ስንታየሁ ቸኮል
መረጃ ከውስጥ የተገኘ
* … ኦነግ መልኩን የቀየረ ኦህዴድ ነው የሚሉት የመረጃዉ ባለቤት “ራሱ ገዳይ ራሱ ቀባሪ እራሱ አማፂ ሆኗል ሲሉ ገልፀዋል።” ማንኛውም ሰው ጥበቃ በሚደረግበት ቦታ መሄድ አይፈቀድለትም፣ መከላከያ ሲመጣ እለፉ ነው የሚባለው፣ በቅርብ ከሚታወቅ የኦሮሞ ተወላጅ ወጪ ወደ ሻምቡ ጫቶ ጫካ መሄድ አይችልም ሲሉ ጥቆማቸዉን ገልጸዋል። ” ኦነግ ማለት እራሱ ኦህዴድ ነው የሚለዉን አጠናክሮታል።
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ በሻምቡ ፣ኦዳ ቡልቅ (ሰቀላ) እና በጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ማዕከል ጫቶ የሚባል ረጅም ጫካ አለ በዉስጡ በግምት ከ15,000 ሺህ በላይ “የኦነግ ሸኔ” ታጣቂዎች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን እነዚህን …”የኦነግ ሸኔ” ሰራዊት ዙሪያውን የሚጠብቁት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል እና ሚኒሻ በጋራ መሆናቸዉ ተገለፀ።
በኦህዴድ መንግስት ዙሪያዉ የተለየ ጥበቃ የሚደረግለት ኦነግ ሸኔ ከዚህም አልፎ ስንቅና ትጥቅ ጫቶ ጫካ ውስጥ እንደሚገባላቸዉ ተናግረዋል።
ኦነግ መልኩን የቀየረ ኦህዴድ ነው የሚሉት የመረጃዉ ባለቤት “ራሱ ገዳይ ራሱ ቀባሪ እራሱ አማፂ ሆኗል ሲሉ ገልፀዋል።” ማንኛውም ሰው ጥበቃ በሚደረግበት ቦታ መሄድ አይፈቀድለትም፣ መከላከያ ሲመጣ እለፉ ነው የሚባለው፣ በቅርብ ከሚታወቅ የኦሮሞ ተወላጅ ወጪ ወደ ሻምቡ ጫቶ ጫካ መሄድ አይችልም ሲሉ ጥቆማቸዉን ገልጸዋል። ” ኦነግ ማለት እራሱ ኦህዴድ ነው የሚለዉን አጠናክሮታል።