደርሱበታል።
“…ፑቲን ወደ ሃገሩ ተመለሰ። ዕድል አግኝቶ፣ በለስም ቀንቶት፣ መጀመሪያ ከንቲባ፣ ቀጥሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መጣ። ዛሬ እንዲህ እግር ከወርች አስሮ ዓለሙን ሰቅዞ ይይዛል ብሎ የገመተ ልብም ያለው፣ የጠረጠረውም ማንም አልነበረም። ፑቲን ስፖርተኛ ነው። ሲጀመር ሰላይም መሆኑ ጠቅሞታል። ሰላይ መሆኑም ከግለሰብ እስከ ሃገር መሪዎች ደካማና ጠንካራ ጎኖቸውን ለማወቅ ረድቶታል። ወደ ዋናው አጀንዳው ምልሰተ ታላቋ ሩሲያ ከማምራቱ በፊት ቀስ በቀስ ጽዳቱን ከቤቱ ነው የጀመረው። ሩሲያዊ ሆነው በሩሲያ አሴት የሚንበዛበዙ ራስ ወዳድ ስግብግብ ባለሃብቶችን አደብ አስያዘ። በፕራይቬታይዜሽን ስም ቀደምት የሩሲያ አባቶች የቋቋሟቸውን ድርጅቶች በዶላር ገዝተው የሩሲያን ሃብት የተቆጣጠሩትን በሙሉ አጸዳቸው። የሩሲያውያንን ሃብት ለሩሲያውያን አስረከበ። የሩሲያ አባቶች ደክመው ያፈሩትን ሃብት በነፃ ገበያ ስም እነ አጅሬ ተቀራምተው ሩሲያውያን በገዛ ዳቦአቸው ልብልቡን አጥተው የድህነት በርኖስ ለብሰው የነበሩትን በሙሉ አይናቸውን ገለጠላቸው። ቀና ማለትም ጀመሩ። አጼ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ደርግም ቢሆን አስከብረው ያቆዩትን ሂዊ በራሷ ሰዎች፣ ዐቢይ ደግሞ ለወጭ ሃገር ሰዎች እየሸጡ እንዳሉት ማለት ነው። በኢንቨስተር ስም የሃገር ሃብት ላይ ከተጣበቁ መዥገሮች አላቀቀ።
“…ከአንድ ሰፈር፣ ከአንድ መንደር፣ በአንድ ትምህርት ቤት አልፈው በእልህ፣ ደግሞም በከፍተኛ ምስጢር የሩሲያን ታላቅነት ለመመለስ ከልጅነት ጀምረው አብረው የነበሩት የሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክም በብዙ ረዱት። አገዙትም። ሩሲያውያን ከልማቱ ጎን ለጎን የቀደመ ክርስትናቸውን እንዲያጠብቁ፣ ከእግዚአብሔርም ጋር እንዲጣበቁ በሰፊው ተንቀሳቀሱ። ኮሚኒስቶቹ እነ ሌኒን ብለው ብለው ያላጠፉት ኦርቶዶክስነትም አበበ። ተሳካላቸውም። እግዚአብሔርን የያዘ እንደሚያሸንፍም በህዝቡ አዕምሮ ውስጥ አሰረጹ። ነውር፣ የዓለም ኃጢአትም፣ ቀላጭነትም በሩሲያ ቦታ አጣ። ምዕራባውያን ቅድስናን የሚያረክስ ሸቀጣቸውን በሩሲያ ለማራገፍ ቢደክሙም ሩሲያውያን እምቢኝ አሉ። አንዳንድ ቅጥረኛ ጋጠወጦች በሞስኮ ዊኒጥ ዊኒጥ ቢሉም በቶሎ ቀሰፏቸው። አደብም አስገዟቸው።
