>

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ለፍትህ መፅሔት ከሰጡት ቃለ መጠይቅ ዉስጥ አንኳር ነጥቦቹ...!!! (ስንታየሁ እሸቱ)


ጄኔራል ተፈራ ማሞ ለፍትህ መፅሔት ከሰጡት ቃለ መጠይቅ ዉስጥ አንኳር ነጥቦቹ…!!!
 
.ስንታየሁ እሸቱ
 

 

*… “ከኃላፊነቴ የተነሳሁት የአማራ ልዩ ኃይል እንዳይደራጅ የሚፈልጉ ጄኔራል መኮንኖች በመከላከያ ውስጥ በብዛት በመኖራቸው ነው…!!! “
ጄኔራል ተፈራ ማሞ 
 
1. መከላከያ ሰራዊት ዉስጥ ካሉ መኮነኖች መካከል የአማራ ልዩ ሃይል እንዳይጣናከር የሚፈልጉ እንዳሉ እንደዉም ቀስ በቀስ እያዳከሙ ማፍረስ እንደሚፈልጉ፡፡
.
2. መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ኋላ ያፈገፍግ የነበረዉ በሴራ ሳይሆን ለረዝም ጊዜ የተዋጋ ሃይል ስለነበርና ህወሓት እስከ ሸዋ እስኪደርስ ያለ ፈረቃ ለተከታታይ ጊዜ እንዲዋጋ በመደረጉ የተፈጠረ ክፍተት እንደሆነ፡፡ ከዚያ ባሻገር መከላከያዉ የሚያስፈልገዉን ዋጋ መክፈሉን፡፡
.
3. የአማራ ልዩ ሃይል አዲስ አበባን ከጠላት በመከላከል ፣ አባይ ግድብን ከመጠበቅ ጎን ለጎን መተከልን ሰላም የማድረግ ተግባር እና ጋሸናን በማስለቀቅ በተደረገዉ ከባድ ጦርነት ዉስጥ የአንበሳዉን ድርሻ መዉሰዱን፡፡ በዚህ ብቃቱ የተነሳም ጠቅላይ ሚንስትሩ አዲስ አበባን የሚከላከል ሁለት ብርጌድ ጠይቀዉ ተልኮ ህወሓትን አሽመድምዶ አሁን ላለበት ደረጃ እንዳበቃዉ፡፡
.
4. የአማራ ልዩ ሃይልን ለማብቃት በሚደረጉ የስልጠና እና ትጠቅ ማደራጀት ስራዎች ላይ ሁሌም ፈተናዎች አየገጠሙን ተቋቁመን ስናልፈዉ እንደነበር፡፡ ለምሳሌ ልዩ ሃይላችንን በኮማንዶ ደረጃ በብዛት የማሰልጠን ፍላጎት እንዳለን ለበላይ ብናሳዉቅም ፍቃድ ተከልክለናል፡፡
.
5. የአማራ ልዩ ሃይል ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ የጦርነት ልምድ ያካበተ ምርጥ ተዋጊ ሃይል እንደሆነ፡፡
.
6. የአማራ ህዝብና ፖለቲከኞች ከኤርትራ ጋር መልካም ግንኙነትን ማጠናከር እንደሚገባዉ፡፡
.
7. ህወሓት የትግራይ ህዝብን ከማንም በላይ ከሚቀርበዉ የአማራ ህዝብ ጋር በማጋጨት ደም እያቃባዉ እንደሆነ፡፡ እንደዚሁም ሕወሓት ከደርግ ጋር ባደረገዉ ጦርነት ስርዓት ያለዉና ለአላማ ይደረግ የነበረ ሲሆን የአሁኑ ህወሓት ግን በእብደትና በደመነፍስ የሚጓዝና የአማራን ህዝብ እበቀላለሁ ብሎ እየተጓዘ እንደሆነ ይህም ትልቁ ስህተቱ እንደነበር፡፡
.
8. የፌደራሉ መንግስት በድርድር ስም ወልቃይትና ራያን ለህወሓት እንዳያስረክብ ስጋት እንዳላቸዉ፡፡ አለያም ልዩ ሃይሉን በማዳከም የክልሉን የመከላከል አቅም አዳክሞ በወረራ እንዳይወሰድ መስጋቱን የሚገልጽ ነዉ፡፡
 
“ከኃላፊነቴ የተነሳሁት የአማራ ልዩ ኃይል እንዳይደራጅ የሚፈልጉ ጄኔራል መኮንኖች በመከላከያ ውስጥ በብዛት በመኖራቸው ነው…!!! “
ጄኔራል ተፈራ ማሞ
*….
“አስር ቦታ የጥይት ምት እያለብኝ በዛ ክረምት በዱላ ገብቼ ያዋጋሁት ለዝና ወይም ለሌላ አይደለም “አማራን እንበቀላለን!?” ብሎ ፎክሮ የመጣውን ኃይል ለመደምሰስ ነው ተሳክቶልኛል ። እነሱ የፈለጉት መሾም እንደሚችሉ እኔም ይሄንን ኃላፊነት እንደማልቀበል ነግሪያቸዋለሁኝ።
ከኃላፊነቴ የተነሳሁት ዋነኛ ምክንያት የአማራ ልዩ ኃይል እንዳይደራጅ የሚፈልጉ ጄኔራል መኮንኖች በመከላከያ ውስጥ በመኖራቸው ነው። ገና ሰናደራጅ “ይፍረስ!” ሲሉ የነበሩ አንዳንዶቹ የኛው ድርጅት የህወሀት አለቅላቂዎች አሉ እነዚህ ናቸው ልዩ-ኃይሉ እንዳይጠናከርና ክልሉ ለጠላት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርጉት።
ማሳለጫ:- ጄኔራል ተፈራ ማሞ አሸባሪዉ ህዉሃት በከፈተዉ ጦርነት በህዉሃት ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲደርስ እና እንዲደመሰስ ያደረገ ጀግና መሪ ነዉ!! በግዳጅ ጊዜም ቢሆን የአማራ ክልል ልዩ ሀይልን በመምራት አመርቂ ድል አስመዝግቦል!! ግን ለምን ከስልጣን የወረደ??? ለአማራ ክልል የሚሆን ዋሳኝ ሰዉ ከስልጣን አወረዱት!! የአማራ ክልል የመሪዎች የስልጣን ዘመን ከ1 እስከ 2 አመት ብቻ ሁኖዋል!!

http://m.youtube.com/watch?v=bNsQJxNg9IQ&feature=share

Filed in: Amharic