>

በመተሃራ በኦነግ ጦር የተገደሉ ወጣቶች በጅምላ በአንድ ጉድጓድ አልጌ ላይ ተቀብረዋል..!!! (አሻራ ሚዲያ)

በመተሃራ በኦነግ ጦር የተገደሉ ወጣቶች በጅምላ በአንድ ጉድጓድ አልጌ ላይ ተቀብረዋል..!!!
አሻራ ሚዲያ

 

በፈንታሌ ወረዳ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በስርዓቱ ውስጥ ባሉ የዘር ማጥፋት ተባባሪዎች የተጨፈጨፉ አማራዎች ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ፤ ዘጠኙ በጅምላ በአንድ ጉድጓድ አልጌ ላይ ተቀብረዋል።
– በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በስርዓቱ ውስጥ ባሉ የዘር ማጥፋት ተባባሪዎች መጋቢት 8/2014 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የተጨፈጨፉ አማራዎች ስርዓተ ቀብር ተፈጽሟል።
ዘጠኙ በግፍ በጥይት የተገደሉ ወጣቶች በአልጌ ቀበሌ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን በጅምላ በአንድ ጉድጓድ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
ንጹሃን ወገኖች በሚጨፈጨፉበት ወቅት የኦህዴድ የፈንታሌ ወረዳን አስተዳዳሪ አቶ ፍሬዘርን ጨምሮ የወረዳው የፖሊስ ኃላፊ እና ሌሎች አመራሮች እንዲደርሱላቸው ተጎጅዎች የተማጸኑ ቢሆንም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ለንጹሃን የድረሱልን ጥሪ ምላሽ ያልሰጡት ከጥቃቱ በስተጀርባ እጃቸው ስላለበት ሊሆን እንደሚችልም ተገልጧል።
በግፍ ተገድለው ስርዓተ ቀብራቸው መጋቢት 9/2014 ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ከተቀበሩት መካከል:_
1) ዘሪሁን ደምሴ፣
2) ጌትነት ታምራት፣
3) ደባልቄ እሸቱ፣
4) ተስፋ ጽዮን ዳንኤል፣
5) ልዑሰገድ መለሰ፣
6) ታደለ ኤሊያስ እና
7) ቢኒያም ወንዜ ይገኙበታል።
ከተገደሉት መካከል 7ቱ ከአማራ ሲሆኑ ታደለ ኤሊያስ እና ተስፋ ጽዮን ዳንኤል የደቡብ ክልል ልጆች መሆናቸው ተገልጧል።
ከ8 በላይ አማራዎች የቆሰሉ ሲሆን እነሱም ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።
ከቆሰሉት መካከልም:_
1) አቶ ድንገቶ የተባሉ አባት መንታ ልጆች ተገድለውባቸዋል።
እድሜያቸው ከ18 እስከ 25 ዓመት ይሆናል።
2) አንድ የ10 ዓመት ልጅ፣
3) ሀብታሙ አያሌው፣
4) ስንታየሁ ፣
5) ተረፈ፣
6) ኤፍሬም እና
7) አያሌው የተባሉ ንጹሃን ይገኙበታል።
Filed in: Amharic