>

ከሕዝብ በስተጀርባ ድርድር ወይስ ሴራ?! (በቀለ ገብሬ)

ከሕዝብ በስተጀርባ ድርድር ወይስ ሴራ?!

በቀለ ገብሬ

ከሐምሌ 2013 የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ህወሐት የአማራንና የአፋር ክልሎችን በጦር ኃይል ወረራ ጀመረ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ደቡብ ጎንደርን፣ ሰሜን ጎንደርን፣ ሰሜን ወሎን፣ ደቡብ ወሎንና ሰሜን ሸዋን ከአማራ ክልል ሲወር፤ ከአፋር ክልል ምዕራባዊ አፋርን ከካሳጊታ አነ ጭፍራን ይዞ የጂቡቲን መንገድ ለመቆጣጠር እልህ አስጨራሽ ውጊያ ተካሄደ፡፡ በምዕራባዊ አፋር በተካሄደው ውጊያ የአፋር ልዩ ሓይል፣ ሚሊሺያ እና ሕዝባዊ ሐይል ከፍተኛውን ትንቅንቅ ሲያደርግ  የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ከአፋር ሓይል ጋር አስፈላጊውን መስዋእትነት ከፍሎ የኢትዮ-ጂቡቲን መንገድ ተከላክሏል፡፡ በአማራ ክልል በተደረገው ውጊያ የአምሐራ ልዩሐይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሺያው እና ሕዝባዊ ሐይሉ ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል የመከላከል ተጋድሎውን ፈጽሟል፡፡

¨የሀገር መከላከያ ሠራዊትም እንደ አፋሩ ግንባር ሳይሆን በአብዛኛው ከራያ/ ኮረም እስከ ሰሜን ሸዋ/ጣርማበር ድረስ በማፈግፈግ እና የህወሐት ታጣቂወች ሲተላለፉ/ሐይል እያመላለሱ ሲያከማቹ አልታዘዝንም በማለት ከማስተናገዳቸውም ባሻገር በፋኖ፣ ልዩ ሐይልና ሚሊሻ  በመስዋዕትነት የተያዙ ገዢ ወታደራዊ ቦታወችን ለቀው እንዲያፈገፍጉም ትዕዛዝ ሰጥተው በብዙ ቦታዎች ይሄው መፈጸሙን በርካታ ታዛቢዎችና ግንባር ላይ ያሉ የጸጥታ ሐይሎችና ገበሬዎች ይመሰክራሉ፡፡ ይህም ሆኖ ከአብዛኛው የአምሐራና አፋር ክልሎች በጥምር ጦሩ ተመትቶ ሊወጣ ችሏል፡፡  ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የመከላከያውም ሆነ የሌሎች ኢትጵያውን ግምት የነበረው ህወሐትን የገባበት ገብቶ ትጥቅ ማስፈታት ነበር፡፡ የፌደራል መንግስቱ አሁንም ትግራይ ሌላ አገር እንደሆነች በማስመሰል መከላከያው ባለበት እንዲጸና እና ወደ ትግራይ እንዳይገባ በመታዘዙ የብዙ ኢትዮጵያውንን ወሽመጥ ከመቁረጡም ባሻገር ህወሐት ጊዜ ተሰጠውና እንደገና ተደራጅቶ ለዳግም ወረራ በቃ፣ ይህንንም ለማድረግ ቻለ፣ በዚህም የአፋርና አምሐራ ሕዝብ ሰቆቃ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጦርነቱ ቆሟል፣ ህወሐት ከአፋርና ከአምሐራ ክልሎች ወጥቷል ከተባለ በኋላ ከአምሐራ 11 ወረዳዎች፣ ከአፋር 5 ወረዳወች በህወሐት ሥቃይ ሥር ናቸው፡፡ ሕዝቡ ያለገደብ በሚሊዮኖች ተፈናቅሏል፣ በመቶ ሽዎች እናቶች፣ ሕጻናት፣ አዛውንት፣ ወጣቶች በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ብቻ ሳይሆን በመድሃኒትና በምግብ እጦት በሽዎች የሚቆጠሩ ሕይታቸው አልፏል፡፡ የተረፉትም ተፈናቅለው ቤት ንብረታቸው ወድሟል ወይም ተዘርፏል፡፡አያቶች፣ እናቶች፣ መለኩሴዎች፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሴት ልጆች እስከ 7 ና 8 በሚደርሱ የህወሐት ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በቡድን ተደፍረዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ ፋብሪካዎች፣ ፍርድ ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የግልና የቡድን እንዲሁም መንግገሥታዊ ያልሆኑና አለምአቀፍ ድርጅቶች ተዘርፈዋል ወይም ወድመዋል፡፡

