>
5:21 pm - Sunday July 21, 3163

ኧረ ኡ...ኡ...ኡ... የጦስ ዶሮ ያለህ....!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

ኧረ ኡ…ኡ…ኡ… የጦስ ዶሮ ያለህ….!!!  
ዘመድኩን በቀለ

*…. ፀረ ህዝብ፣ ነፍጠኛ፣ የድሮ ሥርዓት ናፋቂ፣ የአፄዎቹ ሥርዓት ናፋቂ፣ ጠባብ፣ ፅንፋኛ፣ አክራሪ፣ የሻአቢያ ተላላኪ፣ የአልሸባብ ተላላኪ፣ የግንቦት ሰባት ቅጥረኛ፣ ኦነግ የኦነግ ቡችላ፣ ቅንጅት፣ የቅንጅት ደጋፊ፣ የሚል ነፍ ታፔላና የዳቦ ስም እያወጣ ያፍን፣ ይረግጥ ይገዛ ነበር። ብዙዎች ኢትዮጵያውያን በዘመነ ህወሓት በዶክተር ዐብይ አሕመድ የደኅንነት መሥሪያ ቤት የስለላ መረብ ተጠርጥረው ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ አካላቸው ጎድሏል፣ ተሰደዋል።
“…ሁሉም ዘመን የጦስ ዶሮም ከህዝብ ጥያቄ መሸሻ መሸሸጊያ፣ መደበቂያም ጎሬ ያበጃል። ደርግ በፊውዳሉ፣ በፀረ አቢዮተኞቹ፣ በኢህአፓ፣ በወያኔና በሻአቢያ እያሳበበ የህዝብ ጥያቄ ላለመመለስ ቡርዧ፣ አድሃሪ፣ አቆርቋዥ እያለ ሲነተርከን እርሱም መከራውን ሲበላ ህዝቡንም አፈር ከደቼ ሲያስበላ ከርሞ መጨረሻ ላይ እንደ ጢስ በኖ፣ እንደ ጤዛ ተንኖ ጠፍቶ አረፈው። የደርግ መደበቂያው ይሄ ነበር። ኢፕፔሪሊያሊዝም፣ ገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴ… ወዘተረፈ።
“…ድልድይ አፍራሿ፣ ባንክ ዘራፊዋ፣ ገንጣይ አስገንጣይ ወንበዴዋ ህወሓት ከነ ቁምጣዋና ከነቅጫሟ ሽፍታዋ የኢትዮጵያን መንበረ ሥልጣን በተቆጣጠረች ጊዜም እንደ አባቷ ደርግ የጦስ ዶሮ አላጣችም ነበር። የአላባኒያ ኮሚኒስት ሆና ኮተቤ ስትደርስ ዲሞክራሲን ቃሉን የሰማችው ወያኔ የኮሚንስቱ ካም መፍረሱን ስታይ በፍጥነት ጃኬቷን ቀይራ ሁለቱም እንዳይቀርባት አብዮቱንም፣ ዲሞክራሲውንም ይዛ ጉዞዋን ቀጠለች። ጥያቄ የሚጠይቃትን ሁሉ ታፔላ እየለጠፈች ነዳችን፣ ገዛችን።
“…ፀረ ህዝብ፣ ነፍጠኛ፣ የድሮ ሥርዓት ናፋቂ፣ የአፄዎቹ ሥርዓት ናፋቂ፣ ጠባብ፣ ፅንፋኛ፣ አክራሪ፣ የሻአቢያ ተላላኪ፣ የአልሸባብ ተላላኪ፣ የግንቦት ሰባት ቅጥረኛ፣ ኦነግ የኦነግ ቡችላ፣ ቅንጅት፣ የቅንጅት ደጋፊ፣ የሚል ነፍ ታፔላና የዳቦ ስም እያወጣ ያፍን፣ ይረግጥ ይገዛ ነበር። ብዙዎች ኢትዮጵያውያን በዘመነ ህወሓት በዶክተር ዐብይ አሕመድ የደኅንነት መሥሪያ ቤት የስለላ መረብ ተጠርጥረው ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ አካላቸው ጎድሏል፣ ተሰደዋል።
