>

የአማራ ጥያቄና የብአዴን መልስ,.....?!? (አሳዬ ደርቤ)

የአማራ ጥያቄና የብአዴን መልስ,…..?!?

አሳዬ ደርቤ

➔መተከል ላይ ንጹሐንን ሲጨፈጭፍ የከረመው የጉምዝ ታጣቂ ከቀናት በፊት ከባድ ጥቃት ፈጽሞ የግድቡን ሠራተኞችን እና ጠባቂዎችን ገድሏል፡፡
➔በእነ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የሽብር ሠራዊት አፋር ክልል ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በፈጸመው ወረራ አምሥት ወረዳዎችን ተቆጣጥሮ በርካታ ንጹሐንን መግደልና ማፈናቀል ከጀመረ ወራቶች ቢቆጠሩም የፌደራል መንግሥቱ ግን ዘመቻውን ትቶ ዛቻው ላይ በርትቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይሄው የሽብር ቡድን በቀጣይ አማራ ክልልን ለመውረር ከፍተኛ የጦር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
➔ከሁለት ሳምንት በፊት ወለጋ ላይ ከ200 በላይ አማራዎችን የጨፈጨፈው የኦነግ ታጣቂ ሸዋ ምድር ገብቶ መንገድ መዝጋቱንና ዜጎችን መግደሉን አጠናክሯል፡፡
ሦስቱም የሽብር ቡድኖች ታዲያ ዋነኛ ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማፍረስና የአማራን ደም ማፍሰስ ቢሆንም የፌደራሉም ሆነ የአማራ ክልል መንግሥት አስቸኳይ እቅድ ግን ፋኖን ትጥቅ ማስወረድ ሆኗል፡፡ በዚህም ዘመቻ በዛሬው እለት ትልቅ ጀግና ነጥቀውናል። (ነፍስ ይማር)
እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ታዲያ ተላላኪው ፓርቲ ፋኖ ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ሳይሆን ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት አለመቻሉ ነው፡፡
➔ከላይ ከተጠቀሱት አሸባሪዎች በፊት ፋኖን ማጥፋት የፈለግከው ምን አይነት ጥቃት ፈጽሞ ነው?
➔ሸዋ ምድር በሚርመሰመሰው አውዳሚ ጦር ፈንታ በሸዋ ምድር የሚኖረውን አማራ የማስከበር ግብ ይዞ የተደራጀውን ፋኖ በስጋት መመልከት የቻልክበት ምክንያት ምንድር ነው?
➔በመተከል እና በጎጃም ምድር እየተንቀሳቀሰ ንጹሐንን ብቻ ሳይሆን መከላከያን በማጥቃት ላይ ከሚገኘው የጉምዝ ታጣቂ በላይ በጎጃም ምድር የተደራጀው የአማራ ፋኖ ስጋትህ መሆን የቻለው እንዴት ነው?
➔ወሎን እና ጎንደርን ለመውረር ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኝ ወራሪ ተሸክመህ ‹‹ከዚህ በላይ ውርደትና ውድመት የሚሸከም ሕዝብ የለኝም›› በሚል አቋም በእራሱ ምድር ላይ የተደራጀውን የአማራ ፋኖ ለመበተን የተነሳሳህ ክልሉን መጠበቅ የሚችል ምን ያህል ልዩ ሃይል ቢኖርህ ነው?››…. ለሚሉት ጥያቄዎች ብአዴን የሚሰጠው መልስ እንዲህ የሚል ነው፡፡
‹‹ፋኖን ትጥቅ አስፈታ››
የሚል ቁርጥ ትእዛዝ- ከላይ ስለመጣ
ጥያቄህን ትተህ- ክላሽህን አምጣ፡፡
ጠላት ቢኖርህም
ንብረትክን የሚያወድም- ደምህን የሚያፈስስ
ጌቶች ስላዘዙ
የፋኖ መዋቅር- ባፋጣኝ እንዲፈርስ
ትጥቅህን ፍታና-
ጋቢህን አጣፍተህ- ‹‹ጠፋሁ›› እያልክ አልቅስ፡፡
Filed in: Amharic