>

 በአዲስ አበባ የመሬት ስም ዝውውር, ለሚቀጥሉት 5 ወራት ታገደ ! (ባልደራስ)

 በአዲስ አበባ የመሬት ስም ዝውውር, ለሚቀጥሉት 5 ወራት ታገደ !
ባልደራስ

 
 አህዴዶች በመሬት ይዞታ ኦሮሞ ድርሻውን አልያዘም የሚል አቋም ይዘዋል!
/
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በከተማዋ ከሚያዚያ 5 2014  ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የመሬት ስም ዝውውር እንደማይኖር አስታወቀ።
እገዳው የተጣለው  በዚህ ዓመት በ10 ክፍለ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ 25 ቀጠናዎች ላይ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራ ስለሚሰራ ነው ተብሏል።
በዚሁ መሰረት ይዞታ የማረጋገጥ እና የእወጃ ሥራው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለ5 ወራት ይሠራል ተብሏል።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከንቲባ በነበሩበት ግዜ ተሰራ በተባለ ጥናት፣ የመሬት ባለይዞታዎች በአብዛኛው “በመጤዎችና ነፍጠኞች” ተይዟል ተብሎ በኦህዴዶች ዘንድ እየተነገረ ነው። በዚህም መሠረት፣ የመሬቱ ባለቤት ነው የሚሉትን ኦሮሞ ድርሻ በህጋዊውም ሆነ በኃይል ከፍ የማድረግ ፍላጎት አላቸው።  በከተማዋ ያለው  የቤት ፈረሳና የመሬት ወረራ በዋናነት ከዚህ እቅድ ጋር የተያያዘ ነው።
Filed in: Amharic