>
5:18 pm - Tuesday June 16, 2229

እንደ ወልቃይት አዲስ አበባም ተመሳሳይ ታሪክና ትርክት እያስተናገደች ነው!  (ፊልጶስ)

አዲስ አበባ ሌላዋ  የዘመናችን የኢትዮጵያ ወልቃይት !

 

ፊልጶስ


 የአዲስ አበባ ወጣቶች እየታደኑ እየታሰሩ ነው። የአድዋን 126 የድል ቀን   በሚኒሊክ አደባባይ መከበርና የብልጽግናን ሌብነት በአደባባይ መነገር፤  ለኢሳቷ  (ESAT) የዘመናችን ጣይቱ ብጡልና ለመሰሎቿ የሚዋጥላቸው አልሆነም።  የካራ ማር 44 የድል ቀንም /  አብይ አህመድ ለወጉእንኳን አደረሳችሁ”  ባይሉም፤   የድሉን ቀን ለማክበር የወጡ ኢትዮጵያዊያኖችና  የባልደራስ ለእውነትኛ ዲሞክራሲ አባላት ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተወረወሩ።  አሁንም  ”ኢትዮጵያዊ   ነው”  ያሉትንና በኢትዮጵዮጵያ ሰንደ ዓላማ  አረንጓዲ፣ ቢጫ፣ ቀይ፤ የማይደረደርውን  ሁሉ በየቤቱ እያደኑ በማሰር ላይ ናቸው።  ታዲህ ይህ   በኑጹሃን ላይ የሚደረግ ግፍና በደል  ወልቃይትን ያስታውሰናል። ወልቃይት  የወያኔ መቃብር እንደሆነች ሁሉ፤ አዲስ አበባም ለኦሮሙማብልጽግና መቀበሪያ እንደምትሆን የጎሰኝነትንና የተረኝነትን የአገዛዝ አወዳደቅ ያስተምረናል።

ከዘመናት የወያኔ ግፍና ስቆቃ በኋላ ወልቃይት አሁንም አደጋው እንደተደቀነ ቢሆንም  “ነፃወጥታለች። ወልቃይት ለዚህ ለመብቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ታስረዋል፣  ተገለዋል፣ ተሳደዋል፣ አካለ ስንኩል ሆነዋል፣ በጅምላ ተቀብረዋል፣ በአጠቃላይ ወያኔ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመው ግፍ ሁሉ በደቦ ተፈፅሞባታል። ታዲያ ወልቃይት ከወያኔ ነፃ ስትወጣ አዲስ አበባም በተመሳሳይ ሁኔታ በተረኞቹ ኦሮሙማ-ብልጽግናዎች   በዜጎቿ ላይ   ግፍ እየተፈጸመ ነው።

እንደ ወልቃይት አዲስ አበባም ተመሳሳይ ታሪክና ትርክት እያስተናገደች ነው። 

ልቃይት፤  ወያኔ ትግል እንደጀመረ 1966 እስከ 1967 ድረስ ወደ ሱዳን የሚያደርገው ማንኛውም ደርሶ መልስ ጀብሃ በሚቆጣጠረው በኤርትራ ክፍለ ሃገር አድርጎ ነበር። 1967 መጀመሪያ አካባቢ ወያኔ ርዳታ ድርጅት የዘረፈውን ቁሳቁስና የጭነት መኪናዎች ይዘው ወደ ሱዳን ለመሻገር ሲሞክሩ ጀብሃ።ከዘረፋችሁት ሃብት ግማሹን አካፍሉኝአለ። ወያኔ ስግብግብ ‘’ዘራፍ!’’ አለ። ብሎም አልቀረ፥፥ የዘረፈውን ሃብት ከነመኪናዎቹ አቃጠላቼው። እናም ተከዜን ተሻግሮ ወደ ወልቃይት ፊቱን አዞረ። ቀስበቀስም አካባቢውን ተቆጣጥሮ ከሱዳን ጋር ለሚያደርግ ግንኙነት ብሎም ወያኔ ለህልውናው የደም ስር ወልቃይት ሆነች።

አዲስ አበባ ወያኔአዲስ አበባን የኔ የግሌ ነችለማለት ምክንያት ስላልነበረው ከተማዋን አራቁቶ በልቶ ተቃውሞው ሲያስፈራው በተለይም 1997 ምርጫ በኋላ  የትላንቱን ኦህዴድ፤ የዛሬውን ኦሮሙማ- ኦነጋዊብልጽግና  ከናዝሪት አውጥቶአዲስ አበባ ያንተ ነችአለው። ወያኔ የአዲስ አበባን ህዝብ ለመበቀልና አንገት ለማስደፋት  ከሄደበት መንገድ አንዱ ይህ ነበር ርግጥ ወያኔ የአዲስ አበባን ህዝብ በተዘዋዋሪም በዘረኞቹ  የመቆጣጠሪያ ስልት መቀየሱ ነው። 

