>
5:16 pm - Monday May 24, 7328

ፆም ምንድነው....??? የፆም ጥቅምስ....??? (ዲ.ን የአብስራ ግርማ)

ፆም ምንድነው….??? የፆም ጥቅምስ….???

ዲ.ን የአብስራ ግርማ

 

*…. መብላቸውን እና የሚጠጡትን ጠጅ አስቀርቶ ጥራጥሬ ሰጣቸው
/ ትንቢተ ዳንኤል 1፥13/
*…. ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ሥጋዬም ቅቤን ከማጣቱ ከሳ
 /መዝሙረ ዳዊት 109፥24/
የ2014 አብይ ፆም እሚገባው የካቲት 21/6/2014 ነው። ይህን አውቀን ምን ያህሎቻችን ቅድመ ዝግጅት አደረግን? 1 ንሰሐ ገብተናል?
2 ከተቀያየምናቸው ሰዎችስ ጋር ይቅር ተባብለናል?
3 በአብይ ፆም ውስጥ ስንቶቻችን ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር የሆነውን ደሙን ለመቀበል ልባችንን ንፁህ አድረገን ተዘጋጀን?
4 ስንቶቻችነን ከቂም ከጥላቻ ተላቀን እራሳችንን ክደን በፆም በፀሎት በስግደት ከእግዚአብሔር ጋር በመቅደሱ ለመገናኘት ብሎሞ ስለ ሀገራችን ሰላም ለመማፀን እራሳችንን አዘጋጀን ? እራሳችንን እንጠይቅ እናስብበት አዎ።

 ፆም ምንድነው??

ፆም ማለት ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከመብላትና ውሃ ከመጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት ከጥሉላት ከሥጋ ፣ ከቅቤ ፣ ከወት በአጠቃላይ ከእንስሳት ውጤት መከልከል ነው።
ይህ ብቻ ፆምን ፍፁም ሰለማያደርግ ህዋሳት ሁሉ በየራሳቸው ክፍው ነገር ከመስራት መጠበቅ አለባቸው ብሏል። ይኸውም አይን ክፍው ነገር ከማየት ጆሮ ክፍው ነገር ከመስማት ምላስ ክፍው ነገር ከመናገር ይከልከሉ ይላል። በተጨማሪም አእምሮን ተጎድተው ሰውን አስክረው የማይገባ ከሚያሰሩ እና ከሚያሳስቡ የአልኮል መጠጦችም መጠበቅ  እንዳለብን ማወቅ ይገባናል።
 የፆም ጥቅም….???
የሥጋን ምኞት እምታጠፋ የነፍስ ቁስልን የምታደርቅ ለጎልማሶች ፀጥታን እና እርጋታን የምታስተምር ከእንስሳዊ ግብር  ጠባይ የምትከለክል እና ሰው መላዕክትን መስሎ የሚኖርባት ደገኛ ስርአት ነች። በብሉይ ኪዳን ብዙዎች ፆመው ተጠቅመዋል እግዚአብሔር የፆምን ስርአት የደነገገው ገና ከጠዋቱ አዳምን በፈጠረበት ወቅት ነው። እፀ በለስን አትብላ ማለት ትዕዛዝ ቢሆንም ትዕዛዙ የፆም ትዕዛዝ መሆኑ ከማንኛችንመሰ የተሰወረ አይደለም።
በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አበው ፆምን የፀሎት እናት የእንባ ምንጭ የጽድቅ መሠረት በማለት  ደገኛውን ሥርአት ከሽነው ሲያቀርቧት  ዲያብሎሳዊ ትምህርት ያደረባቸው ደግሞ ወደ ሆድ የገባ አያረክስም ከአፍ የሚወጣ ስድብ ምንዝርነት ግን የረክሳል ነው ያለው መፀሀፍ እና ፆምን አልፆምን ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሚሰጠው ረብ የለም ሲሉ ይስተዋላሉ።
በመሠረቱ ይህን ቃል ጌታ የተናገረው ለፆም አለመሆኑን ማቴ 15፥1-20 ብቻ ማንበቡ በቂ ቢሆንም ለእነዚህ ሐሰተኞች ማስረጃ ይሆን ዘንድ
ኢያሱ እስራኤልአውያንን ወደ ተስፋይቱ ምድር በሚገቡበት ጊዜ ኢያሪኮን በቁጥጥር ስር ካደረጉ ቡሀላ ጋይ የተባለችውን ከተማ ለመያዝ በሚነሳሳበት ወቅት ከዚያ በፊት በእስራኤል ሰልፈኞች ዘንድ ያልታየ የመሸሽ የመፍራት ስሜት ተንፀባረቀ።ከሰልፈኞቹም 36 ሰዎች በጠላት ተመተው ወደቁ።እያሱም ስለ ደነገጠ በታቦተ ህጉ ፊት እስከ ሠርክ በግንባሩ ወድቆ በፆም ዋለ ። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል በደለሰ የፈፀሙ እንዳሉ ነግሮት አጥፊዎቾን ቀጥቶ ህዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቋል። መፀሐፈ ኢያሱ 7፥6-9 አሳይቷል። ይህን ካልን ሰለ ዓቢይ  ፆም እንመልከት።
 ዓቢይ ፆም
ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ የፆመው ፆም ሲሆን ለእኛም አርአያ የሆነበት ነው።ጌታ የፆመው 40 ቀን እና 40 ሌሊት ነው ዓብይ ፆም የተባለበት ምክንየት የጌታ ፆም ስለሆነ እና ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ድል የተነሱበት ነው። ዛሬም ኦርቶዶክስ አውያን የጌታን አርአያ ተከትለው ሰይጣንን ድል እሚነሱበት ነው። እኛ አሁን እምንፆመው 55 ቀናት ነው። ይህም በብዙ ዘንድ ሲተች ይሰማል። በመሠረቱም እንኳን 55 ቀን ዓመትም ብንፆም እግዚአብሔር በፀጋ ላይ ፀጋ ይጨምርንላል እንጂ አያስኮንንም ።ዳሩ ግን 15 ቀናት የተተጨመሩበት ምክንያት
1 በአብይ ፆም ውስጥ ስምንት ሳምንታት ይኖራሉ። ከእነዚህም አሥራ ስምንት እሐድ እና ሰባት ቅዳሜ ይገኛሉ።እነዚህም አስራ አምስት ቀናት ሲሆኑ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ዉሀ ስለማይጦሙ ከእነዚህ ቀናት ሲቀነሱ አርባ ቀን ይመጣል። ስለዚህ ተጨማሪ አሥራ አምስት ቀናት በዓብይ ፆም ውስጥ ቅዳሜ እና እሁድ ምትክ የሚሆኑ ናቸው።
ስለዚህ እኛም ንስሐ ገብተን ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን ሰላሙን ይላክልን።
Filed in: Amharic