>

(አለም አቀፍ የሴቶች ቀን) በሙያቸው የመጀመሪያ በመሆን በግንባር ቀደምትነት የተመዘገቡ ሴት ኢትጵያውያን ፤ (ታሪክን ወደኋላ)

(አለም አቀፍ የሴቶች ቀን)

 March8  በሙያቸው የመጀመሪያ በመሆን በግንባር ቀደምትነት የተመዘገቡ ሴት ኢትጵያውያን ፤
ታሪክን ወደኋላ

1. ልዕልት ፀሀይ ኃይለስላሴ — የመጀመሪያው የነርሲንግ ሞያ ያጠናችና ለመጀመሪያ ጊዜ በሬድዮ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ
2. ዶ/ር ወዳድ ኪ/ማርያም — የመጀመሪያው ሴት ሀኪም
3. አውሮኘላን አብራሪ ወ/ሮ ሙሉ እመቤት እምሩ ሲሆኑ ለብቻቸው አውሮፕላን ያበረሩት ደግሞ ወ/ሮ አሰገደች አሰፋ ናቸው።
4. ወ/ሮ ብርነሽ አስፋው — የመጀመሪያዋ ሴት መሃዲስ
5. ወ/ሮ ሮማንወርቅ ካሳሁን — የመጀመሪያዋ ሴት የሬድዮ ጋዜጠኛ የሴቶች ፕሮግራም አዘጋጅ
6. እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ –የፒያኖ ለስላሳ ሙዚቃ በሸክላ ያስቀረፁ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ
7. ወ/ሮ አፀደወይን ተክሌ — የመጀመሪያዋ ሴት ዳኛ
8. ዶ/ር አዳነች ኪ/ማርያም እና ወ/ሮ መንበረ አለማየሁ – የመጀመሪያዎች ሴት ሚኒስትሮች
9. ዩዲት እምሩ — የመጀመሪያዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር
10. ሠላማዊት ገ/ስላሴ — የመጀመሪያዋ ሴት ተዋናይ
11. ስንዱ ገብሩ — የመጀመሪያዋ ሴት ፓርላማ አባል
12. ወ/ሮ ፀሀይ መላኩ — የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት የረጅም ልብወለድ ደራሲ (ቋሳ)
13. ወ/ሮ የዝና ወርቁ– የመጀመሪያዋ ሴት አጭር ልብወለድ ደራሲ (የተሸጠው ሰይጣን)
14. ፋንታዬ ተሰማ የመጀመሪያዋ ሴት ማሲንቆ ተጨዋች
15. ሜሪ አርምዴ የመጀመሪያዋ የውጪ ፀጉር አስተካካይ (ፍሪዘር)ተመራቂ
16. እቴጌ ጣይቱ ብጡል የመጀመሪያዋ ሴት ብስክሌት የነዱ
17. አልማዝ እሸቴ የመጀመሪያዋ ሴት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር
18. አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ ሴት የኦሎምፒክ ባለወርቅ ተሸላሚ
19. ሞዴል የሀረርወርቅ ጋሻው በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት (International Black Actress)
20. ወ/ሮ ባዩሽ ታደሰና ወ/ሮ ብርቱኳን በቀለ የመጀመሪያዎቹ ሴት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች
21.እማማ ፂዮን ሚካኤል የመጀመሪያዋ ሴት የልብስ ዲዚያነር
Filed in: Amharic