“…ቀጥሎ በጸሎትም በነፍጥም ሃገሩን ከፍ ለማድረግ ታተረ። ከሁሉ አስቀድሞ መከላከያውን ሩሲያዊ አደረገው። አባት ሃገር ሩሲያን፣ ታላቋን ሩሲያ ክብሯን ለመመለስ ቀን ከሌት ለፋ። የተበታተነችዋን ሩሲያን አንድ ለማድረግ በብርቱ ጣረ። መከላከያ ሠራዊቱም ጡንቻው እንዲፈረጥም አደረገ። መጀመሪያ እዚያው ሩቅ ሳይሄድ ልክ አሁን በዓረቦቹና በምዕራባውያኑ እርዳታ ኢትዮጵያን እንደሚወጉት፣ እንደሚያደሙት ተገንጣይ ጽንፈኛ የኦሮሞ እስላሚስቶችን ዶግ አመድ አደድርጎ አፈር ከደቼም አስበልቶ አሸነፋቸው። ድራሽ አባታቸውንም አጠፋቸው። ዋጣቸውም። ጽንፈኞቹ ምዕራባውያኑን ተማምነው ቢዘሉ፣ ቢወራጩም ሩሲያ ግን በጅራፏ ቀጠለች። ተይ የሚላት የሚያስቆማትም ደፋር ከወዴት ይምጣ?
“…ኢራቅን ሽባ ያደረገው አይነት የማዕቀብ መዐት ከምዕራባውያኑ ጎረፈባቸው። ወይ ፍንክች። ይልቅ እነሱ ጠንክረው እየሠሩ ኢኮኖሚያቸውን በማሳደግ ምዕራባውያኑ ራሳቸው የሩሲያ ጥገኛ እንዲሆኑ አደረጉ። ለራበው ስንዴ በገፍ ያመርታሉ። የነዳጅና ጋዝ ዋነኛ አከፋፋይም ሆኑ። የጋዝ ፍጆታቸውን የቧንቧ መስመር ዘርግተው ዶላር ዩሮ ከፍለው፣ ለምነው ከሩሲያ ይሸምታሉ። ስንዴም ለሆዳቸው ሲሉ ከእሷ ነው የሚሸምቱት። ለኬኩም፣ ለዳቦውም ሲሉ ጥገኛዋ ሆኑ።
“… ለኢትዮጵያዬም እንዲህ ዓይነት መሪ ነው የሚያስፈልጋት። አይኑ እያየ በምዕራባውያን ሴራ የተገነጠለች ክፍለ ሃገሩን የሚያስብ፣ የሚቆጭ፣ የሚንገበገብ መሪ ነው የሚያስፈልጋት። ዘረኝነትን የሚጸየፍ፣ አማኝ፣ ከልቡ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው። ዐዋቂ እንጂ አውርቶ አደር ብጥርቅ በጥራቃ ያልሆነ መሪ ነው ሃገሬም የሚያስፈልጋት። ድራሚስት ያልሆነ። አምናለሁ እንደ ፑቲን ያለ ለአምላኩ እንጂ ለሰው የማይንበረከክ። የሃገሩ መፈራረስ እየቆጨው ቀን የሚጠብቅ፣ በመከላከያው ውስጥ፣ ደኅንነቱ ውስጥ፣ ብቻ የሆነ ቦታ ሆኖ ምቹ የሆነ ጊዜ የሚጠብቅ ሰው እንዳለ አምናለሁ። እግዚአብሔርም እንዳዘጋጀ አምናለሁ። ምንአልባትም ያ ሰው ይህን የእኔን ጦማር እያነበበም ይሆናል ብዬም አምናለሁ። ወዳጄ ተንቀሳቀስ።
“…በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት የዛሬዋ ዩክሬን ኤርትራ ልክ ኢትዮጵያውያንን በውስጧ እንደያዘች ሃገር በሆነችው ጊዜ የነበር ጠባይ ነበራት። እሷም ሩሲያ ሆና የሩሲያን ዜጎች እንደያዘች ሃገር ነሽ ተብላ ሃገር የሆነች ሃገር ናት። በዩክሬን የሚኖሩ ሩሲያኛ የሚናገሩ ዜጎች ግን ልክ አሁን ዐማራው በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ኤሊቶች እየደረሰበት ያለው ዕጣ ነበር የደረሰባቸው። ሩሲያውያን ሆነው ሃገር ሲሆኑ በዩክሬን የሩስኪ ቋንቋ ተናጋሪዎች ፍዳቸውን ማየት ጀመሩ። በቁጥር ቢበልጡም ባንክና ታንክ የያዙት ጥቂቶቹ ስለሆኑ ዋጧቸው። ናዝሬት ዐማራ ነው። አለቃው ግን ኦሮምኛ ተናጋሪ ነው። ያውም ከወለጋ መጥቶ። ልክ አሁን በኦሮሚያ ሽመልስ አብዲሳ እና ዐቢይ አሕመድ ዐማራውን እንደሚያጸዱት፣ እንደሚጨቁኑት ነበር የሚጨቁኑአቸው አሉ። ኢትዮጵያውያን ከኤርትራ ሲባረሩ እኮ በውስጥ ሱሪና የወርቅ ጥርሳቸው ሳይቀር እያስወለቁ ገፈው መስወጣታቸውንም አንረሳም። ቆይቶ መለስ ዜናዊ እነሱንም ገፍፎ አስለቀሳቸው። እነሱም ቀን ጠብቀው በዐቢይ ላይ ተንጠላጥለው ትግራይን ቀፎ አደረጓት። ይሄንንም አስታውሱ። አትርሱ። የሩስኪ ቋንቋ ተናጋሪዎቹ ኦርቶዶክሳውያንም ልክ በኦሮሚያ ፍዳቸውን እንደሚበሉት ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን ነበር ፍዳቸውን ይበሉ የነበር ይላሉ በዘርፉ ሁኔታውን የሚከታተሉት የዘርፉ የቦለጢቃ ባለሙያዎች።
“…ይኸውልህ ወዳጄ ቪላድሚር ፑቲን ማለት አባቱ በጦርነት የቆሰለ ወታደር፣ እናቱ የፋብሪካ ወዛደር፣ የቀን ሠራተኛ የነበረች እልም ያለ የደሀ ደሀ ቤተሰብ ልጅ የነበረ ሩሲያዊ ነው። ቤተሰቦቹ ስለዘር፣ ስለ ጎጥ፣ ስለ መንደር ሳይሆን ስለ አባት ሃገር ሩሲያ ታላቅነት እያስቀፀሉ ያሳደጉት በድህነትና በስቃይ ሕይወት ውስጥም ያደገ፤ ሁል ጊዜ ፊቱ ኮስታራና አስፈሪ ሰው እንደመሰለ ያደገ ሩሲያዊ ነው።
“…ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በጦርነት የደከመችው የታላቋ ሶቬየት ኅብረት ጎልማሳ ወታደር፣ ከጦር ዕዙ የእርፍት ጥቂት ቀናትን ወስዶ ከራሽያ ከተሞች አንዷ ወደሆነችው እና የትዳር አጋሩ የሆነችው ማሪዮ ኢቫኖቫ ወዳለችበት ፒተርበርግ ከተማ ተጓዘ። ይህን ጊዜ በከተማው መግቢያ በር ላይ እጅግ ብዙ አስክሬን የያዙ ትላልቅ መኪናዎች ወደ ጅምላ መቃብር ስፍራ በዝግታ እያዘገሙ ሲጓዙ ተመለከተ።
