>

የባልደራስ አመራሮች እና ልዑካን፤ ከታሰሩበት አለአግባብ እስር ተፈተዋል...!!! ያሰረን አዲስ አበባ ያለው ኦሕዴድ/ብልፅግና ነው...!!!" ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ

የባልደራስ አመራሮች እና ልዑካን፤ ከታሰሩበት አለአግባብ እስር ተፈተዋል…!!!
ባልደራስ

“.ያሰረን የአርባ ምንጭ ፖሊስ ሳይሆን አዲስ አበባ ያለው ኦሕዴድ/ብልፅግና ነው…!!!”
 ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ
በአርባ ምንጭ፤ ሴቻ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ታስረው ያደሩት እነ እስክንድር ነጋ ከደቂቃዎች በፊት በከተማዋ ወደ ሚገኘው ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ተወስደዋል። በአደሩበት ፖሊስ ጣቢያ ጧት ምርመራ ቢጀመርም “እኛ እንፈልጋቸዋለን፤ ምርመራውን አቋርጡት” በሚል ትዕዛዝ ነው ወደ ላይኛው የፖሊስ መዋቅር የተወሰዱት።
ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ኤርፖርት  
ከአንድ ቀን እስር በሗላ በእርባ ምንጭ መንቀሳቀስስ እንደማይችሉ ተነግሯቸው አርባ ምንጭን በአይሮፕላን እንዲለቁ ተደርገዋል:: ከፖሊስ ጣቢያ በቀጥታ ወደ ኤርፖርት::
በዶር አብይ አህመድ የሚመራው የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ: በምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጠውን እንቅስቃሴ: በዚህ መልክ ማገዱ የድርጅቱን ውስጣዊ ኪሳራንና  ሽንፈትን የሚይሳይ እንደሆነ ጠቋሚ ነው::
ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ “ያሰረን የአርባ ምንጭ ፖሊስ ሳይሆን አዲስ አበባ ያለው ኦሕዴድ/ብልፅግና ነው” ብለዋል ።
በእስር ላይ የነበሩት የባልደራስ አመራሮች እና ልዑካን፤ ከታሰሩበት አለአግባብ እስር ተፈተው ወደ አዲስ አበባ ተጉዘዋል።
“የታሰርነው ”ጋሞን አማራ ሊያደርጉ ነው’ በሚል ክስ ነው….!!!”
-አቶ ስንታየሁ ቸኮል”
ጋሞን አማራ ሊያደርጉ ” በሚል ክስ ታስረን የነበረ ቢሆንም አሁን ከእስር ተፈተናል።አስገራሚዉ መታሳራችን ሳይሆን የተከሰስንበት ክስ “ጋሞን አማራ ሊያደርጉ” የሚለው ነበር።
     የጋሞ ሕዝብ በፍቅር ሸኝቶናል!
Filed in: Amharic