በአጠቃላይ የአምሐራና የአፋር ሕዝብ በታሪኩኤይቶት በማያውቀው ሁኔታ በዶ/ር አብይ አስተዳደር ተዋርዷል ፡፡ስለዚህ የጦርነቱ ዋና ባለቤት የአምሓራና የአፋር ሕዝብ ነው፡፡
ይህ በዚህ እንደለ ፌደራል መንግሥት ጦርነቱ አልቋል ብሎ ሠራዊቱን ባለበት እንዲጸናና ተኩስ አቁሞ የቀጠለውን ጦርነት ታዛቢ ሆኗል፡፡  ይህ ሁሉ እልቂት ሲፈጸም የሀገርንና
የሕዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሕዝብ በከፈለው የግብር ገንዘብ ተቀጥሮ፣ ሰልጥኖ፣ ታጥቆ ደመወዝ  እየተከፈለው በብሔረሰብ ጠባብ ፖለቲካ ሴረኛ አመራሮች እግር ተወርች ታስሮ ወገኖቹ ሲያልቁ፣ አልታዘዝኩም በማለት ወይም የያዘውን ከተማ/ ገዢ ቦታ እየለቀቀ ለህወሐት እያስረከበ ማፈግፈግ፣ እንዲሁም ፋኖንና ልዩ ኃይሉን ማስመታት የዘወትር ባህሪው ሆኖ ከርሟል አሁንም ይሄው እየተስተዋለ ነው፡፡

ይህ ሁኔታ ቀጥሎ እያለ መንግሥት በሚስጢር ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ከህወሐት ጋር በጎረቤት አገር ኬንያ ድርድር መጀመሩና በሂደት ላይ እንደሆነም ከተለያዩ ምንጮች
እየተሰማ ይገኛል፡፡ ከተመድ ጭምር ተስፋ ሰጪ እየተባለ ፍንጭ እየተሰጠ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚ/ትሩም ዳርዳር ይላቸዋል፡፡ ለምን መደባበቅና መሸፋፈን አስፈለገ? ከህወሐት ጋር ምን ዓይነት ስምምነት ሊደረስ፣ ህወሐት ነጻአውጭ ታጋይ ሆኖ፣ መንግሥት ሆኖም ፣ ዛሬ ከፌደራል ሥልጣን ተወግዶም  በ46 ዓመታት ታሪኩ አድርጎትም አያቅም ዛሬም አያደርገውም፣ የድርድር ሥነ-ልቡናም ሆነ የሰላም መንፈስም የለውም፣ ያለ ጦርነት ውሎ ማደር አይችልም፡፡
ድርድር እንኳን ቢያስፈልግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብሳያውቀው፣ ከዋና ተጎጂዎች በስተጀርባ፣ ተደራዳሪዎች በማይታወቁበትና የድርድር ቅደመ-ሁኔታወች እና የድርድር ጭብጦች
ባልታወቁበትና ስምምነት ባልተደረሰበት ሁኔታ ከህወሐት ጋር ቢተሻሹ ምንም እንደማይፈይድ እና ችግሮችን እንደማይፈታ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አውቆት ከሴራ ፖለቲካው ቢታቀብ ይበጃል፡፡ የጦርነቱ ሰለባዎች፡ 1ኛ. የኢትጵያ መከላከያ ሠራዊት 2ኛ. የአምሐራ ሕዝብ  3ኛ. የአፋር ሕዝብ ናቸው፡፡

