እየታዘባችሁ…!!
ዘመድኩን በቀለ
“…የአገው ፈረሰኞች በዓል ላይ ለመታደም በስፍራው የተገኘችው ቅድስት ብርሃን በፌስቡክ ላይ በተለጠፈ ድንገቴ ፎቶዋ ምክንያት የተነሣ የብዙዎችን ቀልብ ሳበች። ማኅበራዊ ሚዲያውም በቅድስት ፎቶ ተጠለቀለቀ። ራዲዮ ጣቢያዎችና የቴሌቭዥን ጣቢያዎችም ተራወጡባት። እንግዳቸው አድርገው ለማቅረብም ተሻሙባት። ከዚያም አልፎ ከጉብሏ የዓይን ፍቅር ያዘን የሚሉ ዘማውያንም በርክተው ታዩ።
“…የቅድስትን አገው መሆን የሰሙ የኦሮሞ አክቲቪስቶችም “የአገዋ ቆንጆ” በማለት የእባብ ለሄዋን መወድስ አዘነቡላት። የወያኔ ካድሬና ሚዲያዎችም በተለየ መልኩ ዘገባ ሠሩላት። የእነ ፀጋዬ አራርሳው KMN ሚድያም የኩሽ ቆንጆ እያለ የእባብ ለሄዋን መወድሱን አጎረፈላት። አገውን ከዐማራ ለመነጠል ቅድስት ብርሃንን ለመጠቀም ኦህዴድኦነግም ተጣደፈ። ልጅቷን መቆሚያ መቀመጫም አሳጥተው አካለቧት፣ አዋከቧትም።
“…እኔ ደግሞ የልጅቷን መጨረሻ ለማየት ስል ዝም ብዬ እታዘብ ነበር። የአገው ሸንጎ የሚባል የወያኔ ጥፍፍም ሰሞኑን መድረክ ተሰጥቶት በቴሌቭዥን ጭምር ዐማራን እንዲሳደብ እያደረጉት አይቻለሁ። ያውም በአርቲስት አብርሃም ወልዴ የባላገሩ ቴሌቭዥን ላይ። የትግራይ ቴሌቭዥን በተለየ መልኩ ለአገው ብቻ የአየር ሰዓት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ጀምሯል። ለጎንደር ቅማንትን፣ ለወሎ ኦሮሞን፣ ለጎጃም አገውን ሰጥተን ዐማራን ከፋፍለን እናዳክማለን ነው ነገሩ። ፈረንሳይኛው እንደሱ መሆኑ ነው። ለትግሬ ኢሮብ፣ ኩናማ፣ አገው፣ ሰብዓ እንደርታ ቢሰጠው ምን ሊውጠው ነው።
“…በትግራይ “ትግሬ” የሚባል ዘር የሚኖረው ዓድዋ፣ ሽሬ እና አዲግራት ብቻ ነው የሚሉ አሉ። እነዚህ ሦስቱ ወረዳዎች ተሰባስበው አንድ ዞን መፍጠር ይችላሉ እንጂ እንደ ሃገር አክት ማድረግ አይችሉም የሚሉ አሉ። እንግሊዝኛ የሚያወራ ሁሉ እንግሊዛዊ እንዳልሆነ ሁሉ ትግርኛ ቢያወራም ባያወራም በግድ ትግሬ ነው ማለት ግን አይደለም የሚሉም አሉ። ለምሳሌ ተምቤን አገው ነው። አገውኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው። ኢሮብ ትግሬ አይደለም። የራሱ ቋንቋ ያለው ነገድ ነው። አክሱም ዐማራ ነው። ራያ ዐማራ ነው። ኩናማ ትግሬ አይደለም። ወልቃይት ዐማራ ነው። እንደርታም ትግሬ አይደለም።