“…ተራው የዘመነ ህወሓቱ የሰላዮች አለቃ የዶርኮ ዐብይ አሕመድ ሆነ። ዶርኮ ዐብይ ብልጥ፣ አራዳ ልሁን ብሎ እኛን ለማደንዘዝ ሲንቀዠቀዥ የወርቅ እንቁላል የሚጥሉለትን የጦስ ዶሮዎቹን በሙሉ አርዶ በላቸው። ከሻአቢያ ጋር ሲንቀዠቀዥ ታርቆ የጦስ ዶሮ ሻኣቢያን የኖቤል ሽልማት በላበት። ኦነግን ከነታንኩ አስገብቶ እሱን እንኳ ሥራ እየሠራበት ነው። ግንቦት ሰባትን አምጥቶ ገሌ አድርጎ ሚንስቴር አደርጎ አረፈው።  የዚያድ ባሬ ሶማሌን እህት አገር አድርጎ አረፈው። የግብጽ አሽከር ሆኖ ወላሂ፣ ወላሂ ብሎምሎ ዕድሉን ዘጋው። ዐብን እንኳ የጦስ ዶሮ እንዳይሆነው መሪዎቹን ሰብስቦ ሹመት ሰጥቶ ለጎማቸው። አሁን በማን ያሳብ? የጠላት ያለህ የጦስ ዶሮ ያለህ እያለ መከራውን እየበላ ይገኛል። ወያኔን ለጥቂት ቀን የቀን ጅብ፣ ሌባ፣ የመርከብ ሌባ፣ ዱቄት፣ ወንበዴ ምናምን ብሎ ሁለት ሰንበት ተሻገረበት። ብዙም ሳይቆይ ለወያኔም እጅ ሰጠ። አሁን የጦስ ዶሮ እየፈለገ ነው። አዋጭነታቸው ነው አስተማማኝ ያልሆነው፣ ህዝቡም አልቀበል አላምን አለው እንጂ ዕጩ የሚሆኑ ግን አግኝቷል። እነርሱም ፋኖ፣ ሸኔ፣ ጁንታ፣ ባልደራስ እና “አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴ” የሚባሉ መንግሥት ብቻ የሚያውቃቸው አካላት።
“…ፋኖን ሞክሮ ይተወዋል። መቆስቆስ ፈልጓል ምን እንደፈራ ግን መድኃኔዓለም ይወቅ። ሸኔ ራሱ ብልፅግና መሆኑን ህዝቡ ስላወቀ አሁን ሃላል እየወጣ መታየት ጀምሯል። ጁንታም እርቅ ላይ ነው። ባልደራስም ለጠብ፣ ለጦስ ዶሮነት የሚመች አልሆነም። ወገምት የሆነ ፓርቲ ነው። ነቄ የገባው የአራዳ ልጅ ስለሆነ ሰገጤ ፋራዎች በሚያመቻቹት ጨዋታ ውስጥ የሚዘፈቅ አይደለም። በካራማራ በዓል ፖሊስ “ሊበጠብጡ ነበር” ሲል ባልደራስ ግን ሂደቱን በቪድዮ ስለቀረጸው ለሽብር ክሱ አልተመቸም። እንዲያም ሆኖ ግን የኢህአዴግ ልጅ የጦስ ዶሮ መፈለጉን አላቆመም።
