>

"የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቁም እስር ይለቀቁ...!!!" (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

“የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቁም እስር ይለቀቁ…!!!”

 

 

 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 


*…. አቶ ዳውድ ኢብሳ በቁም እስር ላይ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ

ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ ላይ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የማጣራት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል።

በዚህም የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመጋቢት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው በቁም እስር ላይ ናቸው የሚል ጥቆማ በደረሰው መሰረት በተለያዩ መንገዶች ማጣራቱን አስታውቋል።

የቦርዱ መርማሪ አካላት በአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት በማምራት ሊቀመንበሩን ለማግኘት ባደረገው ማጣራት አቶ ዳውድ ኢብሳ በቁም እስር ላይ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በዚህም መሰረት ቦርዱ የላካቸው አጣሪዎች በአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ሲደርሱ ሲቪል የለበሱ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እንደተቀበሏቸው እና አቶ ዳውድ ኢብሳን ለማግኘት የግድ ፈቃድ እንደሚያስፈልጋቸው መታዘዛቸውንም የቦርዱ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

በመሆኑም አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመጋቢት 2013 ዓ..ም ጀምሮ በመኖሪያ ቤታቸው በቁም እስር ላይ መሆናቸውን ከራሳቸው ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ማረጋገጡን ቦርዱ አስታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳን ከቁም እስር እንዲፈታ ቦርዱ አስጠንቅቋል።

Filed in: Amharic