>

ኦነግ/ሸኔ የ100 ዓመት ሽማግሌን በአሰቃቂ ሁኔታ በቤታቸው ውስጥ ገደለ...!!!  (ኢሰመጉ )

ኦነግ/ሸኔ የ100 ዓመት ሽማግሌን በአሰቃቂ ሁኔታ በቤታቸው ውስጥ ገደለ…!!!
 ኢሰመጉ 

 

 የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት የተማሪዎችን ስነ ልቦና ጎድቷል…!!!
/
በፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም የተመሠረተው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣  መጋቢት 13/2014 ዓ.ም  ባወጣው መግለጫ፣  የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሽላቸው መግለፃቸውን ገለፀ፡፡ ውጤቱ የተማሪዎቹን ስነ ልቦና የጎዳ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ተገቢውን ማብራሪያ እንዲሰጥና የእርምት እርምጃ እንዲወስድም ጠይቋል፡፡
እንዲሁም፣ በፈንታሌ ወረዳ፣ አልጌ ቀበሌ ውስጥ ልዩ ቦታው መልቲ ፋብሪካ አካባቢ መጋቢት 9/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ወጣቶች ተገድለዋል ሲል ኢሰመጉ ገልጿል፡፡
እንደሚታወቀው፣ የአካባቢው ነዋሪ ጥቃቱ የተፈፀመው በኦነግ ሸኔ መሆኑንና ብሔር ተኮር እንደሆነም ይናገራል፡፡ ኢሰመጉ ባይገልፀውም፣ በፈንታሌ በተፈፀመው ጥቃት 9 ሰዎች በጥይት ተደብድበው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ 7ቱ አማሮች፣ 2ቱ የደቡብ ተወላጆች እንደሆኑ በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ስርዓተ ቀብራቸውም በአንድ ጉድጓድ ውስጥ በአልጌ ተፈጽሟል፡፡ ህይወታቸው በግፍ የተቀጠፉት ፡-
1.      ዘሪሁን ደምሴ
2.      ጌትነት ታምራት
3.      ደባልቄ እሸቴ
4.      ተስፋጽዮን ዳንኤል
5.      ልዑልሰገድ መለሰ
6.      ታደለ ኤልያስ
7.      ቢኒያም ወንዜ ናቸው፡፡
እንዲሁም፣ ኢሠመጉ ባወጣው ሪፖርት ላይ፣ በምዕራብ ሸዋ መጋቢት 9/2014 ዓ.ም፣ አርብ ቀን፣ ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት፣ አምቦ ወረዳ፣ ኢላም ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ቄስ አምደጽዮን የተባሉ የ55 አዛውንት እና አቶ ተፈራ ኃይሉ የተባሉ የ100 አመት እድሜ ባለፀጋ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን ማረጋገጡን አትቷል፡፡ በሌላ በኩልም፣ በምዕራብ ወለጋ በርካታ ሕዝብ መፈናቀሉን፣ ንፁሐን መሞታቸውንና ንብረት መውደሙን ገልጿል፡፡
በመጨረሻም ባቀረበው ጥሪ፣ የፌደራል እና የሚመለከታቸው የክልል መስተዳድሮች በታጣቂዎች እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ፣ እንዲሁም የዜጎችን በሕይወት የመኖር እና የአካል ደህንነት መብቶችን እንዲያስከብሩ ጠይቋል፡፡
Filed in: Amharic