>

የተዛባ ታሪካችን መጠገኛው አዲስ አበባ ናት!  (ስንታየሁ ቸኮል)

የተዛባ ታሪካችን መጠገኛው አዲስ አበባ ናት! 

ስንታየሁ ቸኮል

 

“.. ይቺን ከተማ ሙሉ ለሙሉ በእጃችን መቆጣጠር ለረጅም ጊዜ ሥልጣናችን የምናስጠብቅበት መሳሪያ ነው የሚል ግምገማ  ኦህዴድ ብልፅግና አለው። ይህን አቋሙን ለማስፈፀም የያዘዉ ታክቲክ የፖለቲካ ዋነኛ አጀንዳ በሆነችው ርዕሰ መዲና የአዲስ አበባን ሕዝብ “በሸኔ ” ተከበብክ  በፍርሃትና እስር ማሸበር በኑሮ ውድነትና መሰል ችግሮች አንገቱን ደፍቶ ተረኝነትን አምኖ እንደ ሕግ እንዲቀበል እየተሰራበት ነው።
ለዚህ ተመጣጣኝ መልስ ፍርሃትን አሽቀንጥሮ የሚጥል ትውልድ ይፈልጋል መደራጀት ሕዝባዊ ትግሉን ማፋፋም ይገባል። የአዲስ አበባ ታሪክና የማንነት ውቅር ወደኃላ መለስ አድርጎ ያለመሽኮርመም ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ እንዳመጣጡ ማስተናገድ ያስፈልጋል።
አፍጥጦ የመጣ ስግብግብ ቡድን የኃይል ሚዛን በሚቀይር ትግል መከባበር እንጅ መለማመጥ ከአንገት በላይ ፍቅር አስፈላጊ ሆኖ አይታየኝም። በዙሪያህ ከበብኩ የሚለውም በሌላው ተከቧል የቆምክበት መሬት ያንተ ካልሆነ የሱም አይደለም። በጥያቄ እንጅ በስጦታ የሚበረከት መብትና ነፃነት የለም! አዲስ አበቤ …
Filed in: Amharic