>

አንድ  ቀን!

አንድ  ቀን!

አንድ  ቀን
የቆሰሉ ሕዝቦቿ
ያነቡት  ልጆቿ
የእምነት ደጆቿ
ያለቁት ዜጎቿ

የቀሩት ተጽናንተው
ሰላምን አግኝተው
ዳግም አንሰራርተው
እያዩ ባይናቸው

የመዳን ምፅአቱን
የአምላክንም ፍርዱን
የጠፋው ሰላምን
ያን የክፋት ቀንን

ሀገራቸን ሳታልፍ
አቅማችንም ሳይረግፍ
እምነት ሳይገፈፍ
ሰላም ሳይጠለፍ

እንምባቸንን ጠርገን
መለያየት  ትተን
ባንድነት ተሳስበን
ልንተያይ አብረን

ታሪክ ተለውጦ
ምትሀቱ ተገልጦ
ሀገር አጥፊም ጠፍቶ
ኢትዮጵያነት በልጦ

ህዝብም ተሰባስቦ
ባገሩ ተውቦ
አንዱ ለአንዱ አስቦ
ባንዲራ አሸቅቦ
ሊታይ ተውለብልቦ

የምኖርበት ቀን
ይበልጥ ተቀራርበን
ጊዜያትን ለውጠን
በአብሮነት ተሳስረን
የተስፋውም ዘመን
ይሆናል አንድ ቀን!

(ተጻፈ በ -ዘምሳሌ)

Filed in: Amharic