>
5:33 pm - Thursday December 6, 1314

500 ቀናት....!!! (ኦሃድ ቢንአን)

500 ቀናት….!!!

ኦሃድ ቢንአን

 


አገራችንን ትልቅ ዋጋ ያስከፈላት ቴድሮስ አድሓኖም እና ጓዶቹ የለኮሱት ጦርነት እነሆ 500ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ ወያኔና ጭፍራዎቿ ይህን ቀን የሚዘክሩት እንደተበደለ ጭቁን ድርጅት እንጂ ሃገርን ለ27 አመታት የመዘበረ፣ በሕዝቦች መካከል መርዝ የረጨ እና በወራዳ ብሔረተኝነት ዘቅጦ የገዛ አገሩን መከላከያ የጥይት እራት የቀለበ ድርጅት እንደሚሆነው አይደለም፡፡
በጦርነቱ ሶስቱ ሰሜናዊ ክልሎቻችን ቢጎዱም የትግራይ መከራ ግን ከሁሉም የከፋ መሆኑን አስረጅ አየስፈልገውም፡፡ አሳዛኙ ጦርነትና እና መዘዞቹ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህይወትን ዘርፎናል፡፡ እንደ ሃገር ትልቅ ውድቀት እና ገበና መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በታሪካችንም ይህን ያክል ሕይወት ያጣንበት የጦርነት ምዕራፍ ገጥሞን አያውቅም፡፡
ስለሞቱት ሁሉ ግድ ይለናል፡፡ በሶስቱም ክልሎች የተገኙት እና የጦርነቱ ምድጃ እላያቸው ላይ የተለኮሰባቸው ወገኖቻችን አሰቃቂ ምዕራፎችን አይተዋል፡፡ የ30ው አመታት የህወሓት የፖለቲካ መስመር ዳፋ መሆኑን ለነቴድሮስ አድሓኖም ማስረዳት አውቆ የተኛን መቀስቀስ ነው፡፡ ዛሬ እነሱ የፈጠሩት ክፋት አጻፋዊ ጭካኔ ይዞ ሰዎች በቁም የሚቃጠሉበት ምዕራፍ ላይ ተደርሷል፡፡
እንደ አንድ ዶክተር የህይወት ክቡርነትና ቅድስና፣ አይነኬነትና ልዩ ዋጋ ሊሰጠው እንደሚገባው ቢያውቅ ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን የራሱን ወታደሮች በአለም አቀፍ አሸባሪዎች የማስወጋት ድፍረት ያለው ዝቃጭ ስለ ሰሜን ዕዝ መከላከያ ወታደሮች ምን ሊሰማው ይችላል?
ቴድሮስ አድሓኖም ይህን ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን ስለሌሎች ኢትዮጵያውያን ሰለባዎች አንድም ነገር ትንፍሽ ሳይል የቆየውና የኮቪድ-ደባቂው ዳይሬክተር ሁኔታ አስገራሚነት እና እንዴት እንደሱ አይነት የነቀዘ ሰው እዛ መስሪያ ቤት ውስጥ ዕድል ማግኘቱ ማየት አለም የፍትሕ መድረክ አለመሆኗን ማሳያ ሆኖናል፡፡
ስለ ትግራይና ተጋሩ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ግድ ይለናል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ሆኖ አያውቅም፡፡ ነገር ግን በነቀዘ ብሔረተኛ አፓርታይዳዊ ፍልስፍና ተገንዞ፣ ለመውጣት የሚያደርገው ጥረት ከግንዛቤው አቅም በላይ ሆኖበት፣ ያልነበረ የጅብ ወለደ ጠላት (አማራው) ተስሎለት፣ መከሰት ለሌለበት ጦርነት መኖር ያለባቸውን በኩራት ልጆቹን እየማገደ መኖሩ በህወሓት ክፋት ተሸፍኖ 500 ቀናት ተቆጥረዋል፤ ቴድሮስ አድሓኖም ኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ለትግራዩም ለአማራውም እኩል ስሜት እንዲኖርህ ያደርጋል፤ ነገር ግን አንተና የክፋት ባልደረቦችህ ያን አይነት እይታ የመጎናጸፍ ዕድሉ የላችሁም፡፡ ላንተ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በኮቪድ እንዳስጨረስካቸው የአለም ሕዝቦች አንድ ሆነው ሊታዩህ ይችላል፤ ለኛ ግን ሁሉም ወገኖቻችን ናቸው፤ ጥረታችንም ጓዶችህ የፈጠሩት እንክርዳድ ድርጅት በጭፍን ርዕዮተ አለም አዲስ አበባን ተቆጣጥሮ ኢትዮጵያን የመከራ ደብር ለማድረግ ያደረጋችሁትን ጥረት ኢትዮጵያዊው እንዳከሸፈው ሁሉ ክፋታችሁን ለማክሸፍ ነው፡፡