“… እዚያው ትግራይ ለምሳሌ ትግሬዎች ኢሮቦችን “ስደተኛ” ብለው ነው የሚጠሩት። እንደርታን ደግሞ “ለማኝ” ነው የሚሉት። የአክሱምን ሰው ቀጥቃጭ፣ ቡዳ ነው የሚሉት። ደብተራም ነው ብለው ይሰድቡታል። ሃብታሞችም፣ ገዢዎችም አሽዓዎች ናቸው ይባላል። ከዚህ የተነሣ ዓድዋዎች የአክሱም ሴት አያገቡም። የእንደርታ ሰው መቀሌ ላይ ፋብሪካ ቢከፈት የተረፈው ነገር ቢኖር በዓድዋዎቹ ትግሬዎች መፈናቀል እና ወደ ልመና መሰማራት ነው።
“… ትግሬዎች ዐማራን ለመበታተን እንቅልፍ ስታጡ የሆነ ቀን ከራሳችሁ ውስጥ እንደዚያው እሳት ተነሥቶ እንዳይፈጃችሁ ተጠንቀቁ። ከአዲግራት፣ ሽሬ እና ዓድዋ ውጪ ትግሬ የሚባል የለም። ዓድዋም ቢሆን አያቱ ወይ ጎጃሜ፣ ወይ ወላይታ፣ ወይ ጉራጌ ነው። ከአሽዓ (አክሱም፣ ሽሬ፣ ዓድዋ ትግሬ ውጭ ሌላው የክልሉ ሰው ራሱን “ተጋሩ” ብሎ አይጠራም። ኢሮብ ኢሮብ ነው።
“…ትግራይ ክፍለሃገር” የሚባለውም የተመሠረተው በኢትዮጵያ ምክንያት እንጂ በትግሬነት ምክንያት አይደለም። ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ስላለች ነው ብዙ ነገዶች ያሉባት ትግራይ ትግራይ የሆነችው። የተባለችውም። እያንዳንዱ ጎሣ ወደማንነቱ ይመለስ ከተባለም ትግራይ ዞንም ወደማንነቷ ትመለሳለች። በትግሬነት ስም የታሠሩትም በትግራይ ክልል የሚገኙ ነገዶችም ነፃ ይወጣሉ። ከዚያም የራሳቸውን ዕድል ራሳቸው ይወስናሉ ማለት ነው።
“…ኦሮሞዎችም ተረጋጉ። ዐማራን ለመበታተንና ኢትዮጵያን ለመበታተን የምታደርጉትን ጥረት አቁሙ። የሸዋ ኦሮሞ፣ የወለጋ፣ የጉጂ፣ የቦረና፣ ምንትስዬ ቅብጥርስዬ ተብሎ ትግል ቢጀመር ምን ሊውጣችሁ ነው። ከዚያም ቤት እሳት አለ የሚለውን ተረት በደንብ ደጋግማችሁ ብትሰሙት መልካም ነው። በመስታወት ቤት የሚኖር የድንጋይ ውርወራ ፀብ ውስጥ አይሳተፍም። ሰው ተኝቶ ምራቅ ወደ ሰማይ አይተፋም። ከተፋ ግን መልሶ ይሚለደፈው ራሱ ላይ ነው። ጠላቴ ይገባበታል ብለህ ጉድጓድ አትቆፍር፣ ከቆፈርከው ግን የሚገባበት አይታወቅምና አርቀህ አትቆፍረው። ያለማወቅ ግን እንዴት ክፉ ጠላት ነው በማርያም።
“… ለምሳሌ… የሸዋን ኦሮሞ ከሌሎቹ ኦሮሞዎች ጋር በባህል አለባበስ፣ በቤት አሠራር፣ በሀዘንና ደስታ አገላለፅ፣ በአመጋገብ፣ በሃይማኖት አይመሳሰሉም በማለት ራሳቸው የሸዋ ኦሮሞዎች ይሟገታሉ።
1ኛ. በባህል፣ በአለባበስ የሽዋ ኦሮሞዎች ከሃረር ቆቱ፤ ከአሩሲ፣ ከባሌ፣ ከቦረና፣ ከጉጂ፣ ከጅማ እና ወለጋ ጋር ከቋንቋ ውጭ ከሸዋ ኦሮሞ ጋር የሚያመሳስል ነገር አንድም ነገር የለም።
2ኛ. በቤት አሠራር፣ በሀዘን እና በደስታ አገላለጽ ከሐረር ቆቱ፣ ከአሩሲ፣ ከባሌ፣ ከቦረና፣ ከጉጂ፣ ከጅማና ከወለጋ ጋር የሸዋ ኦሮሞ የሚያመሳስለው አንድም ነገር የለም።
