>

መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማድረግ እየተሯሯጡ ነው...!!!   (መ/ር ኢንጅነር ታሪኩ አበራ)

መፈንቅለ ፓትርያርክ ለማድረግ እየተሯሯጡ ነው…!!!
  መ/ር ኢንጅነር ታሪኩ አበራ

 

  ★…. አቡነ ዮሴፍና ዳንኤል ክብረት ከመንግሥት ጋር ሆነው በአቡነ ማትያስ ላይ ሕዝብ  ሊያሳድሙ እየተንቀሳቀሱ ነው…!
 
★ በሀገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን አጥብቃችሁ ተቃወሙ ይህ አስነዋሪ ተግባር ቤተክርስቲያንን የሚያዋርድ ሃይማኖታችንን የሚያሰድብ አስጸያፊ  ድርጊት ነው…!
ተጨባጭ መረጃ አግኝተናል።ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ከመንበረ ፕትርክናቸው አንስተው ወዳልታወቀ ሥፍራ በግዞት  በመውሰድ በእርሳቸው መንበር ላይ በመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሌላ ፓትርያርክ ለመሾም ኮሚቴ አዋቅረው እየተንቀሳቀሱ ነው።ኮሚቴውን የሚመሩት የአድማው ጠንሳሾች ዳንኤል ክብረትና አቡነ ዮሴፍ ናቸው።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተለያየ ጊዜ የመንግሥትን ሕገ ወጥ ድርጊት ፊትለፊት በመቃወማቸውና መንግሥት እንዳሻው ሊያዛቸው ስላልቻለ በመንግሥት በኩል ፓትርያርኩን ከሕዝብ ጋር የሚያጣላ ፕሮፓጋንዳ በሚዲያዎች በኩል በከፍተኛ ደረጃ ለመክፈት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።በተከፋይ አክቲቪስቶቻቸውና በሌሎችም ሶሻል ሚዲያ ኔትወርኮች በመታገዝ በፓትርያርኩ ላይ የሥም ማጥፋት ዘመቻ ለመክፈት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።
የተወሰኑ አካላት ደግሞ ከመንግሥት በጀት ተመድቦላቸው በአማራ ክልል በመንቀሳቀስ ሕዝቡን በፓትርያርኩ ላይ በአመፅ ለማስነሳት ከፍተኛ ዕቅድ ይዘው ሊንቀሳቀሱ በዝግጅት ላይ ናቸው።
በጠቅላይ ቤተክህነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው በዝርዝር የያዟቸውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ አባቶችንና የመምሪያ ሠራተኞችን ያለምንም ምክንያት ወደ እሥር ቤት ለማስገባት ከመንግሥት ጋር ስምምነታቸውን ጨርሰዋል።
በሀገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ይህንን እጅግ አሳፋሪና አስነዋሪ አመጽ በከፍተኛ ድምፅ ልንቃወምና ቅድስት ቤተክርስቲያንን ልናስከብር ይገባል።እንደ አባ ዮሴፍና እንደ ዳንኤል ክብረት ያሉ የዲያብሎስ ማደሪያዎች ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በእስላምና በፕሮ*ቴስታንት ፊት እያወረዷትና እያሰደቧት ስለሆነ እነዚህን ርካሽ ሰዎች በአንድነት በመቃወም በአካልም፣በስልክም፣ በጽሑፍም ተቃውሟችንን ልንገልጽላቸውና አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ በመውሰድ  ቅድስት ቤተክርስቲያንን ልናስከብር ይገባል።
Filed in: Amharic