>

ያየሁት ሁሉ አይቅርብኝ ባዩ ብልጽግና እና ምእራባውያኑ...!!! (ታደለ ሲሳይ)

ያየሁት ሁሉ አይቅርብኝ ባዩ ብልጽግና እና ምእራባውያኑ…!!!
 
የታጨደው ስንዴ!
——————-
ለመሪዎች ወንበር የታጨደው ስንዴ
እኩል ነው መርምሩት ከሞተው ዘመዴ።
ቶሎ እንደታጨደው እንደስንዴው ሁሉ
ለመሪዎች ወንበር አልቋል ሰው በሙሉ።
በዚህች በኔ ዘመን በዚች በኔ ዓለም
ለመሪዎች ወንበር ያልታጨደ የለም።
ታደለ ሲሳይ
 
*…. አንዱ ሰርቶ አልምቶ ይበላል የኛዎቹ ገለው፣ አፈናቅለው ፣ጨፍጭፈው ፣አሳደው በማሳ ውስጥ ዘና ፈታ ይላሉ…!!!
የመጀመሪያው ፎቶ በቀን ሶስቴ  ከመመገብ አልፈው በሙሰኛና ማህይማን ፖለቲከኞች ምክንያት ችጋራም የሆኑ አገራትን የሚረዱ ምእራባዊያን  የተነሱት ሲሆን:-
:
ወግ አይቀር ሲዳሩ ማልቀስ እንዲሉ…2ኛው ፎቶ ደግሞ በቀን አንዴ መብላት ብርቅ የሆነባት፤ በ21ኛው መክዘ ሰው በጎሳ ፖለቲካ እርስበርስ በሚተራረድባትና ዳቦ ብርቅ ሆኖ ህጻናት በርሃብ በሚረግፉባት የአንዲት መናኛ ዳቦ በ10 ብር፤ ዘይት 1000 ብር የሚሸጥባት #ክስረት ፓርቲ መባል ሲገባቸው “ድርጊተ ክፉ በስም ይደፉ” እንዲሉ ራሳቸውን “#ብልጽግና ” ያሉ የእኛይቱ ሂፖክራት መሪዎች ናቸው…።
:
አንዱ ሰርቶ አልምቶ ይበላል የኛዎቹ ገለው፣ አፈናቅለው ፣ጨፍጭፈው ፣አሳደው በማሳ ውስጥ ዘና ፈታ ይላሉ..።
:
የህጻናት ርሃብና እልቂት፣ የንጹሃን መታረድ፣ ደንታ ያልሰጣችሁ እናንተ አረመኔዎች እግዚአብሔር ይመለከታል የግዜ ጉዳይ ነው በቅርቡ ዋጋ ትከፍላላችሁ !!!
Filed in: Amharic