>

ለእብሪተኛው ኦህዴድ መግለጫ የተሰጠ ምላሽ!  (ወንድወሰን ተክሉ)

ለእብሪተኛው ኦህዴድ መግለጫ የተሰጠ ምላሽ!

 
 ወንድወሰን ተክሉ
 
*…. የጽንፈኝነት መፈልፈያ የሆነቺው ኦሮሚያ ጽንፈኞቻን ከማጽዳት ይልቅ ድንበር ዘሎ የአማራ ጽንፈኛ አስቸገረን በማለት እራስን ማጽዳት አይቻልም-!!!!
 
የኦህዴድ ሊ/ር የሆነው አቢይ አህመድ አሊ ስልጣን ከያዘበት መጋቢት 2018 ጀምሮ በመተከል፣በወለጋ፣በሰሜን ሸዋና በአጠቃላይ ኦሮሚያ ለጆሮ የሚቀፍ አሰቃቂ ወንጀል አንዳችም ትጥቅ ባልታጠቁ ንጹኋን ላይ ሲፈጸም እስኪያንገሸግሽን ድረስ አይተናል – ሰምተናልም። በዚህ አራት ዓመት ውስጥ በኦሮሚያና በመተከል በአማራነታቸው ብቻ እየተመረጡ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ቁጥር ከ12ሺህ በላይ ነው። ይህ አሃዝ በሰሜኑ ከትህነግ ጋር በተካሄደ ጦርነት የሜቱትን ፈጽሞ አይጨምርም። በወለጋ ዜጎች በአማራነታቸው በጅምላ ሲታረዱ የአቢይ ኦህዴድ ጽንፈኝነት አስቸገረን ብሎ አያውቅም። በወለጋ ዜጎች በእሳት ሲቃጠሉ ጽንፈኝነት አሰቸገረኝ ብሎ አያውቅም። በመተከል የሰው ልጅ በጅምላ ተጨፍጭፎ በግሬደር ሲቀበር ጽንፈኝነት አስግሮናል ብሎ አያውቅም።
በኦሮሚያ ሻሸመኔ፣ዝዋይ፣ነጌሌ፣ባሌ፣ሀረርና በሰሜን ሸዋ አጣዬ ዜጎች እንደጉድ ሲታረዱ ሲበለቱ ቤት ንብረታቸው ዶግ አመድ ሲደረግ አጣዬን የመሰለች ትልቅ ከተማ እንዳለ ስትወድም ፈጽሞ ጽንፈኝነት አስቸገረኝ አላለም።
በወለጋ ከ20 በላይ ባንኮች በጠራራ ጸሀይ ሲዘረፉ የጽንፈኝነት ጉዳይ ነው አላለም። በአረቱ የአቢይ ዘመን በመላ ኦሮሚያ፣በመተከልና በሰሜን ሸዋ ለተፈጸመው አስቃቂ ጭፍጨፋ- የወላድ ማሕጸን በቢላ ሲተረተር፣የሰው ልጅ ስጋ እየተበለተ ሲበላ፣የሰው ልጅ ህይወት በቁሙ ቤንዚን ተርከፍክፎበት በእሳት ሲቃጠል አይደለም ጽንፈኝነት አስቸገረኝ ብሎ መግለጫ ሊያወጣ ይቅርና አዝናለሁ እንኴን አንዲት ቀን ብሎ አያውቅም።
በአራት ዓመት አገዛዙ ለተፈጸመና ዛሬም እየተፈጸመ ላለው ህልቆ መሳፍርት የሌለው አሰቃቂ ወንጀል ድርጊቱ የጽንፈኞች ተግባር ነው በጋራ እንታገል ብሎ የማያውቅ በንጹኋን ደም የፖለቲካ ቁማር ቆማሪው አቢይ አህመድ አሊ ዛሬ ኢቀመንበርነት በሚመራው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ኦህዴድ በኩል አይኑን በጨው አጥቦ በሰሜን ሸዋ አማራ ዞን ምንጃር ሸኮራ አውራ ጎዳና ቀበሌ ንጽሃንን ሊጨፈጭፍ የተጋዘን ኢ-መደበኛን ታጣቂን ገዳይ ቡድን ጀግኖቹ የምንጃር ተርቦች ቀንድበው ቀንድበው እምሽክ ሲያደርጉት የአማራ ክልል ጽንፈኞች ወደ ኦሮሚያ ክልል ዘልቀው በመግባት የጸጥታ ሃይሎች ላይ እርምጃ ወሰዱ በማለት ጽንፈኝነትን እንዋጋ የሚል መግለጫ ሲያወጣ ለማየት ችለናል።
