>

ፖለቲካችን ከድጡ ወደ ማጡ ለመጓዙ በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ የተደረገው እስር አይነተኛ ማሳያ ነው! (ጌታቸው ሽፈራው)

ፖለቲካችን ከድጡ ወደ ማጡ ለመጓዙ በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ የተደረገው እስር አይነተኛ ማሳያ ነው!
ጌታቸው ሽፈራው

~ፓርላማና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሆነው ሕዝብን የሚሳደቡ በበዙበት ታምራት ሀሳቡን መግለፁ እንደ ስድብ ተቆጥሮ አሁንም በእስር ላይ ነው።
~ከፍተኛ የአገር ክህደት ወንጀል የሆነውን መከላከያ ሰራዊትን ያህል በመምታት የተሳተፉ ሰዎች ተፈትተው ታምራት ነገራ ግን በእስር ላይ ነው።
~ጊዜያዊ አዋጅ ተነስቶ በጊዜያዊ አዋጅ የታሰረው ታምራት ነገራ አሁንም በእስር ላይ ነው!
~በርካታ ንፁሃንን ያስጨፈጨፉ ለፖለቲካው ወዘተ ተብለው ተፈትተው፣ “ንፁሃን ለምን ይጨፈጨፋሉ” ያለው ታምራት ነገራ አሁንም እስር ላይ ነው።
~ፓስተር ተብለው ዩቱዩብ ተከፍቶላቸው ሕዝብን የሚሰድቡ አሉ። አንደኛውን ክልል ለማበጣበጥ ኦሮሚያ የተደበቁ ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን። ታምራት ስለ ኢትዮጵያ ስለጮኸ እስር ላይ ነው።
~የታሰረበት መንገድ ደግሞ አሳዛኝ ነው። አዲስ አበባ ለማሰር አልበቃ ብላ ኦሮሚያ ወስደው አሰሩት።  የግል እስረኛ አደረጉት። ስልጣን በዚህ ደረጃ መጠቃቂያ፣ ንፁሃንን ማጥቂያ ሆነ።
ይህ በታምራት ላይ የተደረገው ግፍ ሁሉ ነገ በማንም የሚደርስ ነውረኛ ተግባር ነው። በማንኛውም ሀሳቡን በሚገልፅ ላይ ሁሉ ይደርሳል።
በርካታ የታሰሩ ሰዎች አሉ። በሀሰት ሰበብ ፈልገው ያሰሯቸው የአዲስ አበባ ወጣቶች አሉ። ምንም ሳያደርጉ ለማስፈራሪያ የታጎሩ አሉ። በዚህ ወቅት የታምራት ነገራን ያህል እጅግ አሳፋሪ እስር ግን የለም። የታምራትን እስር መቃወም ለሁሉም ፍትሕ መጠየቅ የሚሆነው የገዥዎቹ የነውር ጣሪያ የታየበት ስለሆነ ነው።
Filed in: Amharic