“…ድንገት ከሬሳዎቹ መሐል ወደ ዘመቻ ከመሄዱ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ለሚስቱ ማሪያ ኢቫኖቫ የገዛውን አይነት ጫማ ከአንዲት ሴት አስክሬን እግር ላይ ተመለከተ። “ሚስቴ ትሁን?” በሚል ስጋት እና ፍርሃት ጫማውን ወደተመለከተው አስክሬን ተጠጋ። እንደፈራውም አልቀረም። ሚስቱን ከሬሳ ክምሮች መሃል አገኘ። ይህን ጊዜ ሚስቱን በጅምላ ላለመቅበር ፍቃድ ጠይቆ ሲወስዳት አልፎ አልፎ ትክ ትክ የሚል ትንፋሽ እንዳላት አስተዋለ።
“…ሚስቱን በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም ወስዶ ያለቀ ትንፋሽ ላይ ህይወት ቀጠለ። ይህ ኩነት ከተፈጸመ ከሁለት ዓመት በኃላ በ1952 ዓ.ም ይህቺ ሴት ወንድ ልጅ ተገላገለች። ስሙንም ፑቲን አለችው። ሙሉ ስሙም ቭላድሚር ቭላድሚሮቪች ፑቲን ይባላል። አሁን የታላቋ ራሽያ ሀገረ ገዢም የሆነ። የዓለማችን ቁጥር አንድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተብሎም ስሙ በደማቅ ቀለም የተጻፈ ሰውም ሆነ።
“…አሁን ሩሲያን ከዓለማችን ዋነኛ የነዳጅ አምራች ሃገሮች ተርታ አሰልፎ፣ 70% የሚሆነው የሩስያ ሕዝብም ባለ መካከለኛ ገቢ አድርጎ፣ የሩስያ ሕዝብን የነፍስ ወከፍ ገቢም ከ28 ሺህ ዶላር በላይ አድርሶ እየመራ ያለ ቆፍጣና ነፍጠኛ መሪ ነው። አሁን የሃገሪቷ ዋና ከተማ ሞስኮ የዓለማችን ቁጥር አንድ የሆኑ ብዙ ቢልየነሮች መገኛ ሆና እንድትገኝ አድርጓታል። አሁን ሩሲያ የዓለማችን ቁጥር አንድ የኒዩክለር ክምችት ያላት ሀገር እንድትሆንም አድርጓታል። በአውሮፓም አንደኛ እና በዓለም ሁለተኛ መሆን የቻለ የሃገር መከላከያንም ገንብቷል። ፑቲን ከዛሬ 30 ዓመታት በፊት በምዕራባውያን ሰራ የፈረሰችውን የሶቭዬት ኅብረትን መልሶ የመገንባት ዕቅዱን እውን ለማድረግ ጉዞውን እያገባደደ ያለ ይመስላል ነው የሚባለው።
“…በመጨረሻም ዩክሬን እንደ ደረጄና ኃብቴ፣ እንደ ፍልፍሉ፣ እንደ ተስፋዬ ካሳ፣ እንደ ክበበው ገዳ ያለ ኮሜዲያን መርጣ ስትቀልድ መሬው ፑቲን ነፍጠኛው እጅ ላይ ጣላት። የሶሪያው ፕሬዘዳንት በሽር አላአሳድ እንዳሉት “ፑቲን ታሪክን የማረም” ሥራ ላይ ናቸውም ተብሏል። ነፍጥ፣ ከልብ እና ከሃይማኖት ጋር ሲኖርህ ታሸንፋለህ። ኮሚኒስቷ ሂዊም፣ አራጁ ሸኔም፣ ድራሚስቱ ዐቢይ አህመድም አይፈነጩብህም። አቅም ሲኖርህ ስብሃት ነጋን የመሰለ ቁጥር አንድ ቢላደን አትፈታም። ስትበረጠቅ አትኖርም። ሲልኩህ ወዴት፣ ሲጠሩህ አቤት ብለህ ተላላኪ አትሆንም።
“…እኔም የኢትዮጵያዬን ፑቲን እየጠበቅኩት ነው። የሆነ ቀን፣ ከሆነ ስፍራ ድንገት ይመጣል። እየጠበቅኩት ነው።
Filed in: Amharic