3ኛ. በአመጋገብ የሸዋ ኦሮሞ የሚመገበው የጤፍ እንጀራ በጥሩ ወጥ ነው። ሌሎቹ የሚመገቡት የበቆሎ ገንፎ ነው። የሸዋ ኦሮሞ ገብስን ለቆሎ፣ ለእንጀራና ከዚያም አልፎ ጠላና አረቄ በማድረግ ይበሉታል፣ ይጠጡታል። ሌሎቹ ገብሱን ቢበሉትም በምንም ዓይነት ኬሚስትሪ ባህላዊ መጠጥ አያደርጉትም። የላቸውምም። በገብስ ፈንታ አብዛኛዎቹ ጫት ይቅማሉ ቡናንም ይበላሉ። ይጠጣሉም።
4ኛ. በሃይማኖት…የሸዋ ኦሮሞ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ነው። ሌሎቹ ደግሞ የእስልምናና የፕሮቴስታንት እምነትን ይከተላሉ። ከዚህ የተነሣም ኦርቶዶክስ ተከታዩን የሸዋ ኦሮሞ ሌሎቹ ይጠሉታል። ይገድሉታል። የእነሱን መስጊድና ቸርች እያስፋፉ የእሱን ቤተ ክርስቲያን ያወድሙበታል። ያቃጥሉበታል። ዐማራን በሚያዩበትዓይን ያዩታል። ዐማራን በሚጠሉበት አይንም ይጠሉታል። ኦርቶዶክስ እምነቱንም ለማዳከም እና ለመከፋፈል የሚሞክሩትም እነሱ ናቸው። ሥልጣን ለማግኘት እንኳ የሸዋ ኦሮሞ ወይ ፕሮቴስታንት፣ ወይ እስላም መሆንም አለበት። ሽመልስ አብዲሳ፣ ታከለ ዑማ፣ አዳነች አቢቤ በሙሉ የሸዋ ኦርቶዶክስ የነበሩና በቅርቡ ሃይማኖታቸውን ለሥልጣን ሲሉ ለውጠው መልሰው ወገናቸውንና ማንነታቸውን የሚወጉ ባንዳዎች ናቸው። ዐብይ አሕመድ የጅማ እስላምና ፕሮ መሆኑ ይያዝ።
“…ሌሎችን አቆይተን እስቲ የሃረር እና የሸዋ ኦሮሞን አናወዳድር የሚሉም አሉ። የሸዋ ኦሮሞ ሲናገር ረጋ ብሎ ነው። የሃረርጌው ደግሞ በአብዛኛው በጩኸት፤ በችኮላና በጥድፌያ ነው፡፡ በተፈጥሮም ያየን እንደሆነ እነሱ ባብዛኛው ጥርሳቸው ወጣ ወጣ ያለ ነው። የሸዋ ግን እንደዚያ አይደለም። እነሱ ሽርጥ ነው የሚለብሱት። ሸዋ ግን ሱሪና ኮት ነው የሚለብሰው። እነሱ ሜንጫና ገጀራ ይይዛሉ። ይሠሩበታልም። ይገዳደሉበታልም። ሸዋ ግን በአብዛኛው ዱላ ነው የሚይዘው። የቦረናና ጉጂ ኦሮሞ ደግሞ የወንድ ብልት ይሰልባሉ። የሸዋ ኦሮሞ እንኩዋን ብልት ሊሰልብ የሚሰልቡትንም ይጠየፋል። እነሱ የወንድብልት ባህላዊ ምልክት አድረገው ግንባራቸው ላይ አስረው ይውላሉ። ይህን አሳፋሪ ተግባር የሽዋ ኦሮሞዎች አያደርጉትም። በቱለማ ምድር በአዲስ አበባም ጭምር በኦሮሞ ባህል ማዕከል ላይ ይህንን አሳፋሪ ምልክት በሃውልት መልክ ሁላ ነው ያቆሙት። ይሄ የወንድ ብልት ቆርጦ ግንባር ላይ ማድረግ እስኪ በሞቴ ይላል ጠያቂው እስኪ በሞቴ እንኩዋን እኛን የሸዋ ኦሮሞዎችን ይቅርና የወለጋዎችንስ ይወክላልን በማለት ነው የሚጠይቀው?
