>

ስለ HR 6600....!!! (አሳዬ ደርቤ )

ስለ HR 6600….!!!

አሳዬ ደርቤ

*….. በእውቀትም በመረጃም በማስረጃም አስረድቷል ሰምቶ መረዳት የእኛ ፋንታ ነው።  ከዛ ውጪ በካድሬ መንጫጫት የሚለካው የሀገር ፍቅር ሳይሆን የአድር ባይነት ልክ ነው!
 
የአማራ ግፉዓን ድምጽ ለመሆን ሳስብ የመናገር ነፃነት ስለተሰጠኝ ሳይሆን ከአቶ ደመቀ ወንበር ይልቅ የአሳምነው ጽጌ መቃብር ምቹ መሆኗን ተረድቼ ስለሆነ የትኛውም አይነት ዛቻ አያሰንፈኝም።
እናም እንደ አንድ የአማራ ተወላጅ HR-6600ን እንዲቃወም ከፈለጋችሁ የሚከተሉትን ጥያቄዎቼን መመለስ ይገባችኋል።
➔በሕይወት የመኖር መብታቸውን ማስከበር ሲገባችሁ በትሕነግ፣ በኦነግና በጉምዝ ታጣቂ ሲገደሉ የኀዘን መግለጫ ነፍጋችሁ፣ ከጋዜጠኞች ካሜራ ደብቃችሁ፣እልቂታቸውን በሰበር ዜና ሸፋፍናችሁ… በዶዘር በቀበራችኋቸው ዜጎች ሥም የአማራን ሕዝብ ይቅርታ እንዲትጠይቁ፥
➔የኦነግ ሸኔ አመራር ሆነው መንግሥት መር ጭፍጨፋ ይካሄድ ዘንድ መንገድ ሲጠርጉ የከረሙ የብልጽግና አመራሮች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ፤
➔እነ ጌታቸው ረዳን የማደን ተግባር በአዲስ መልክ እንዲጀምር፤
➔ የትምህርት ውጤታቸው እንዲበላሽ የተደረገባቸው የአማራ ተማሪዎች ውጤት ተስተካክሎ ይቅርታ እንዲጠይቁ፤
➔የጦር መሳሪያ ግዢ ልንከለከል ነው ከሚል ለቅሶ በፊት “ኢመደበኛ ሃይል” በሚል ፍረጃ በድሮን የምትዝቱበት “ፋኖ” ከአማራ ልዩ ሃይልና ሚኒሻ ጋር ላደረገው ተጋድሎ እውቅና እንዲሰጠው፤
➔ወደ አገራቸው ከተጠሩ በኋላ በክህደት አርጩሜ ተገርፈው የተባረሩ ዲያስፖራዎች ይቅርታ እንዲጠየቁ፤
➔ማሳ ለማሳ በመዞር ፈንታ የተራቡ ዜጎችን እንዲትጎበኙና የእለት ጉርስ እንዲታደርሱ እጠይቃለሁ።
ከዚህ ውጭ ግን ፋኖን በኢመደበኛ ሃይልነት የፈረጀ ሃይል “ጥይት መግዛት ተከለከለ” ብዬ የምጮህበት አፍ የለኝም።
Filed in: Amharic