>

በዝቋላ ወረዳ በህወሓት ስር ከተያዙ 6 ቀበሌዎች 18ሺህ ዜጎች ተፈናቅለዋል...!!! (DW)

በዝቋላ ወረዳ በህወሓት ስር ከተያዙ 6 ቀበሌዎች 18ሺህ ዜጎች ተፈናቅለዋል…!!!
DW

“…. በዝቋላ ተፈናቃዮች ጣቢያ አዋላጅ ነርስ ደርቤ ውዱ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደተናገሩት 2,298 ሕጻናት በመጠለያ ጣቢያው ይገኛሉ። ነገር ግን አልሚ ምግብ የላቸውም። ተፈናቃዮቹ የሚመጡት በህወሓት ስር ካሉ የዝቋላ ወረዳ 6 ቀበሌዎች መሆኑንም ገልጸዋል። 
 
በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዝቋላ ወረዳ በህወሓት ከተያዙ የወረዳው አካባቢዎች የሚፈናቀሉ ሕጻናት ቁጥር መጨመሩን የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ። አንድ ተፈናቃይ እናት ከወለዱ ጥቂት ቀን ቢሆናቸውም ሲሚንቶ ላይ እንደሚተኙ ነው የተናገሩት። በዝቋላ ተፈናቃዮች ጣቢያ አዋላጅ ነርስ ደርቤ ውዱ ለዶይቼ ቬሌ በስልክ እንደተናገሩት 2,298 ሕጻናት በመጠለያ ጣቢያው ይገኛሉ። ነገር ግን አልሚ ምግብ የላቸውም። ተፈናቃዮቹ የሚመጡት በህወሓት ስር ካሉ የዝቋላ ወረዳ 6 ቀበሌዎች መሆኑንም ገልጸዋል። አቶ ደርቤ ከረጂ ድርጅቶች ለሕጻናቱ ዓልሚ ምግብ እየመጣ እንደሆነ ቢሰሙም እስካሁን ወግን ደ መጠለያ ጣቢያው እአልደረሰም ነው ያሉት። «እርዳታው ለሕጻፃናቱ የሚደርስ ከሆነም መልክም ዜና ነው» ብለውታል።
መጠለያ ጣቢያው ንፅህና የሌለው በመሆኑና  የውሀ አቅርቦት ባለመኖሩ ህፃናቱ ለከፋ የተቅማጥ ህመም እየተጋለጡ እንደሆነም ነው ባለሙያው የተናገሩት። ከ5 ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው 80 ሕጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት የተጋለጡ እንደሆኑና ህክምና እየተሰጣቸው እንደሆነም አመልክተዋል። በዝቋላ መጠለያ ጣቢያ 80 እናቶች የእርግዝና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን የማዋለጃ ቁሳቁሶችና ግብዓቶች በመጠለያ ጣቢያው ባለመኖሩ 7 እናቶች ወደ ሆስፒታል ሄደው እንዲወልዱ ተደርጓል እንደ አቶ ደርቤ። ከተፈናቃዮቹ መካከል በቅርቡ እንደወለዱ የሚናገሩት አንድ ተፈናቃይ በወጉ መታረስ ባይችሉ እንኳ ስሚንቶ ላይ እንደሚያድሩ ለበሽታ እየተጋለጡ መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። በዝቋላ ወረዳ በህወሓት ስር ከተያዙ 6 ቀበሌዎች 18ሺህ ዜጎች ተፈናቅለዋል።
በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የኮሙዩኒኬሽን መምሪ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ያለው የተፈናቃይ ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እያደገ መሆኑን ይናገራሉ። በአሁኑ ጊዜም የተፈናቃዮቹ ቁጥር በብሔረሰብ አስተዳደሩ 65,757 ደርሷል ነው ያሉት። በመካከላቸውም አካል ጉዳተኞች የሚያጠቡ እናቶች፣ ሕጻናት፣ አቅመ ደካማ አባቶች እና እናቶች እንደሚገኙባቸው አስረድተዋል። ምንም እንኳ የምግብ እርዳታ ወደ አካባቢው ቢሄድም በቂ ባለመሆኑ በርካቶቹ ለከፍተኛ ርሀብ መጋለጣቸውንም ተናግረዋል። ተፈናቃዮቹ የሚሰጣቸውን 15 ኪሎ ግራም ስንዴ በአካባቢው ኤሌክትሪክ ባለመኖሩ ማስፈጨት ባለመቻላቸው ስንዴውን ለገበያ አውጥተው ሸጠው እንጀራ በውድ ዋጋ ገዝተው እንደሚመገቡም ገልጸዋል። አክለውም ርሀብ የለም እያሉ በተራቡ ወገኖች ላይ የሚያሾፉ አካላት ትክክል አለመሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል ነው ያሉት አቶ ከፍያለው። ረሀብ ተፈናቃዮችን እያሰቃየ ነውም ብለዋል። ተፈናቃዮች በቶሎ ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ካልተመቻቸና ወደ ግብርና ሥራቸው ካልተሰማሩ በቀጣይ ዓመትም የባሰ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል ከወዲሁ አስጠንቅቀዋል። እንደ አቶ ከፋያለው 16, 375 ተፈናቃዮች በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መጠለያዎች ይገኛሉ። 49, 381ዱ ደግሞ በየዘመድ እና በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለዋል። ከነዚህ ውስጥ 2,521 ሕጻናት፣ 882 ነፍሰጡሮች፣ 3,398ቱ ደግሞ ተማሪዎች መሆናቸውን መግለጻቸውን ከባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን በላከው ዜና አመልክቷል።
ፎቶ ፤ ከዋግህምራ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተገኘ
Filed in: Amharic