>

የተዓምረኛዋ አገር ተዓምራት ቀጥሏል...!!! (የሸገር ልጅ)

የተዓምረኛዋ አገር ተዓምራት ቀጥሏል…!!!

የሸገር ልጅ

*… ጠቅላይ “ዳቦ በሙዝ በልታችሁ ሩጡ!!” ማለታቸውን   ካድሬው በብርሀን ፍጥነት ተቀብሎ ተግባራዊ. አድርጎታል
*..ካድሬዎች የሙዝና የአቦካዶን ጥቅም ለህብረተሰቡ በማስረዳት ተጠምደዋል።
 
ነገ ደግሞ እንጄራ እንዲህ ተጠቅልሎ ይጎረሳል፣ቂጣ በጎመን ይጣፍጣል በማለት ስልጠና ሳይሰጡ ይቀሩ ይሆን?
፦አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ።
አንዲት ባልቴት ሆስፒታል ሄደው፦
ዶክተሩ ፦ለጣናው ሙዝ፣ፓፓዬ፣አቦካዶ፣ጥራጥሬ ለምሳሌ አተር፣ባቄላ የመሳሰሉትን፣
ቀይ ሥጋ፣ወተት፣እንቁላል፣ዓሳ የመሳሰሉ የምግብ ዓይነቶችን ጧት፣ቀንና ማታ ቢመገቡ በአጭር ጊዜ ጤናዎ ይመለሳል።
ቢላቸው፦
ባልቴቷ ምን ቢሉ ጥሩ ነው?
ዶክተሩን ያልካቸውን ምግቦች የምመገበው በእኔ ሂሳብ ወይስ ባንተ ብለውት እርፍ።
ወገን አረ እየታሰበበት ሰው የሚጠቅመውንና የሚያስፈልገውን ያውቃልና እባካችሁ ከቻላችሁ የመንግስት ባለሥልጣናት ከዘረፋችሁትና ከነጠቃችሁት ገንዘብ የድርሻውን አካፍሉት ያኔ ሳይነገረው የሚጠቅመውን ይበላል።
እናንተ ሁሉንም ዘርፋችሁት በምኑ ይብላ?አረ ግፍ ይሆናል እግዚአብሔርን ፍሩ።።
Filed in: Amharic