>

የቴዎድሮስ ካሳሁን "ደሞ በአባይ"  በምርጥ ነጠላ ዜማነት መመረጡ  የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ሙያ የሚያነቃቃ ነው...!!! (ታታ አፍሮ -ነፃ ብዕር)

የቴዎድሮስ ካሳሁን “ደሞ በአባይ”  በምርጥ ነጠላ ዜማነት መመረጡ  የኢትዮጵያን የኪነ-ጥበብ ሙያ የሚያነቃቃ ነው…!!!
ታታ አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በለዛ አዋርድ ላይ “ደሞ በአባይ” በተሰኘው ዘፈኑ ምርጥ ነጠላ ዜማ በሚል ዘርፍ እጩ ሆኖ ቀርቧል። እውነት ለመናገር እንደ አንድ የቴዲ አፍሮ አንድናቂ የቴዲ አፍሮን ነጠላ ዜማዎች ከሌላው እኩል ነጠላ ዜማ ብሎ ለመጥራት እጅግ እጨነቃለሁ። የሆነው ሆኖ እንዲህ ያሉ ዝግጅቶች መኖራቸውና እንደ ቴዲ አፍሮ ያለ የሙዚቃ ቅመም የሆነ ሰው እጩ ሆኖ መቅረቡ እሰይ ይበል ያስብላል። ምክኒያቱም ይኼ የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ሙያን የሚያነቃቃ አጋጣሚ ነው። በሚሊየኖች ልብ ውስጥ ነግሶ የኖረው እውቁ እና ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢልቦርድ ላይ እጩ ሆኖ ቀርቦ በአንደኛነት ደረጃ ሲመራ የቆየ ትልቅ አርቲስት ነው።
ቴዲ አፍሮ በሙዚቃው ዓለም በደረሰበት ስኬት ምክኒያት የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ ሲያስጠራ ቆይቷል። CNN, BBC, CG Tv ወዘተ ስለ ቴዲ አፍሮ ሰፊ ዘገባን ሰርተዋል። ይኼ ኩሩና ስመ ጥሩ አርቲስት ወደ ተጠቀሱት ሚዲያዎች ተጉዞ ሳይሆን ሚዲያዎቹን ወደ እቤቱ ጋብዞ ነበር አብሯቸው ቆይታ ያደረገው። ይኼ ደግሞ ለአገራችንም ይሁን ለኪነጥበቡ ትልቅ ጀብድ ነው። ምክነያቱም ዓለማችን ላይ ትልቅ አድማጭ ያላቸው ሚዲያዎች ናቸው የቴዲ አፍሮን ደጅ የጠኑት።
ስለ ቴዲ አፍሮ ግዝፈትና ስለደረሰበት ስኬት በጥቂት ሰሌዳ አይደለም በግዙፍ ብራናም ቢከተብ ቅንጣቱን ቢገልጽ ነው። ቴዲ አፍሮ በቆመበት መድረኮች ሁሉ እውነተኛ ጥበቦቹን ያንጸባረቀ፤ በሄደበት ሁሉ እውነትን አጽንቶ የያዘ፥ ድልን የለመደ ታላቅ ሰው ነው። የዚህ ሰው አድናቂዎች በአቋሙ የሚኮሩበት በስራው አብዝተው የሚወዱት ሰው ብቻ ሳይሆን በማያወላዳ አቋሙ የሚተማመኑበት ሰው ጭምር ነው። በዚህ ዘመን በቴዲ አፍሮ ልክ እርግጠኛ ሆነህ የምትወደው አርቲስትም ይሁን የፖለቲካ ሰው በፍጹም የለም።
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቴዲ አፍሮን መምረጥ ለአድናቂዎቹ የራስን ጥቅም እንደማስከበር ነው።
ቴዲ አፍሮን በምርጥ ነጠላ ዜማ ለመምረጥ
ማስታወ
ብዙ ሰዎች ወደ ዌብሳይቱ እየገቡ ስለሚመርጡ የሰርቨር መጨናነቅ ሊኖር ይችላል። ቢሆንም ግን በተደጋጋሚ በመሞከር እንድትመርጡ ይሁን… እንዲሁም የአመራረጥ ሂደቱን በተመለከተ የአንድ ደቂቃ ቪዲዮ ስላለ እሱን ቢመለከቱ ይረዳዎታል።
የአመራረጥ ሂደቱን ማየት ካሻዎ
Filed in: Amharic