ልብ እናድርግ!… ወያኔ ጀበሃ ግዛት አታልፍም ሲለው የሄደው ወደ ወልቃይት ነበር። የአዲስ አበባ ህዝብ የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቀደሞ የተረዳ በመሆኑ፤ የሱን ወንቶፈንቶ የጎሳ ፓለቲካ “— የነካ እንጨትሲያደርግበት ለኦህዴድ አዲስ አበባን በእጅ መንሻ ሰጠው። ወያኔ ፈንጅ ለመቅበሩርግጠኛ ነበር፥፥ ለምን እና እንዴት? ብለው የማይጠይቁት የኦህዴዲ ጽንፈኞች ደግሞ እንደ ትልቅ ድል ቆጥረውታል።

ወልቃይት፤ ወያኔዎች የወልቃይትን ማንነት ለማጥፋት ከግድያ ጀምሮ የትግራይ ተወላጆችን በተለያየ መንገድ ‘’ዲሞግራፊውን’’ ቀየሩት።  ከተለያዩ አካባቢዎች ህዝብን በመሰብሰብና በማስፈር  በሱዳን የተሰደዱ ስደተኞችን ከመመለስ ጀምሮ፤ ከጦሩ የተሰናበቱትን በመቶ የሚቆጠሩ እና ከተለያዮ የትግራይ ወረዳዎችን ይጨምራል። ኢኮኖሚውንም ተቆጣጠሩት። ስራ እየተመረጠ ለወያኔና መሰሎቹ ብቻ ተሰጠ። ዜጋው ከአፓርታይድ በከፋ ከምድር በታች ያለ ኢ-ሰባአዊ ሁሉ ተፈፀመበት።

አዲስ አበባ፤ የትላንቱ ኦህዴዲ የዛሬው ኦሮሙማብልፅግና ‘’አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ብቻ አይደለችም፤ ኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ማግኘት ይገባታል አለ::’’ አደረጋትም ዜጎች ልፍተውና ደክመው ያስገነቡትን ቤት በማን አለብኝ ለኦሮሙማ ተከታዩች አደሉት።

የአዲስ አበባ ህዝብ በልማት ስም ቤት ንብረቱ እየፈረስ እንደ አሮጌ ቁና የትም ተወረወረ ፤በምትኩ ተረኞቹ የኦነጋዊብልጽግናዎች ከየቦታው እየተጠረሩ ሁሉንም ነገር ተቆጣጠሩት፥፥ አዲስ አበባ ዜጎች ተወልደው ባደጉበት ባይተዋር ሆኑ። ወጣቶቹ ተምረው ስራ ማግኘትና ኑሮ መመሰረት ህልም ስለሆነባቼው መሰደድና በባዕድ አገር፡ መከራተት እጣ ፈንታቼው ሆኖ፤ ብዙዎቹ በሳአውዲ እስር ቤት የምድርን ስቃይ ሁሉ ይከፍላሉ።

የአዲስ አበባ ህዝብ በግልጽ በኢትዮጵያዊ ማንነቱና ለዘመናት በገነባው ማህበራዊ እሴት ላይ ጦርነት ታወጀበት፥፥ በወልቃይት እንደተደረገው ሁሉ በአዲስ አበባም ከሱማሌ ክልል ተፈናቀሉ የተባሉት ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ አሰፈሩበት። ይህም አልበቃቼው፤ በአንድ ቤት ውስጥ እስክ 170 የሚደርስ መታወቂያ ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ የእነሱ ተወልጆች በገፍ አደሉምርጫ”  አድርገን አሸነፍን አሉ።

በወልቃይት ወያኔ እንዳደረገው ሁሉ ኦሮሙማብልፅግና የከተማዋን ማንነት ለማጥፋት ከስም መቀየር ጀምሮ እስከ አዲስ ክፍለ ከተማ መፍጠር ድረስ ሄዱ። በከተመዋ ነርሱን ቋንቋ የማይናገር የስራም ሆነ የኢኮኖም ተጠቃሚ መሆን እንዳይችል በመንግሥት ደረጃ መዋቅር ዝርግተው ይሰራሉ። የኦሮሚያ ፍርድ ቤት  በዋና ከተማ ላይ በማቋቋም በፍትህ ላይ ተሳለቁ።  ገዥዎቻችን በድግስና በግብዥ እየተምነሸነሹ፡ አዲሰ አበቤ ግን በችግርየበይተመልካች’’ ሆኖ ይሰቃያል።

ወልቃይት፤ ወልቃይቶች በማንነታቸው ወያኔ ሲዘምትባቼው ጮሁ፣ ታሰሩ ተገደሉ ታገሉ በኢትዮጵያም ወያኔን የማስወገድ የትግል ፋና ወጊ ሆኑ ትግሉን አገር አቀፍ እንዲሆን ሰቆቃቼው በዓለም ዳርቻ እንዲሰማ ከፍ አድርገው ጮሁ ትግላቼው ፍሬ አፍርቶ ዛሬ ለነፃነት በቁ።