የዚህ ይሉኝታውን በማን አለብኝነታዊ እብሪት ጠቅልሎ የበላው አቢይ መራሹ የኦሮሚያው ኦህዴድ እብራታዊ እይታ ከዚህ በፊት በጎጃም ሞጣ አራት መስጊዶች በተቃጠለበት ወቅት በብርሃን ፍጥነት ድርጊቱን አውህዞ መግለጫ እንዳወጣ ሁሉ ዛሬም ባለፈው ሳምንት ወደ ሰሜን ሸዋ አማራ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ዘልቆ የገባን ኢ-መደበኛ ታጣቂ ቡድንን የአካባቢው ነዋሪ በአልሞትባይተጋዳይነት እራሱን መከላከል በመቻሉ ጨጔራው በንዴት በግኖ ድርጊቱን የአማራ ጽንፈኞች በኦሮሚያ ክልል ዘልቀው  የፉጸሙት ጥቃት በማለት ጽንፈኝነት የሀገራችን አደጋ ነው ሲል በጋራ እንዋጋው የሚል የድፍረት መግለጫን ሊያወጣ ችሏል።
የአቢይ መራሹን የኦሮሚያው ኦህዴድ መግለጫ ስንመለከት «……. የአማራና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀንደኛ ጠላት የሆኑት በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ  ጽንፈኛ ሀይሎች   በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ዘልቀው በመግባት በሰላማዊ ዜጎችና ጸጥታ አካላት ላይ የፈጸሙት አስጸያፊ ድርጊት የክልሉን ህዝብ ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡
 ይህ ጽንፈኛ ሀይል ስለፈጸመው አስጸያፊ ድርጊት  የክልሉን የመንግስት ሚዲያ  ጨምሮ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ሲያስተጋቡ፤ ጥላቻን ሲሰብኩና የግጭት ነጋሪት ሲጎስሙ በዝምታ ማያት ተጋቢ አለመሆኑን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጽኑ ያምናል…» በማለት የገለጸውን የመግለጫው አስኴል ፍሬ መልእክት አድርገን ስንጠቅስ በውስጡ የያዛቸውን « የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላቶች………… የአማራ ጽንፈኞች…….. በኦሮሚያ ግዛት ዘልቀው በመግባት…. …   ..የኦሮሞ ሕዝብ ተቆጥቷል….   » የሚሉትን ቃላቶች በጽሞና ትርጉማቸውን እንድተገነዘቡ በማለት ነው።
ማነው ጽንፈኛ ?? የትኛውስ ነው የኦሮሚያ ክልል ?? የተገደለው ንጹኋንስ ማን ነው?? የኦሮሞ ሕዝብ የሚቆጣውስ ለምንድነው ? በማን ላይስ ነው የሚቆጣው ??
የዘፈን ዳርዳርታ ለእስክስታ እንደተባለው የአቢይ አህመድ መራሹ የኦህዴድ ብልጽግና መንግስት ላለፉት አምስትና ስድስት ወራት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን እና ይህም የተለወጠው ፖሊሲ አዲስ የኋይል አሰላለፋዊ መስመር የፈጠረ መሆኑን ይህ ጸሀፊ በተለያዩ አርእስቶች ስር ደጋግሞ የገለጸ መሆኑን እያስታወሰ በዚህ አዲሱ የአቢይ ፖሊሲ መሰረት የአማራ ልዩ ኋይል፣ የአማራ ፋኖ እና አጠቃላይ የአማራ ኋይሎች ፖለቲካዊ አደረጃጀትን እና አሰላለፍን ተቆጣጥሮ በእሱ ፍላጎት ስር ለማዋል ፋኖን ትጥቅ የማስፈታትና ልዩ ኋይሉንም አዳክሞ የማፍራረስን እርምጃን ለመውሰድ የልዩ ኋይሉን ዋና አዛዥ ብ/ጄ  ተፈራ ማሞን ማባረሩን እና በፋኖላይ ትጥቅ የማስፈታትና ብሎም የማሳደድ ዘመቻ መክፈቱ ይታወቃል።
ሆኖም ይህ አማራውን ትጥቅና የተደራጀ ድርጅት አልባ የማድረግ ዘመቻዊ እቅዱ እንዳቀደውና እንዳሰበው እየተፈጸመለት ባለመሆኑ አሁን በግልጽ ወረራዊ ዘመቻ ለመክፈት የወሰነበትን ሁኔታን ፍትሃዊነትን ለማላበስ፦
 