የነዚህ ሰለባ የማህበረሰብ  አካላት፡

1ኛ. የጠፋው ህይወት 2ኛ አካለ-ጎደሎ  የሆኑ ህጻናት፣ እናቶች፣ አባቶች እና ወጣቶች 3ኛ የየአካባቢው የወደሙና የተዘረፉየመንግሥት፣ የህዝብ፣ የግልና የድርጅት ሀብቶች/ንበረቶች 4ኛ. በየማህበረሰቡ ከእምነቱና ባህሉ ውጭ እጅግ አስጸያፊ በሆነ መንገድ በግለሰብና  በቡድን ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሴት ህጻናት፣ አናቶች፣ አሮጊቶችና መነኮሳት የተደፈሩበት፣ የደረሰው የሞራልና ማህበራዊ ቀውስ ተጠንቶ ባልታወቀበት 5ኛ. በቤተ-ዕምነቶች ላይ የደረሰው ፍርሰት፣ የቅርስና ንብረት ዘረፋ እና ኢ-ሞራላዊ በሆነ ሁኔታ በበተ-መቅደስና በመስጊዶች ውስጥ አልኮል አስገብቶ ከመጠጣት ባሻገር በክቡር መስቀሉ ላይና መስጊደች ውስጥ በመጸዳዳት በተ-ዕምነቶችን አርክሰዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተጠንተው ዋጋቸው ታውቆ የድርድሩ አካል ባልሆኑበት ሁኔታና ከሁሉም ጉዳተኞች ማህበረሰቡ ያመነባቸው ተደራዳሪዎች በለሉበት ሁኔታ የሚካሄደው የድርድር ሽር ጉድ ህወሐት ይህንን ሁሉ ውድመት አድርሶ  በአሸናፊነት የሚወጣበትና ጠ/ሚ አብይ  ወልቃይትንና ራያን በሴራ ለማስረከብ እንዲሁም ተጨማሪ መሬቶችን ከአምሐራና አፋር እናንተ ተዋግታችሁ ያዙ ኋላ በድርድር ለእናንተ እንወስናለን የሚል የሞኝስምምነት በመግባት ሀገሪቱን በዘላቂ ቀውስ ውስጥ በመተው፣ የራሳችሁ ጉዳይ እኛ የራሳችንን ዕድል እንወስናለን በሚል ሀገሪቱን ከማፍረስ ሴራ የዘለለ ውጠት አያመጡም፡፡ ምናልባት ዛሬ በናይሮቢ ከተማ በአሜሪካኖች አመቻችነት ሽምግልና ከህወሐት ስዬ አብርሀና ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ፣ ከኦህዴድ ወርቅነህ ገበየሁና ለማ መገርሳ ሆነው በኬንያ አሸማጋይነት የሚያካሄዱት ስምምነት የኢትዮጵያን ሕዝብ የማይመለከት ግን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ትልቅ ሴራ እየተደገሰ መሆኑን እያንዳንዱ ዜጋ ሊገነዘበው ይገባል፡፡

