>

ሃሃሃሃሃሃሃ... የኢሳት ጋዜጠኞች ከኢሳት ጋር መለያየታቸውን ገለጡ!!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ሃሃሃሃሃሃሃ… የኢሳት ጋዜጠኞች ከኢሳት ጋር መለያየታቸውን ገለጡ!!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እግዚአብሔር ያሳያቹህ Live ወይም  የቀጥታ ስርጭት ባልሆነ ወይም ተቀርጾ በሚቀርብ የኢሳት ዝግጅት ላይ ነው እንግዲህ ኢሳትን ወይም ቦርዱን እንደጉድ እያብጠለጠሉና እያወገዙ መግለጫ በመስጠት “ከኢሳት ጋር ተጣልተናል፣ ሌላ ‘ኢሳት ኢንተርናሽናል!’ የሚባል ሚዲያ ልንመሠርት እየተንቀሳቀስን ነውና እርዱን!” ብሎ መጠየቅን፣ “እስከዚያው ድረስ ግን ዕለታዊ ፕሮግራማችንን በባላገሩ ቴሌቪዥን ተከታተሉን!” ብሎ በተጣሉት ኢሳት ቴሌቪዥን ላይ መግለጫ መስጠትን የመሰል ቂልነት የተሞላ የሕዝብን ንቃተ ሕሊና በእጅጉ የናቀን የእነ መሳይ መኮንንን መግለጫ እንዴት አያቹህት???
ጋዜጠኞቹ ምክንያት ብለው ካቀረቧቸው ምክንያቶች ደግሞ፦ 
* በእኛ ስም ከተለመነው 250 ሽህ ዶላር ግማሹን ለኢዜማ ሊሰጥብን በመሆኑ፣
* ኢሳት በአሜሪካ የግንቦት7/ኢዜማ ፓርቲ ባለቤትነት የተመዘገበ በመሆኑ፣
* ደሞዛችን በመቀነሱ የመሳሰሉት አስቂኝ ምክንያቶች ናቸው!!!
እኔ የምለው ከመርሕ፣ ከእውነት፣ ከሕዝብ ጋር ተጋጭተው ወይም ፊት ለፊት ተላትመው፣ ከጋዜጠኝነት ሞያዊ አሠራር ሥነምግባርና ኃላፊነት ውጭ በሆነ መንገድ ወይም ሚዛናዊነትን ፈጽሞ ባልጠበቀ መልኩ አሸባሪውን ብልጽግናን የፋና እና የዋልታ ጋዜጠኞችን እንኳ በእጅጉ ባስናቀ መልኩ አደግድገውና ወገባቸውን አስረው፣ በጣም ነውረኛና ኢሞራላዊ በሆነ መንገድ የሚያገለግሉ ሰዎች ኢሳት የኢዜማ/ግ7 ሆኖ በአሜሪካ የተመዘገበ ጣቢያ መሆኑን ማወቃቸው እንዴት ፈጽሞ ሊውጡት የማይችሉት ሊሆንባቸው ቻለ???
ከለውጡ ድራማ በፊት እነኝሁ ጋዜጠኞች ኤርትራ ድረስ ወርደው ዘገባ ሲሠሩ ማንን ያገለገሉ መስሏቸው ነበር እንዲያ በተጋዳይ ስሜት ኢሳትን ሲያገለግሉ የነበሩት???
ወይ አለማፈር እናንተየ በጣም እኮ የሚገርም ነገር ነው!!!
ይሄ ሁሉ የጋዜጠኞቹ ማደግደግ ደግሞ “ከኢዜማ ይልቅ እኛ ለብልጽግና ፍጹም ታማኝ ነን!” ለማለት መሆኑ ነው ደግሞ የእነኝህ ሰዎችን ወራዳነትና ቆሻሻነት እጅግ አስከፊ የሚያደርገው!!!
የገረመኝ ነገር ደግሞ ጋዜጠኞቹ ከሰጡት መግለጫ በኋላ በውይይታቸው “ቦርዱ የቢሮ ኪራይ መክፈል በማቆሙ አከራዮቹ አውጥተው ሊጥሉን በመሆኑ፣ የሳተላይት ኪራይ መክፈል ስላቆሙ ነው ይሄንን መግለጫ ያወጣነው!” ብለው ትክክለኛውን ምክንያት እየተናገሩ መልሰው ደግሞ ኢሳትን ለመልቀቃችን ምክንያቶቻችን እነዚህ ናቸው ብለው ከላይ የጠቀስኳቸውን ምክንያቶች መጥቀሳቸው ነው!!!
አየ እነ ቀልማዶ!!!
የእነዚህ ወራዶች መጨረሻ እንዲህ መሆኑ እንዴት አስደሰተኝ መሰላቹህ!!! ምድረ ወራዳ ሁሉ ገና ካርቶን ተሸካሚ ትሆኛለሽ ማን ይረዳሻልና ነው “እርዱን ሌላ ሚዲያ ልንመሠርት ነው!” ብለሽ ዓይንሽን በጨው አጥበሽ ለፀረ ሕዝቡ አሸባሪ አገዛዝ እያሽቃበጥሽ በየዕለቱ የምታቃጥይውን ሕዝብ ሳታፍሪ “እርዱን?” የምትይው እነ ወራዶ???
የሸፍጠኛውን፣ የሴረኛውን፣ የመሠሪውን የወያኔ/ኢሕአዴግን ኢሳቶችን ያጃጃለና በውሸት ሽኩቻ የተጣሉ አስመስሎ እንዲተውኑ በማድረግ ኢሳትን የማክሰም ወይም የመዝጋት ቴክኒክ ግን ሳላደንቅ አላልፍም!!!
ኢሳት ሕዝብን ክዶ ለአገዛዙ ሲያደገድግ ይሄንን ነበር የተናገርኩት “አያዋጧቹህም ከሕዝብ ጋር ካቆራረጧቹህ በኋላ አንቅረው ይተፏቹሃል ከሁለት ያጣ ጎመንም ሆናቹህ ትቀራላቹህ!” ነበር ያልኳቸው ይሄው ያልኩትም አልቀረ በዚህ መልኩ ተዋርደው መጨረሻቸው ይሄ ሆነ!!! አያሳዝኑም???
Filed in: Amharic