>
5:28 pm - Friday October 9, 5868

አልጋና ጾም...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

አልጋና ጾም…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

በጣና ደሴት፤ ክብራንቅዱስ ገብርኤል ገዳም የተመሰረተው በ1313 ዓ.ም ሲሆን የወንዶች ገዳም በመባል ይታወቃል። በገዳሙ ሙዚየም ውስጥ ካየሁዋቸው ብዙ ነገሮች አንዱ የንጉስ ተክለሀይማኖት ተደራራቢ አልጋ ነው። ከዚህ በታች የምታዩት የጠፍር ተደራራቢ አልጋ በ1864 የተሰራ ሲሆን ተደራራቢ ሆኖ የተሠራበትም ምክንያት ከጾም ወቅት ጋር ተያይዞ እንደሆነ አስጎብኛችን ገልጸውልናል። በጾም ወቅት ባለትዳሮች ጾም እንዳይገድፉ አልጋ ለይተው መተኛት ስለነበረባቸው በጾም ወቅት ንጉሱ ይህን አልጋ ይጠቀሙ ነበር። ባልና ሚስቱ ተደራራቢው አልጋ ላይ ተለያይተው በመተኛት የጾሙን ወቅት በጸሎት ያሳልፉ ነበር።
ይህ ታሪክ ነገስታቱ በዛ ዘመን ለሀይማኖታቸው ያላቸውን ቀናይነት ብቻ ሳይሆን የሚያሳየው ለሚስቶቻቸው ያላቸውንም ክብርም ያሳያል። ጾም ሲፈታም ‘ካልጋ ወድቄ ነበር’ ብሎ ከመናዘዝና ከሀጢያቴ ይፍቱኝ ከማለትም ያድናል። የተደራራቢ አልጋ ሥራ ጽንሰ ሀሳብም መነሻው ከወዴት እንደሆነ ያመላክታል። ከዚህ አልጋ አጠገብ ደግሞ በ1307 ዓ.ም የተሠራውና ከ700 አመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የንጉስ አምደ ጽዮን አልጋ ከነመጎናጸፊያው ይገኛል።
እንግዲህ የሁዳዴን ጾም የምትጾሙ ባለትዳሮች ይችን የንጉስ ተክለሀይማኖትን ተደራራቢ የጾም ወቅት አልጋ ቢያንስ ቢያንስ ብትጎበኟት ጥሩ ነው።
Filed in: Amharic