1ኛ -የምንጃርን ክስተት በኦሮሚያ ግዛት ውስጥ የተፈጸመ ነው ብሎ መግለጹ
 
2ኛ -ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራ ጽንፈኞች ነው ማለቱ
 
3ኛ- ጽንፈኞቹ ያላቸው የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላቶች ብሎ መግለጹ
 
4ኛ- የኦሮሞ ሕዝብ ተቆጥታል ማለቱ
 
5ኛ – የኦነግ ሸኔን ስም ለይስሙላ መጥቀሱ ሊፈጽም ለተመኘው መጠነ ሰፊ ዘመቻ አመላካችነቱ የምንጠቅሰው ቁልፍ ነጥብ ነው።
 
፠ የአማራው አጸፋ ምን መሆን አለበት???
ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንደተባለው ለመበላት የተፈረደባት አሞራ እኔ ጅግራ አይደለሁም ብላ በመከራክራ እና በማሳመን ሳይሆን ከመበላት እምትድነው ፈጥና በመብረርና ባለመያዝ ብቻ ነው ከመበላት እራሳን የምታድነው።
አማራው ከእነዚህ ገተት ከሆኑት ኦህዴዳዊ ብልጽግና ጋር ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራ ግዛት እራስን በመከላከል ነው እያለ በመሞገት ለማሳመን ቅንጣት መጣር የለበትም። የአማራ ፋኖ የአማራ ልዩ ኋይልና የአማራ ታጣቂ ሚሊሺያም ጽንፈኛ አይደለም ሀገርና ወገን ወዳድ ነው እያለ ለማሳመን አሁንም ሰከንድ ማጥፋት የለበትም።  የእውነተኛ ጽንፈኝነት ትርጉም የሰውን ልጀ በቁም በእሳት በማቃጠል፣ከእኔ ብሄር ውጪ ሌላ ብሄር ተወላጅ በክልሌ መኖር አይችልም ውጣ ከክልሌ እያሉ ማባረር፣ ምንም ያልታጠቁ ንጹኋንን በግፍ መጨፍጭጨፍና የመንግስትና የሕዝብን ንብረት መዝረፍና ማውደም የጽንፈኝነት መገለጫዎች እንደመሆናቹው መጠን እና ይህ አይነቱ ተግባርና ድርጊት የኦሮሚያ ክልል አይነተኛ መገለጫ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር በሆነበት እኛ ጽንፈኞች ነን እና አይደለንም በሚል ከንቱ ሙግት ውስጥ ፈጽሞ ሳንዘፈቅ በሁሉም የአማራ ግዛት ውስጥ ያሉንን ዘርፈ ብዙ የአማራ ታጣቂ ኋይል ማለትም  የአማራ ልዩ ኋይል የአማራ ፋኖ የአማራ ታጣቂ ሚሊሺያ እና የፖለቲካ አመራሩ በተለይም በቅድሚያ የሸዋው ዞን የተቀናጀና የተጣመረ አመራራዊ የእዝ ሰንሰለት መስርቶ በተጠቀቅ መጠበቅ እና የሚመጣውን ማንኛውንም አይነት ሃይል እንደ አመጣጡ ለማስተናገድ ወስኖ  መዘጋጃት ነው የሚገባን እንጂ  ጅግራ ነህ ብሎ ሊበላህ የሚመጣን የኬኛን አውሬ እውነቱን በማሳወቅ አሳምነለሁ ብሎ መዘናጋት ፈጽሞ አይጠበቅብንም።
