>

በዳቦ ስሙ ብልጽግና " ስውር ሸኔ ነው" ስንል በማስረጃ ነው...!!!

እውነታው ይህ ነው….!

በዳቦ ስሙ ብልጽግና ” ስውር ሸኔ ነው” ስንል በማስረጃ ነው…!!!


 

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ምስክርነት የዚህ ዋና ማስረጃ ነው…..።
በዕለቱ ጥዋት አካባቢ አንዳንድ ምልክቶች ነበሩ 4 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ከዛ በኃላ ወደ ቀን 7 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ መሳሪያ የጫኑ በልዩ ልዩ በአይሱዙ ፣ በመሳሰሉ መኪናዎች ጭነው የመጡ ሰዎች አልፍ ሲልም የመንግስት ተሽከርካሪ ጭምር የተጠቀሙ ሰዎች ናቸው የመጡት…።
 የቡድን መሳሪያም አጥምደው ነው የመጡት፤ መጀመሪያ ላይ በአውራ ጎዳና ከተማ ውስጥ አለፉ ከዛ መጨረሻ ላይ ዳር ላይ ሲደርሱ የፌዴራል ፖሊስ ምንድነው ሲላቸው መጀመሪያ እሱን ገደሉ ከዛ ተመልሰው ወደ ማህበረስቡ ገቡና ወደ 8 ሰዓት አካባቢ በጣም የጦፈ ጦርነት ውስጥ ነበር የተገባው ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል…።
በነገራችን ላይ እንደ ምንጮቻችን ጥቁምታ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ ቦሌ፣ኡርጊ እና ጠዴቻ በሚባሉ ቀበሌዎች በሽመልስ አብዲሳ መንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው መሰልጠን ከጀመሩ ሰባት ወራት አለፉ። እዚህ አካባቢ የሚሰለጥነው የኦሮሞ ብልፅግና ኢ-መደበኛ ታጣቂ(ሸኔ) ቁጥር ከ3000 እንደሚበልጥ የሚታወቅ ሲሆን መከላከያ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ብሔር የሆኑ አሰልጣኞችም ጭምር ያሰለጥኗቸዋል…።
እንግዲህ ይህ ሀይል ነው በላፈው ሳምንት ፑል ቤት በመግባት ከ15 በላይ አማራዎችን በመተሓራ ከተማ በግፍ የጨፈጨፉት። ትናንት ደግሞ ከአዋሽ በመነሳት በአንድ FSR፣ 2 landcruser እና በአንድ ተጭነው መጥተው ምንጃር ሸንኮራ ወረዳን የማውደም ተልዕኮ ተሰጥቷቸው መጡ። አውራ ጎደና ሲደርሱ የተገኘው ላይ ሁሉ መተኮስ ጀመሩ በዚህም እስከ አሁን በግልፅ የታወቀ 3 አማራዎች ሲሞቱ ከ7 በላይ መቁሰላቸው ተሰምቷል። በተለይ እነዚህ ቀበሌዎችን ጨለለቅ፣ ቀርጣፋ፣ ጀርጀባ ቆላ እና አውራ ጎደና ለማውደም ቢሞክሩም በአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ ያሰቡት ሳይሳካ 29ኙ ተደምስሶ ቀሪው እግሬ አውጭኝ ብሎ ሲፈረጥጥ የመጡበት 4 መኪናም ተማርኳል…።
ይሄን የሰማው የሽመልስ መንግስት ግን ያሰቡት እኩይ ተግባር ስላልተሳካ፤ የአማራው እነሱ በሚፈልጉት መጠን ባለመጨፍጨፉ እንዲሁም በቀበሌው ያሉት የአርሶ አደሩ ቤቶች ስላልተቃጠሉ ተበሳጭተዋል፤ ብስጭታቸውንም ራሱን የተከላከለውን የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖ በሀሰት በመክሰስ እየገለፁ ነው…።
ለማንኛውም በብልጽግና መራሹ ሀይል የሚመራዉ ተስፋፊው እና ወራሪው ኦነግ እየተባ የሚጠራዉ የፈሪወች ስብስብ በምንጃር በኩል ያደረገው ሙከራ በጀግናው የምንጃር ህዝብ እና በተወርዋሪዉ የሸዋ ፋኖ ጠንካራ በትር ለጊዜዉ  እንዲከሽፍ ሆኗል…።
አማራ የምትከበረው እንዲህ እንደ ምንጃሮቹ እሳት ስትተፋ ነውና ከዚህ በኋላ እሳት ጎርሰህ እሳት ለብሰህ እሳት በመትፋት መሰል ወራሪ ኦነግ ሸኔን በሚገባው ቋንቋ ለማናገር መቼም የትም ክንድህን አበርታ…።
Filed in: Amharic