>
5:33 pm - Tuesday December 5, 2682

ሰውዬው ንብረትነቱ የገዳዮቻችን ደመኝነቱ የሁላችን ነው...!!! (መስከረም አበራ)

ሰውዬው ንብረትነቱ የገዳዮቻችን ደመኝነቱ የሁላችን ነው…!!!
መስከረም አበራ

* …. “መፈናቀል ሁሉም ቦታ አለ፤ በክልላችን እንኳን ብንወስድ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን
ኦሮሞዎች ተፈናቅለዋል…!!!”
ዶር ይልቃል ከፋለ
ከታች የምታነቡትን  ንግግር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተፅፎ ቢሰጠው እንኳን በዚህ ሰውዬ ሁኔታ ተረጋግቶ አይናገረውም።  ወደ ብአዴን ወንበር የሚመጣው የመጨረሻው ሰው በገዛ ህዝቡ ላይ በመዝመት የመጨረሻው የሮቦትነት ፕሮግራም የተጫነበት ዞምቢ ነው! ይህ ሰውዬ ባለንበት ወቅት ያለው የመጨረሻው Version  የሮቦትነት ፕሮግራም የተጫነበት ነው! የተጫነበትን ተዘርግፎ ወርዷል!!!! ሰውዬው ንብረትነቱ የገዳዮቻችን ደመኝነቱ የሁላችን ነው!!!!!!!!!ደመኛውን ከትከሻው ያላሽቀነጠረ ህዝብ እንዲህ በለቅሶ ድንኳኑ እየተደነሰበት ይኖራል !
👇
“መፈናቀል ሁሉም ቦታ አለ። በክልላችን እንኳን ብንወስድ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን
ኦሮሞ ተፈናቅለዋል። ከጎንደር ቅማንት ተፈናቅለዋል። ቤኒሻንጉል’ም ቢሆን አማራ ብቻ ሳይሆን ጉሙዝም ተፈናቅሏል። በኦሮሚያም ኦሮሞም ተፈናቅለዋል፣ ተገድለዋል። ሁሉም ጋር ህመም አለ። የአማራውን ብቻ ነጥሎ ማስጮህ ወደ ዘላቂ መፍትሔ አይወስደንም። እባካችሁ ፅንፍ እየረገጣችሁ አማራን ከሌላው ኢትዮጵያዊ አትነጥሉት። ሕገመንግስቱ ይሻሻል እያለን ነው። በጩኸትና በፅንፈኝነት አማራን ከሌላው እየነጠለን በሕገመንግስቱ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ማነው ከአማራው ጋር የሚቆመው..? አማራን ከሁሉም ጋር እያናከሰን እረፍት አየነሳነዉ ነዉ።ስለሆነም እባካችሁ አክቲቪስቱም፣ ባለስልጣናቱም እንስከን እንስከን እንስከን..! “
ዶር ይልቃል ከፋለ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር
Filed in: Amharic