“…የሽዋ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያን ለመመስረትና ከጠላት ለመከላከል አባቶቻቸው ትልቁን አስተዋጽኦ አድርገዋል። ሌሎቹ ግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጣም ትልቁን ጥረት አድረገዋል። እያደረጉም ነው። ለሀገራችን ህይወታቸውን የሰጡ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባቸው ጀግኖች ያሉት የሸዋ ኦሮሞ ነው። (ራስ ጎበና ዳጬ፣ አብዲሳ አጋ፣ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ወዘተ ማየት ይቻላል። እነሱ አንድም ለሀገር ምስረታና ከጠላት ለመከላከል አስተዋጽኦ ያደረጉ ጀግኖች የላቸውም። ከተጠቀሱት ጀግኖች ውስጥ አንዱ እንኳን አያከብሩም። ይነቅፋሉ፣ ይሰድባሉ። ለሱማሌ አግዞ ኢትዮጵያን ለወጋው ለዋቆ ጉቱ የሚሰጡትን ክብር ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ለኢትዮጵያ አንድነት የታገለውን ራስ ጎበና ዳጬን ከሃዲ ብለው ሀገር አፍራሽ የነበረውን ዋቆ ጉቱን ለማጀገን እንዴት እንደሚጥሩ አሳይተውናል፡፡
“… የአሩሲ ኦሮሞው ጃዋር መሐመድ የሸዋ ኦሮሞ ስብስብ የሆነውን ኦፌኮን ተቀላቅሎ በአክራሪ ጽንፈኞች የሞላው፣ ኦህዴድ ከወለጋና ከባሌ በስመ ኦሮሞ አምጥቶ ሸዋ ላይ ሥልጣን፣ መሬት፣ ገንዘብ ሰጥቶ ያፈሰሰውን የሸዋ ኦሮሞ ከገዛ ርስቱ እየተፈናቀለ ያለውን ረስቶት አይደለም። እናም ትግሬዎችም ኦሮሞዎችም ዐማራን ለመከፋፈል የምትሄዱበት መንገድ አያዋጣችሁምና እረፉ ለማለት ነው። የሚሻለው ተከባብሮ፣ ተቻችሎ መኖሩ ነው። ዐማራ እንደሆን ዲሞክራት ነው። ጨፍላቂም አይደለም። ለምሳሌ አሃዳዊነት ያለው ትግራይና ኦሮሚያ ነው። ዐማራ በውስጡ ለኦሮሞ፣ ለአገው፣ ለቅማንት እውቅና ሰጥቶ፣ በራሳቸው ቋንቋ፣ ዞንና ምክርቤት ሰጥቶ እያስተዳደረ ነው። በትግራይና በኦሮሚያ ግን በግድ ተጨፍልቀህ ኦሮሞና ትግሬ ተብለህ ትገዛለህ እንጂ የፌደራሊስትነት ሽታውም የለም። እናም ኦሮሞዎችና ትግሬዎች ተረጋጉ።
“…ነገርን ነገር አንሥቶ ሌላ ታሪክ ውስጥ ዶለኝ እንጂ እኔ እንኳ ማውራት የፈለግኩት ስለ አገዋ ቆንጂት ፍጻሜ ነው። ታዲያ እኔ ዘመዴ ምን ታዘብኩ መሰላችሁ ቅድስቴን አዳሜ ሆይ፣ ሆይ፣ ሆይ አላትና፣ ከኢንጅባራ አካልበው እያንደረደሩ ወደ ሸገር አመጧትና፣ ከማንነቷ አወጧት፣ በአንድ ጊዜም ያቺን የተፈጥሮ ውብ ሴት ቀለም ቀባብተው የአፈር ገንፎ ጦጣም አስመሰልዋት አረፉት። ያለ ሜካፕ በተፈጥሮ ውብ የሆነችውን የአገው ዐማራ ቆንጆ ሴት በአንዴ ዱቄት ቀብተው ያለ ቀለም ሰው የማይመስሉ ዱቄታሞች ከራሳቸው ተርታም አሰለፏት። ቅድስትም በአንደዜ ከልዕልትነት ወደ “ሰኞ ጠዋት ዝናብ ዘንቦ ፊትነት” ለወጧት። በቅድስቴ የደረሰ በእህታችሁም፣ በልጃችሁም፣ በሚስታችሁም አይድረስ። ቅድስትም ተረጋጊ። የኦነግና የህወሓትን ቦለጢቃም በደንብ መርምሪ። ከዶክተር ባልሽም ጋር እንዳፋቱሽም ሰምቻለሁ… ይሄ ሀሜት እውነት ከሆነ እመኚኝ ጋለሞታ፣ ሸርሙ* አድርገው ሊያስቀሩሽ ነውና በቶሎ ተመለሺ። አለበለዚያ የባልሽ ግፍ በራሱ በአፍጢምሽ ይደፋሻል። ድራሽ አባትሽንም ያጠፋሻል። እነሱ እንደሁ እንደ ኮንዶም ተጠቅሞ መወርወር ልማዳቸው ስለሆነ ተጠንቀቂ። የቀደመው ውበትሽም፣ ማንነትሽም ይሻልሻል ባይ ነኝ። ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።
“…እየታዘባችሁ…!!