ይህ አቢይ መራሹ የኦህዴድ እብሪታዊ ፍላጎትና ዓላማ አጠቃላይ ሰሜን ሸዋ እስከ ሰሜን ወሎ ድረስ ዘልቆ የሚገባውን የጽንፈኛና የተስፋፊዋን ሁሉን ኬኛ ታላቂታን የኦሮሚያን ካርታ እውን ከማድረግ ዓላማ አካያ የታሰበበትና ተዘጋጅቶበት የተወሰነ ዘመቻ መሆኑን ልብ ብለን ለዚህ ደግሞ በትህነግ ወረራና ዘመቻ ምክንያት የተፈጠረውን የአማራን ሕዝብ እራሱን የማደራጀትና እራሱን የማስታጠቁን ሁኔታ ለማፈራረስ ያቀደ መሆኑን በመገንዘብ አንዳችም አይነት የተባባሪነት  ምላሽ ሳንሰጥ በአመለካከት በፕሮፖጋንዳና ብሎም በስነልቦናም አካያ አንጥረን ልንመልስ ይገባል።
ንጹሃንን ሊገድልና ሊጨፈጭፍ የመጣን ገዳይና ጨፍጫፊን ቡድን ቀንድቦ በማክሸፉ የኦሮሞ ሕዝብ ተከፍቶ ተቆጥታል ለሚለው ለአቢያዊው የኦህዴድ ቱልቱላ ፈጠራ የአማራ ሕዝብ ለአራት ዓመታት በመላ ኦሮሚያ ሲጨፈጨፍ ስለምን የኦሮሞ ሕዝብ ድርጊቱን ኮንኖ እና አውግዞ ድምጹን አላሰማን ብሎ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አልተቆጣም ። ሕዝባችን ሕዝብን እና ብልጣብልጥ ቁማርተኛ የፖለቲካ ሃይሎች ዘንድ አንድነት ሳይሆን ያለው ልዩነት ነው ብሎ የሚያምን የበሰለ ሕዝብ ነው። በአንጻሩም እነ አቢይና ኦንህዴዳዊያን የኦሮሞ ሕዝብ ልክ ደም እንደጠማውና የሰውን ደም ምሱ እንደሆነ ጭራቅ ንጹሃንን ለመጨፍጨፍ የተጋዙ ነፍሰ ገዳዮች ላይ ለተወሰደው እርምጃ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እንደተወሰደ እርምጃ አድርጎ ሕዝቡ ይህንን እያስተጋባ ነው የሚለን ከሆነ ያ የራሱ የአቢይ መራሹ ኦህዴዴዊ በሽታና  ችግር እንጂ  የእኛ የአማራዊያን ችግር አይደለም- አይሆንምም!!!!
በሁለቱ ሕዝብ መካከል አላስፈላጊ የጠላትነት ግንብ እየገነባ ያለው በኦሮሞ ስም ነጋዴው አቢይ መራሹ የኦህዴድ ብልጽግና ወንበዴ ቡድን ነው እንጁ ሌላ ማንም ጽንፈኛ በድን በዚህች ሀገር የለም።
ሊገድልህ የሚመጣን ማንኛውንም ሃይል መደምሰስ መብት ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮ አዊ  ግዴታም  ጭምር ነው።
የአቢይን ጭምብል ያስወለቁት የምንጃሮቹ አናብስት ፋኖዎቻችን ምስጋና ይሁንና ዛሬ ላለፉት አራት ዓመታት በዳቦ ስሙ ኦነግ ሸኔ እየተላከከ በሕዝባችን ላይ ሲፈጹም የነበረ ጭፍጨፋ በምንጃር በመክሸፉ የአቢይ ኦህዴድ በግላጭ የተደመሰሱት ጨፍጫፊ ታጣቂዎች የኦሮሚያ ጸጥታ አስከባሪዬ ናቸው በማለት ደማቸውን እበቀላለሁ ብሎ ተነስታል።
ይህንንም ውሳኔውን  በመንግስት መገናኛና አገልግሎት ምኒስትር ለገሰ ቱሉና በኦሮሚያው ሽመልስ አብዲሳ በኩል አስነግራል።
መላው አማራ እንደ አመጣጡና በአግባቡ ለማስተናገድ እና ብሎም እንደ አስፈላጊነቱ ማስተማሪያ ለመስጠት ወስኖ መዘጋጀት ነው እንጂ እሚጠበቅበት ከንቱ እስጥ አገባ ውስጥ ተዘፍቆ ጽንፈኛ ያለመሆኑን ለማሳመን መጋጋጥ አይጠበቅበትም።
ድል ለሰፊው የአማራ ሕዝብ!!!
በተባበረ አማራዊ አንድነት ክንድ አማራዊ ህልውናችንን እናስጠብቃለን!!!!
Filed in: Amharic