>
5:31 pm - Wednesday November 13, 4548

አማርኛ የማይችል የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ በከተማዋ ነዋሪ ላይ በተፈፀመ የግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ፍ/ቤት ቀረበ! (ባልደራስ)

አማርኛ የማይችል የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ በከተማዋ ነዋሪ ላይ በተፈፀመ የግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ፍ/ቤት ቀረበ!
ባልደራስ

*… ፖሊሱ ኦሮምኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚችል ለፍ/ቤቱ በአስተርጓሚ ተናግሯል!
/
አማርኛ የማይችል የአዲስ ፖሊስ፣  በምሽት በሁለት ጥይት ተተኮሶ በተገደለ የአዲስ አበባ ነዋሪ ጉዳይ ተጠርጥሮ ትላንት አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፌድራል ፍርድ ቤት ቀረበ። ግድያው የተፈፀመው ከፖሊስ አባላት በተተኮሱ ሁለት ጥይቶች የአዲስ አበባ ነዋሪ ላይ ነው።
 ተጠርጣሪው ዳኛ ፊት ቀርቦ፣ ስለተጠረጠረበት ጉዳይ ሲጠየቅ፣ አማርኛ ቋንቋ እንደማይችል ተናግሮ ከመርማሪ ፖሊሶች መካከል ኦሮሚኛ ተናጋሪ ፖሊስ ተመርጦ፣በትክክል ለማስተርጎም ቃለ መሃላ ፈፅሞ ተጠርጣሪው ቃሉን ሰጥቷል። ከዚህ ፖሊስ ሌሊ፣ በዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ አምስት ፖሊሶች የተከሰሱ ሲሆን፣ ሁሉም ከአዲስ አበባ ውጭ የተመለመሉ ናቸው።
እንደሚታወቀው፣ ከምርጫ 97 ቦኃላ በጥቅሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ በተለይ ደግሞ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፖሊስነት እንዳይመለመሉ በህወሓት ተከልክሏል። ከዚያ ቦኃላ ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል የተመለመሉ ፖሊሶች ቁጥር ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ሄዶ፣ ከሞላ ጎደል ሙሉ ለሙሉ እየጠፋ በመሄድ ላይ ይገኛል። ከህወሓት ውድቀት ቦኃላ ኦህዴድ ሥልጣን ሲይዝ ሂደቱ ይበልጥ ተጠናክሮ፣ ምልመላው በተለይ በኦሮሚያ ላይ እንዲያነጣጥር ተደርጓል። ምልምል ፖሊሶቹ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት የሚል እምነት ያላቸውና ለብዙሃኑ የከተማዋ ህዝብ የተሳሳተ ግንዛቤ ያላቸው ናቸው።
Filed in: Amharic