>

የጄኔራል አበባው ታደሰን ፎቶ በገጿ የለጠፈቺው ሆስቴስ ለእስር ተዳረገች ...!!! (ጋሻ መልቲ ሚዲያ)

የጄኔራል አበባው ታደሰን ፎቶ በገጿ የለጠፈቺው ሆስቴስ ለእስር ተዳረገች …!!!
ጋሻ መልቲ ሚዲያ

የኢትዮጲያ አየር መንገድ በረራ አስተናጋጅ የሆነቺው ሆስተስ መቅደስ ተስፋዬ የጄኔራል አበባው ታደሰ ጋር የተነሳቺውን ፎቶ በፌስቡክ ገጿ ላይ በመለጠፏ ለመታሰር እንደበቃች መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ፎቶውን የተነሱት ጄኔራሉ ወደ አስመራ ሲመላለሱ በነበረበት ወቅት በአንደኛው ጉዞአቸውና ሆስተሷ አስተናጋጅ በሆነችበት ወቅት የተነሱት ፎቶ ሲሆን ዛሬ ለመቅደስ ተስፋዬ መታሰር ምክንያት የሆነው ይህው ወደ ኤርትራ የተደረገውን ምስጢራዊ በረራን መደበቅ በመፈለጉ ምክንያት ልጅታ ፎቶውን ከፌስቡክ ገጻ ላይ እንድታነሳው ከተደረገ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ለመታሰር እንደበቃች ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።
 ላለፉት ሶስት ዓመት ከፍተኛ ፍቅር ላይ የነበሩት አቢይ እና ኢሳያስ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ወደ ባላንጣነት ደረጃ እየተሸጋገሩ ያሉበትን ሁኔታ እያየን ሲሆን የአቢይ መንግስት በምንሊክ ቤተመንግስት በቦሌ አየር መንገድ ጣቢያና በበርካታ የኢትዮጲያ ደህንነት ተቌም ውስጥ ተሰግስገው የነበሩትን የሻእቢያን የደህንነትና የጸጥታ አባላትን ጠራርጎ ካስወጣ ወራቶች ተቆጥረዋል።
የአቢይ መንግስት በተቻለው መጠን እራሱን ከኢሳያስ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት የበጠሰ ለመምሰል በሚጥርበት ወቅት ይህንን ግንኙነት ይዞታን በሚጣረስ መልኩ የመቅደስ ተስፋዬ ፎቶ የጄኔራሉን የአስመራ ጉዞን የሚያሳይ በመሆኑ ለእስር ሊዳርጋት ችሏል።
Filed in: Amharic