እነዚህ የእርቅ ምልክቶችም ህወሐት ካቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች መልስ ሲሰጣቸው እየታየ ነው፡፡ ለአብነትም ያህል፡ የህወሐት  እስረኞችን  ፍቱ (ተፈቱ)፣ የኢፈርት ኩባንያወችን፣ ሕንጻዎችንና የባንክ  ሂሳባችን ይለቀቁ(ተለቀቁ)፤ የትግራይ ድንበር ወደ ነበረበት ይመለስ የህንንም ለመፈጸም ወልቃይትንና ራያን ለማስረከብ ጦርነቱ አልቋል በሚል ሰበብ ሠራዊቱ ራያን አስረክቧል፣ ወልቃይትን አሳልፎ ለመስጠት በሁለት መንገድ እየሄደበት ነው‹፣ ይሄውም የአምሐራን ልዩ ሃይል በማዳከምና በማፈራረስ እንዲሁም ፋኖን ትጥቅ በማስፈታትና በማዋከብ ላይ ይገኛል፣ ከዚያም የህወሐት ጦር ወሮ እንዲይዝ በማመቻቸት ላይ ይገኛል፣ ሌላው አካሄድ ደግሞ ወልቃይት በፌደራል ሥር ሆኖ ሕበ-ድምጽ እንዲሰጥ ተብሎ እንደ ምርጫውና የሲዳማ ሕዝበ-ድምጽ  እጅ ሥራ ተከሽኖ  ለትግራይ ለማስረከብ ነው፣  ካልሆነም ይሄው ተግባር  የተመድ የሰላም አስከባሪ ጦር ወልቃይት ገብቶ የሕዝበ ድምጽ ድራማውን ለመከወን የአብይ አስተዳደርና የአማራ ክልል አስነዋሪው የበአደን አስተዳደር ደፋ ቀና እያሉ መሆናቸውን ሁኔታወችና ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

የአምሐራ ፋኖን ማፍረስና ልዩ ሃይሉን ማደከምም የህወሐቶች የጓደኝነት ጥያቄ መሆኑም እየተሰማ ነው፡፡ ህወሐቶች እንደ ቅደመ ሁኔታ ካነሷቸው ሞልቃቃ ጥያቄዎች መካከል እስከ አሁን ፍንጭ ያልታየው የመከላከያ አዛዦች  በተለይ  ኤታማጆር ሹሙና ምክትላቸው አንዲነሱላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ነው፡፡ ከሁሉም አስቂኝ የሚሆነው የኢትዮጵያ መንግሥት (ተደራዳሪዎች)  ሰላም አስከባሪ ጦር  ይግባልኝ ማለቱ ነው፣ ይህ ተሸናፊነት ነው፡፡

ለማንኛውም በዚህ ጦርነት ለወደመው ሁሉ የአብይና የአምሐራ ክልል በአደን አስተዳደሮች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ከሕዝብ በስተጀርባ በድብቅ ድርድር ኦህዴድና ህወሐት በሕዝብ ላይ የሚጭኑት ሰምምነት ተቀባይነትም የለውም ሰላምም አያመጣም፡፡ ተወደደም ተጠላ አሁን ያለው መንግሥት የብሔረሰብ/የቡድን መንግት ስለሆነ ኦህዴድና ህዋሐት የአምሐራንም ሆነ የአፋርን ሕዝብ አይወክሉም፣ እንዲያውም ጠላቶች ናቸው፡፡ መከላከያ ሠራዊቱም የሕዝብ እንጂ የአንድ ብሔረሰብ ፖለቲካ ቡድን የግል ኩባንያ አይደለም፡፡

የአገር ዳር ድንበር ተደፍሮ በባዕድ ሃይል ተይዞ፣ ሕዝብ በጉልበተኛ ቡድን በከባድ መሣሪያ ሲጨፈጨፍ በሽዎች ሕጻናት፤ እናቶችና አዛውንት ሲገደሉ፣ በመቶ ሽዎች ተፈናቅለው ሁብት ንብረታቸው ወድሞ በአንድ ጀንበር ተርበውና ታርዘው የምጽዋት እጆች ጠባቂ ሲሆኑ፣ ይሄው በአፋርና አምሐራ ክልሎች ሕያው ምሥክር ሆኖ እያለ፣ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ሆኖ አልታዘዝኩም ማለት ሃላፊነትን መዘንጋትና ከታሪክ ተወቃሽነትም አልፎ በሕግ ማስጠየቁ አይቀርምና መከላከያ ሠራዊት አባላት ሀገር ስትፈርስ ዝም ብላችሁ
አትመልከቱ፡፡

Filed in: Amharic