>

የባልደራስ ድጋፍ ሰጭ በሰሜን አሜሪካ የአዲስ አበባን የጅምላ እስር አወገዘ!

የባልደራስ ድጋፍ ሰጭ በሰሜን አሜሪካ የአዲስ አበባን የጅምላ እስር አወገዘ!


የባልደራስ ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ ፣ “ግለሰቦችን በማሰር በደም የተፃፈ የኢትዮጵያን ታሪክ ማጥፋት አይቻልም”  በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተፈፀመውን የጅምላ እስር አውግዟል፡፡
ማህበሩ ባወጣው መግለጫ፣ “የሰሜን አሜሪካ ባልደራስ ድጋፍ ማህበር፣ በዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰትና እስር በጥብቅ ያወግዛል፤ የታሰሩ ወገኖቻችንንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር በአስቸኳይ እንዲፈቱ ያሳስባል፤ በተጨማሪም በመላው አለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አፈናውን እንዲያውቀው ዘመቻ የምንጀምር ስለሆነ፣ የዘመቻው አካል በመሆን በእስር ላይ ለሚገኙት ድምጽ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ”
Filed in: Amharic