>

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአድዋ ድል! (ሶልያና ኤፍሬም)

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአድዋ ድል!

ሶልያና ኤፍሬም

ከታች የምታዩት ምስል በ1940 ዓ.ም የተሳለ ስዕል ነው። አሁን ላይ የሚገኘው በእንግሊዝ ሙዝየም ውስጥ ነው።  በአሜሪካ በካናዳ በጀርመን በፈረንሳይ በእንግሊዝ ወ.ዘ.ተ ያሉት የኢትዮጵያ የብራና መጻህፍት እና ነገስታት የሚጠቀሙበት ቁሳቁስ እና አልባሳት እንዲሁም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ንዋየ ቅድሳት ከኢትዮጵያ የሚወጡት በውስጣችን ባሉ ቁማርተኞች መሆኑን እንዳትዘነጉ።
አባቶቻችን ድል አድርገው ከሀገር ያስወጧቸው ጣልያኖች እና አውሮፓውያን እኛ ዘመናዊ ታንክ እና መሳሪያ ይዘን ኢትዮጵያ ያሸነፈችን በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት ነው ብለው ያምናሉ። በዚህም ምክንያት ሙዝየማቸው ውስጥ የሰቀሉት ስዕል ቅዱስ ጊዮርጊስን በአድዋ ጦርነት ላይ ያደረገውን ተራዳኢነት የሚገልጽ ነው። ሩቅ በመሄድ የአውሮፓዊያንን እምነት ለማስረዳት የተገደድኩት የእኛ አባቶች የሚነግሩንን ታሪክ እንደ ተረት ተረት ስለምንቆጥር እንጂ እውነታውን አባቶቻችን በቃልም ሆነ በጽሑፍ አስቀምጠውልን አልፈዋል ።
እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ ኢትዮጵያ ውስጥ በእምነት እኩልነት በማሳበብ በመሪዎቻችን ደረጃም ይሁን በተራው ህዝብ አድዋ ሲዘከር ቅዱስ ጊዮርጊስ ለድሉ ያደረገው ተራዳኢነት አይነሳም። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ የሆኑ የፕሮቴስታንት እና የእስልምና እምነት ተከታይ ዜጎችን ላለማስከፋት ነው። ይሁን መንግስት ዝም ያለው ለፓለቲካዊ ጥቅሙ ነው።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ተከታይ የሆነው ፣ በቅዱሳን ተራዳኢነት የምናምነው ፣ የፀጋ ስግደት የምንሰግደው ፣ 60 ሚልዮን ህዝቦች ማን አፋችንን ለጉሞን ነው ስሙን ለመጥራት የፈራነው ?
የድሉ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ልኮ ከባርነት ነፃ አወጣን! ክብር ለአምላካችን ይሁን!
Filed in: Amharic