በዚህ ሁኔታ የህወሓት ቀቢጸ-ተስፋ እርምጃዎች ብዙዎች ወገኖቻችንን የህወሓትን በደል አልፈው ከጀርባ ያለውን የትግራይን ሕዝብ መከራ ለማገናዘብ አቅም እንደሚፈታተናቸው ማየቱ ሌላው ብሔራዊ ገመናችን ቢሆንም አሁን ወደ አማራ ክልል ፈልሰው የመጡትን ተጋሩ ሕዝቡ የሚችለውን እያደረገ እየተንከባከባቸው መሆኑ የህወሓትን የዘመናት የጥላቻ ዘመቻ የሚንድ ነው፡፡
ቴድሮስ አድሓኖም የምትገርም ምሁር ነህ፤ በዚህ የዲግሪዎችህና አሁን በየአገሩ ገንዘብ እየከፈልክ የምትሰበስባቸው የክብር ዶክትሬቶች የቅሌት አክሊልህ መሆናቸውን ልብሕ ያውቀዋል፡፡ የዛሬ 500 ቀናት በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች በተጠንቀቅ በመጠበቅ ላይ የነበሩት ወገኖቻችን የትግራይን ገበሬ በማገዝ ሰብል በመሰብሰብ እና አንበጣ በመከላከል ሲደክሙ የነበሩ ወታደሮቻችን ደማቅ የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው ወደ አልጋዎቻቸው ሄደው ለየድካም ማስወገጃ የናፈቁትን እንቅልፍ ሳያገኙ ለዘላለም እንዲያሸልቡ የተደረገው አብረዋቸው በዋሉ የሠራዊቱ አባሎች ጓዶቻቸው ነበር፡፡ ወታደር ወታደርን ዘርና ቋንቋ መርጦ ግድያ የፈጸመበት የውርደት ቀን ነበር፡፡ ይህ የህወሓት ተግባር ታሪክ የማይረሳው የውድቀት ማሳያ ሆኖ ይቀራል፡፡
ቀጣዩ የማይካድራው ጥቃትም ሰዎች በቋንቋቸው እና በ“ብሔራቸው” ተመርጠው የተጨፈጨፉበት ወቅትም የ500 ቀናት ቁስላችን ነው፡፡ ህወሓት ማንነቱን እና ምንነቱን ያሳየበት ይህ ታሪካዊ የገበና ቀን ዛሬ 500ኛ ቀኑን ደፍኗል፡፡ ቴድሮስ አድሓኖም ጄኔቫ ቁጭ ብለህ ወደ ዩክሬይን ፊቱን ያዞረውን የስፖንሰሮችህን ትኩረት ለመሳብ “500 ቀናት” የሚል ዘመቻ እያስተባበርክ መሆንህን ማየት በጣም ያስገርማል፡፡ ስለ ትግራይ ህዝብ መቆርቆርህ ባልከፋ ነበር፡፡ ነገር ግን ምን አለ አንዴ እንኳን የወያኔን ድርጊት ማውገዝ ተሳነህ? ስብዕና የለህማ፤
ያንተን የወያኔን ግፍ አለማውገዝና ከእውነት ሳትታረቅ የአማራ እና የአፋር ሕዝቦች ያስተናገዱትን መከራ ሳታወግዝ 500 ቀናት መቆጠራቸውን ሳስብ እገረማለሁ፡፡ የት ሄጄ ላልቅሰው ያስብላል፡፡ ሴኮ፣ ደብረጺዮን እና ጻድቃን ያመኑትን ግድያ፣ አለም ያረጋገጠውን ዘር ጭፍጨፋ ቁጭ አድርገህ “500 ቀናት” ስትል መስማት ለማንነታችን ያለህን ንቀት ያሳየናል፤ ዳሩ ከእንዳንተ አይነቱ ዶር ፍራንክስታይን ምን መጠበቅ ይቻላል?
የሰሜን ዕዝ ጀግኖችን የታረዱበትን እና የማይካድራ ንጹሃን የተጨፈጨፉበትን “500ኛ ቀን” የምንዘክረው የአንተን እና ግብረ አበሮቻችሁን ክፋት እያሰብንና የፍትህ ቀንን እየናፈቅን ነው፡፡ አንረሳውም፤ አንድ ቀን ሁላችሁም ለፍርድ ትቀርባላችሁ፤ ለጊዜው በስፖንሰሮችህ ክንድ ተሸፍነህ የምትኖር ቢመስልህም አንድ ቀን ፍትሕ ብርሓኗን ታሳርፍብሃለች፤ እንደማንላቀቅ እና የሞቱትን ወገኖቻችንን ደም ከእጆችህ እንደምንቀበልህ አትርሳው፡፡
እንደናዚ ወንጀለኛ እየተሽሎኮለክ ለመኖር እንደምትዘጋጅ ነፍስህ እንደምትነግርህ ግልጽ ነው፤ ሌሊት ተኝተህም ስለምትኖርበት የምሽግ ቤት አሰራር መላ መምታት እንደጀመርክ ለብልህ አይነግሩም፤ “ሓጢያተኛ ሳያሳድዱት ይሸሻል፤” አደለ ነገሩ፤ ነገር ግን የትም ሄደህ የትም አታመልጥም፤ ፍርድህን ትቀበላለህ፤ እስከዛው ከውርደትህ ጋር ኑር፤
Filed in: Amharic