“…አሁን በዚህ በዘመነ ብልፅግና ትግሬ ሆነህ ራበኝ ብትል ጁንታ፣ ወያኔ ነህ ትባላለህ። ዐማራ ሆነህ ራበኝ ብትል ነፍጠኛ ነህ ትባላለህ። ሱማሌ ብትሆን የጁንታ ተላላኪ አልሸባብ፣ ጉራጌ ብትሆን ግልገል ነፍጠኛ ተብለህ ትፈረጃለህ፣ ትደፈጠጣለህ። አዲስ አበቤ ከሆንክ ደግሞ ባልደራስ ነህ፣ ፀረ ኦሮሞ ተብለህ ትከሰሳለህ። ችግሩ ኦሮሞም ሆነህ አይለቅህም። እንዲያውም የኦሮሞው ይብሳል። ኦሮሞ ሆነህ ራበኝ ብትል የነፍጠኛ ተላላኪ፣ የጁንታ ናፋቂ ቅጥረኛ፣ ሸኔ፣ አባቶርቤ ትባላለህ። ቻለው እንጂ…ዋጥ አድርገው፣ ምንም ብትራብ፣ ብትጠማ፣ ብትቸገር ከነፍጠኛ፣ ከወያኔ እኩል እኛ ልጆችህ ላይ እንዴት አፍህን ትከፍታለህ? ይባላል። ኦሮሞ ሆነህ እንዴት የኦሮሞ መንግሥት ትቃወማለህ? ከሃዲ፣ ጎበና፣ ሚኒቲስ፣ ቅብጥርስዮ ብለው እሳት እንደነካው ላስቲክ ያጨራምቱታል።
“…እኛ ኦሮሞ ስለሆን ነው ምድረ ነፍጠኛ፣ ምደረ ጁንታ፣ ተላላኪው ኦነግ ሸኔ የሚቃወመን ብለው ይለፍፋሉ። ለብልፅግና መደበቂያ ኦሮሙማ ለጊዜው ምቹ አፈር ሆኖለታል። ዋሻው ሆኖለታል። ግን እስከየት ድረስ ያዘልቀዋል ነው ጥያቄው? ለሚርበው፣ ለሚጠማው፣ ኑሮ አፈር ከደቼ እያበላው ላለው ህዝብ እስክንድርን፣ ባልደራስን፣ ፋኖንና ጁንታን በመክሰስ መሰናክሉን ማለፍ ይቻላል ወይ? ሼም የሚባል ነገር የለም ወይ? ሃገር ማስተዳደር ሲያቅትህ በዘርህ ውስጥ ተሸጉጠህ ለማለፍ የምታደርገው ጥረት ቢያስበላህ እንጂ አያተርፍህም።
“…አዲስ አበባን ፊንፊኔም፣ ፉልፉሌም ብትላት ጠብ የሚል ነገር የለም። ባለቤቱ የማይገለጽ፣ የመቼ እንደሆነ የማይታወቅ፣ በየትኛው መጋዘን የተያዘ እንደሆነም የማይገለፅ የተከዘነ የዘይት ካርቶን እያሳየህ ዜና ስለሠራህ የዘይት ዋጋ እንደሁ አይቀንስልህም። የቤት ኪራይም፣ የጤፍ ዋጋም አይቀንስልህም። ሙሉ ኢትዮጵያ ቁቤ ቢናገር ቋንቋው ቢዴነ አይሆነውም። ዳቦ አይሆነውም። ሙሉ አዲስ አበባን በኦሮሞ ወጣቶች ብትሞላው በቀበሌ፣ በወረዳ፣ በከተማ አስተዳደሩ ላይ ብታፈሰው ሥራ፣ እንቅስቃሴ ከሌለ ስንዝር አታራምደውም። ህዝብ እየበዛ አንተ ለህዝቡ ሥራ መፍጠር ሳትችል ቁጭ ብለህ ተጎልተህ ካድሬ ካድሬ እየተጫወትክ አታሻግረውም። ህዝብ እየተራበ አንተ ቢሮ እድሳት ላይ፣ መናፈሻ ግንባታ ላይ ተጠምደህ መፍትሄ አታመጣለትም። ቤርቤረሰቦች ሁሉም ሙልጭ ብለው አልቀውልህም ኦሮሞን ብቻ ይዘህ አታሻግረውም። ቦረናን ምን ፈየድክለት? ኣ? አልተገናኝቶም። የፈለከውን በል በዚህ ሕገ መንግሥት፣ በኢህአዴግ ቁጥር ሁለቶች ጭንቅላት ኢትዮጵያ አትነሣም።
“…መፍትሄው ቦታውን፣ ሥልጣኑን ለሚችል መስጠት፣ መልቀቅ ብቻ ነው። ሌባ ሃገር መምራት አይችልም። ሌባ ሌባ ነው። አከተመ።
Filed in: Amharic