>

የቦረናው ግፍ!! (ከዶ/ር በቃሉ አጥናፉ)

የቦረናው ግፍ!!

ከዶ/ር በቃሉ አጥናፉ

በቦረና ዞን ተልተሎ ወረዳ ባጋጠመው ድርቅ ምክንያት ከብቶቻቸውን ያጡ ገበሬዎች  ሰዎችን ጠምደው እንደ በሬ ሲያርሱባቸው ታይቷል፡፡ ይህ ክስተት ለኦህዴድ/ብልፅግናም ይሁን ለሌሎች የብልፅግና አመራሮች  ምንም ስሜት አይጭርም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ በሙስና ገንዘብ ማጋበስ ላይ ናቸው እንጂ የዜጎች ችግር፣ ብሶት እና ሰቆቃ አጀንዳቸው ሁኖም አያውቅም፤ ባስ ሲልም በዜጎች ህመም መሳለቅ የባህሪያቸው መገለጫ ነው፡፡  

የተስፋየ ገ/አብ የልብ ወለድ የሀሰት ትርክትን አምናችሁ፣ የአባስ ሀጂ ማስረጃ አልባ ቃላዊ መጣጥፎች እንደ እውነት ተመርኩዛችሁ የቂምን ሀውልት ከማቆም ይልቅ አፈር ጭሮ፣ የሰማይን ጠል ጠብቆ ለሚመግበን ገበሬ ዘመናዊ የእርሻ ማሳሪያዎችን ማቅረብ የገበሬውን ህይወት ምንኛ ባቀናው ነበር፡፡ ዳሩ ግን ለሆዳቸው ሲል ለተሰባሰቡ የብሄር ፖለቲከኞች እና የጎሳ ፖለቲካ ጠባቂዎች የገበሬው ህይወት ለአፋዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መጠቀሚያ ያደርጉታል እንጅ ለገበሬው ህይወት ጠብ የሚያደርጉለት አንዳች ነገር የለም፡፡ 

በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን እንኳንስ የሰውን ልጅ በሬንም ጠምዶ ማረስ የኃላ ቀር የአስተራረስ ዘዴ ነው፡፡ የሰው ልጅ እንደ በሬ  ተጠምዶ ሲታረስበት ማየት የአስተዳደር ችግር ነው፤ ልታፍሩበት ይገባል፡፡ 

Filed in: Amharic