አዲስ አበባ አዲስ አበባሜ በማንነቱ ላይ በግልጽ ጦርነት እንደታወጀበት ሲያውቅ መታገል ጀመረ። በህዝቡ ያልተመረጠ ከንቲባ ሲሾምበት አጥብቆ ተቃወመ፥፤ ግን ወያኔዎች እንዳደረጉት ሁሉ የአዲስ አበባ ባለተረኞቹ  ኦሮሙማብልጽግናዎች ሰላማዊ ታጋዮችን ከብዙ ማገላታት በኋላ ወደ ዘብጥያ አወረዷቸው።  ከአንደ አመት ተኩል  እስር በኋላ   የትኛውን  የጦር ዕዝ እንደመቱ ባናውቅም፤  የወያኔ አድራጊፈጣሪና መሰሎቻቸው ሲፈቱ እነሱም ተፈቱ።  

ለግዜውም ቢሆን አዲስ አበባን ታጋይ አልባ ያደረጓት መሰላቼው። ወያኔንም ወልቃይቶችን የቻለውን ያህል ገሎና አሳዶ ታጋይ አልባ ያደረጋት መስሎት ነበር።ግን ታጋይ ይሞታል ትግል ግን አይሞትምናወልቃይቶች ገና ብዙ ተጋድሎ ቢጠባቅቸውም  በነጻነት ለመኖር በቁ። የአዲስ አበባ የአሁኑ ትግል የህልውና ትግል ነው::  ለአዲስ አበባ ህልውና መከበርና ስለ ፍታዊነት በሰለጠነና በሰላማዊ የጠየቁ ዜጎችን በግፍ አስሮ ሰላም አይኖርም። የአሁኑ የግፍና የአፈሳ እስር ደግሞ ህዝብን ለመታገል የበለጠ ቆራጥ ያደርገዋል እንጅ አያንበረከከውም።

የአዲስ አበባ ህዝብመዲናችን የማንም ሳትሆን የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ብሎም የአፍሪካ ነችናራስን በራስ የማስተዳደር የተፈጥሮ መብታችን አትከልክሉን ለዘመናት ከመላው ያአገሪቱ ክፍል በተውጣጡ ዜጎች የተገነባውን ማንንነት አትንኩብን! አክብሩልን! ከኢትዮጵያዊነይት ማማ አንወርድላችሁምበአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማችን አንደራደርም ! አለ እንጂ፣ የራሱ ያልሆነውን አልጠየቀም።

ለባለተረኛ ገዥዎቻችን የምናስተላልፈው መልእክት፤  በአሁኑ ግዜ አገራችን ከጦርነቱ ባልተናነሰ የኑሮ ውድነት እየተጠበሰው ነው።  ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ብሎ መከራና ችግሩን ሁሉ ችሎ አገሩን የሚያሰቀድመውን የአዲስ አበባ ህዝብ አትፈታተኑት። ትላንት ጎሰኝነትንና ጸረኢትይጵያዊነትን እንደ ጡጦ አጥብቶ ካሳደጋችሁ ወያኔ ተማሩ።  ምንም ይሁን ምንም ኢትዮጵያዊነት ለሁላችን መደሃኒትና መዳኛችን መሆንኑ አሁንም ከወያኔ ስህተት ተማሩ ! ብለን እንመክራለን።  አዲስ አበባ ለሁላችንም ትበቃለች። አቅፋ ደግፋ ትይዘናለች።  የአዲስ አበባ  ህዝብ አብሮና ተከባብሮ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መኖርን እንጅ፤ የአንድን ጎሳ የበላይነት የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም። ለዚህም ነውአዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ናት!” የምንለው። ‘’አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው! ’’ የምንለው:: ስለዚህም ህዝብ ለታላቋ ኢትዮጵያ ሲል ቅድሚያ የሚሰጠው  የአገርና የህዝብ አንድነት ስላለ እንጅ በእናንተን የመንደርተኝነትን አገዛዝና ፓለቲካ ሊቀበል ቀርቶ መፈጠራችሁንም ባያውቅ ይመርጥ ነበር።  መገንዘብ ያለባችሁ ህዝብ ከእንናተ ከገዥዎቻችን እጅጉን በበለጠ አገሩን ያስቀድማል። እናም  ነገዛሬ ሳትሉ በህገወጥ መንገድ ያሰራችኋቸውን ወግኖቻችን ፍቱ።   ጨቋኝ ጎሰኛም ሆነ የነጻነት ታጋይ ከወልቃይት ይማር።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

 

 

´

Filed in: Amharic