በመጪው እሁድ በመላ አማራ ክልል ሰልፍ ተጠርቷል…!!!
ባልደራስ
በደብረማርቆስ ከተማ የ12ኛ ክፍልን ውጤት
በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ
/
የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት በመቃወም በደብረማርቆስ ከተማ ዛሬ በ15/7/2014 ዓ.ም ሰልፍ ተካሄደ፡፡ በሰልፉ ላይ መምህራንና ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ “በ12ኛ ክፍል ውጤት ተስፋቸውን የተነጠቁ ተማሪዎችና ወላጆች ፍትህ ይሰጣቸው” በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመጪው እሁድ፣ መጋቢት 18/2014 ዓ.ም.በመላው የአማራ ክልል ባሉ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ተደርጓል፡፡ ጥሪውን ያስተላለፉት የአማራ ወጣቶች ማህበር እና የአማራ ተማሪዎች ማህበር ሲሆኑ፣ የሰልፉ ዓላማን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ “በ12ኛ ክፍል የአማራ ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ምሁራዊ የዘር ፍጅት/Intellectual Genocide/እና በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መንግሥታዊ የዘር ማጥፋት የሚያወግዝ እና ለሁለንታዊው ትግሉ መጀመሪያ የሚሆን ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ የፊታችን እሁድ መጋቢት 18/2014 ዓ.ም ይደረጋል” ብለዋል፡፡
እንደሚታወቀው፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከሁለት ሳምንታት በፊት ባወጣው መግለጫ፣ አሁን ያሉት አስገዳጅ ሁኔታዎች የሚቀጥሉ ከሆነ፣ ሕጋዊ የሆነ ሠላማዊ ሰልፍ ለመጥራት ሊገደድ እንደሚችል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